የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 90

90
እግዚአብሔርና ሰው
1እግዚአብሔር ሆይ!
በዘመናት ሁሉ አንተ መጠጊያችን ነህ።
2ተራራዎችን ከመሥራትህና ዓለምንም ከመፍጠርህ በፊት፥
አንተ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም አምላክ ነህ።
3ሰው ወደነበረበት እንዲመለስ ታዛለህ፤
ተመልሶም ትቢያ እንዲሆን ታደርገዋለህ።
4ለአንተ አንድ ሺህ ዓመት እንደ አንድ ቀን ነው፤
አልፎ እንደ ሄደው እንደ ትናንት ነው፤
እንደ ሌሊትም ጥቂት ሰዓቶች ነው። #2ጴጥ. 3፥8።
5ሕይወታችንን ልክ እንደ ሕልም ታሳልፈዋለህ፤
እኛ በየማለዳው እንደሚታደስ የሣር ቡቃያ ነን።
6ሣር ወዲያው አድጎ ያብባል፤
ሲመሽ ግን ጠውልጎ ይደርቃል።
7እኛ በቊጣህ ጠፍተናል፤
በመዓትህም ደንግጠናል።
8ኃጢአታችንን በፊትህ ታኖራለህ፤
የተሰወረውንም በደላችንን ለአንተ በሚታይ ቦታ ታስቀምጣለህ።
9ዘመናችን ሁሉ በቊጣህ ያልፋሉ
የዕድሜአችንም ፍጻሜ እንደ እስትንፋስ ነው።
10ዕድሜአችን ሰባ ዓመት ነው፤
ቢበዛም ሰማኒያ ዓመት ነው፤
እነዚያም ዘመናት በችግርና በሐዘን የተሞሉ ናቸው፤
ዕድሜአችን በቶሎ ያልቃል፤ እኛም እናልፋለን።
11አንተን የሚፈሩ ሰዎች ቊጣህን የሚረዱትን ያኽል፥
የአንተን የቊጣ ኀይል የሚያውቅ ማነው?
12ጥበበኞች ለመሆን እንድንችል
ዕድሜአችን ምን ያኽል አጭር እንደ ሆነ አስተምረን።
13እግዚአብሔር ሆይ!
ቊጣህ እስከ መቼ ይቈያል?
እባክህ ለአገልጋዮችህ ራራ!
14በዘመናችን ሁሉ እንድንዘምርና ደስ እንዲለን
ዘለዓለማዊውን ፍቅርህን በየማለዳው አሳየን።
15የመከራ ዓመቶች አሳልፈናል፤
ብዙ ሐዘንም ደርሶብናል፤
በዚህ ሁሉ ልክ ደስታን ስጠን።
16እኛ አገልጋዮችህ ታላቁን ሥራህን እንድናይ ፍቀድልን።
ልጆቻችንም የኀይልህን ክብር እንዲያዩ አድርጋቸው።
17እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ!
በረከትህ ከእኛ ጋር ይሁን፤
የምናደርገውንም ሁሉ አሳካልን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ