ኑ፤ ደስ እያለን ለእግዚአብሔር እንዘምር፤ በድነታችንም ዐለት እልል እንበል። ምስጋና ይዘን ፊቱ እንቅረብ፤ በዝማሬም እናወድሰው። እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነውና፤ ከአማልክትም ሁሉ በላይ ታላቅ ንጉሥ ነው። የምድር ጥልቆች በእጁ ናቸው፤ የተራራ ጫፎችም የርሱ ናቸው። እርሱ ፈጥሯታልና ባሕር የርሱ ናት፤ እጁም የብስን አበጀ። ኑ፤ እናምልከው፤ እንስገድለትም፤ በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ፤
መዝሙር 95 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 95
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 95:1-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos