ኑ፤ እግዚአብሔርን በመዝሙር እናመስግን! ለመዳናችን አምባም የድል እልልታ እናስተጋባለት! ወደ ፊቱ ቀርበን እናመስግነው፤ በዝማሬም ለእርሱ እልል እንበል! እግዚአብሔር ታላቅ ንጉሥ ነው፤ በሌሎች አማልክት ሁሉ ላይም ንጉሥ ነው። የመሬት ጥልቀቶች በመዳፉ ውስጥ ናቸው፤ የተራራ ጫፎችም የእርሱ ናቸው። እርሱ የፈጠረው ስለ ሆነ ባሕር የእርሱ ነው፤ የብስንም የፈጠሩ እጆቹ ናቸው። ኑ፤ ዝቅ ብለን እንስገድ! በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ!
መጽሐፈ መዝሙር 95 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 95:1-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos