የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ምሳሌ 26

26
1በረዶ በበጋ ወራት፥ ዝናብም በመከር ወራት እንደማያስፈልግ ሁሉ ለሞኝ ክብር አይገባውም።
2ወፎች ወዲያና ወዲህ ሲበርሩ ምንም ጒዳት ሊያደርሱብህ እንደማይችሉ ሁሉ ከንቱ ርግማንም ምንም ጒዳት አያመጣብህም።
3ፈረስን መግረፍ በቅሎንም መለጐም እንደሚያስፈልግ ሁሉ ሰነፍንም መቅጣት ያስፈልጋል።
4የማይረባ ጥያቄ ለሚያቀርብልህ ሞኝ ሰው፥ አንተም እንደ እርሱ ሞኝ እንዳትሆን መልስ አትስጠው።
5ሆኖም ጠቢብ ነኝ ብሎ እንዳይመጣ ሞኝነቱን በመግለጥ መልስለት።
6ሞኝን መልእክተኛ ማድረግ የገዛ እግርን እንደ መቊረጥና ዐመፅን እንደ መጋበዝ ይቈጠራል።
7ሞኝ በምሳሌ የሚጠቀመው ሽባ ሰው በአንካሳ እግሮቹ የሚጠቀመውን ያኽል ነው።
8ለሞኝ ክብርን መስጠት ድንጋይን በወንጭፍ ላይ አጥብቆ አስሮ ለመወንጨፍ እንደ መሞከር ነው።
9የሞኝ በምሳሌ መናገር ሰካራም በእጁ ላይ የተሰካውን እሾኽ ለማውጣት እንደ መታገል ያለ ነው።
10በመንገድ የሚተላለፉትን ሞኞች ወይስ ሰካራሞች ሁሉ የሚቀጥር አሠሪ ያገኘውን ሰው ሁሉ እንደሚያቈስል ቀስት ወርዋሪ ነው።
11ሞኝነቱን ደጋግሞ የሚገልጥ ሞኝ ሰው ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ ውሻ ነው።
12በራሱ አስተሳሰብ ጠቢብ የሆነ ከሚመስለው ሰው ይልቅ ሞኝ ሰው ተስፋ አለው። 13ሰነፍ ሰው “አንበሳ በመንገድ ላይ አለ፤ የሚያስፈሩ አንበሶች በጐዳናዎች ይዘዋወራሉ” ይላል።
14መዝጊያ በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር ሰነፍም በአልጋው ላይ መገላበጥ ያበዛል።
15አንዳንድ ሰዎች በጣም ሰነፎች ናቸው፤ ሌላው ቀርቶ በወጥ ያጠቀሱትን እንጀራ መጒረስ ያታክታቸዋል።
16ሰነፍ፥ በቂ ማስረጃ ከሚሰጡ ከሰባት ሰዎች ይበልጥ አስተዋይ የሆነ ይመስለዋል።
17በማይመለከትህ ነገር መከራከር በመንገድ የሚተላለፈውን የውሻ ጆሮ እንደ መያዝ ይቈጠራል።
18-19ሰውን አታሎ “በቀልድ ነው ያደረግኹት” የሚል ሰው በአደገኛ የጦር መሣሪያ እንደሚጫወት ዕብድ ሰው ነው።
20እንጨት ከሌለ እሳት ይጠፋል፤ አሾክሿኪ ከሌለም ጠብ ይቆማል።
21ከሰል ፍምን፥ እንጨትም እሳትን እንደሚያበዛ ጠብ አጫሪ ሰው ጠብን ያባብሳል።
22የአሾክሻኪ ቃል እንደ ጣፋጭ ምግብ ደስ እያሰኘ እስከ ውስጥ ሰውነት ይወርዳል።
23በልቡ ክፋት እያለ በአንደበቱ ልዝብ ቃል የሚናገር ሰው ውጪው በሚያምር በብር ቀለም እንደ ተቀባ የሸክላ ዕቃ ነው።
24ተንኰለኛ ሰው በአፉ ይሸነግላል፤ በልቡ ግን ተንኰልን ያውጠነጥናል። 25እርሱም ልቡ በጥላቻ የተሞላ ስለ ሆነ፤ በሚያባብል ቃል ቢያቈላምጥህም አትመነው፤ 26ጥላቻውን ቢሰውርም፥ የሚያደርገው ክፉ ነገር በሰው ሁሉ ዘንድ ግልጥ ነው።
27ለሌሎች ወጥመድን የሚዘረጉ ሰዎች ራሳቸው ይያዙበታል፤ በሰው ላይ የሚሰዱት የድንጋይ ናዳ እነርሱን መልሶ ይጐዳቸዋል።
28ዋሾ አንደበት የሚጐዳቸውን ሰዎች ይጠላል፤ የሽንገላ ንግግርም ጥፋትን ያመጣል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ