1
መጽሐፈ ምሳሌ 26:4-5
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
የማይረባ ጥያቄ ለሚያቀርብልህ ሞኝ ሰው፥ አንተም እንደ እርሱ ሞኝ እንዳትሆን መልስ አትስጠው። ሆኖም ጠቢብ ነኝ ብሎ እንዳይመጣ ሞኝነቱን በመግለጥ መልስለት።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ምሳሌ 26:11
ሞኝነቱን ደጋግሞ የሚገልጥ ሞኝ ሰው ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ ውሻ ነው።
3
መጽሐፈ ምሳሌ 26:20
እንጨት ከሌለ እሳት ይጠፋል፤ አሾክሿኪ ከሌለም ጠብ ይቆማል።
4
መጽሐፈ ምሳሌ 26:27
ለሌሎች ወጥመድን የሚዘረጉ ሰዎች ራሳቸው ይያዙበታል፤ በሰው ላይ የሚሰዱት የድንጋይ ናዳ እነርሱን መልሶ ይጐዳቸዋል።
5
መጽሐፈ ምሳሌ 26:12
በራሱ አስተሳሰብ ጠቢብ የሆነ ከሚመስለው ሰው ይልቅ ሞኝ ሰው ተስፋ አለው።
6
መጽሐፈ ምሳሌ 26:17
በማይመለከትህ ነገር መከራከር በመንገድ የሚተላለፈውን የውሻ ጆሮ እንደ መያዝ ይቈጠራል።
Home
Bible
Plans
Videos