የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 148

148
ፍጥረቶች ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግኑ
1እግዚአብሔርን አመስግኑ!
ከላይ ከሰማያት አመስግኑት።
2እናንተ የእርሱ መላእክት ሁሉ አመስግኑት፤
በሰማይ ያላችሁ ሠራዊቱ ሁሉ አመስግኑት።
3ፀሐይና ጨረቃ አመስግኑት።
የምትበሩ ከዋክብት ሁሉ አመስግኑት፤
4ከፍተኞች ሰማያት አመስግኑት፤
ከጠፈር በላይ ያላችሁ ውሃዎችም አመስግኑት።
5ሁሉም የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ!
እርሱ አዘዘ እነርሱም ተፈጠሩ።
6ምንጊዜም በማይፈርስ ድንጋጌ
ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም መሥርቶአቸዋል።
7የባሕር አራዊትና የውቅያኖስ ጥልቀቶች
እግዚአብሔርን ከምድር አመስግኑ።
8እሳትና በረዶ፥ ዐመዳይና ደመና፥
ትእዛዙን የምትፈጽሙም ብርቱዎች ነፋሳት
እግዚአብሔርን አመስግኑ።
9ኰረብቶችና ተራራዎች፥
የፍሬ ተክሎችና የደን ዛፎች ሁሉ አመስግኑት።
10አራዊትና ለማዳ እንስሶች፥
በምድር የምትሳቡና በክንፍ የምትበርሩ ፍጥረቶች ሁሉ
እግዚአብሔርን አመስግኑት።
11ነገሥታትና የምድር ሕዝቦች፥
መሳፍንትና ፈራጆች ሁሉ አመስግኑት።
12ጐልማሶችና ልጃገረዶች፥
ሽማግሌዎችና ልጆች ሁሉ አመስግኑት።
13የእርሱ ስም ከሌሎች ስሞች ስለሚበልጥና
ክብሩም ከምድርና ከሰማይ በላይ ከፍ ያለ ስለ ሆነ
ሁሉም የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ!
14ለእርሱ ቅርብ የሆኑትን ታማኝ አገልጋዮቹን እስራኤልን
ከፍ ከፍ አደረጋቸው፤
ምስጋናንም አቀዳጃቸው።
እግዚአብሔርን አመስግኑ!

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ