የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 148:1-5

መጽሐፈ መዝሙር 148:1-5 አማ05

እግዚአብሔርን አመስግኑ! ከላይ ከሰማያት አመስግኑት። እናንተ የእርሱ መላእክት ሁሉ አመስግኑት፤ በሰማይ ያላችሁ ሠራዊቱ ሁሉ አመስግኑት። ፀሐይና ጨረቃ አመስግኑት። የምትበሩ ከዋክብት ሁሉ አመስግኑት፤ ከፍተኞች ሰማያት አመስግኑት፤ ከጠፈር በላይ ያላችሁ ውሃዎችም አመስግኑት። ሁሉም የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ! እርሱ አዘዘ እነርሱም ተፈጠሩ።