ሙሴ የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ፥ ሆባብን “እነሆ፥ እግዚአብሔር ሊሰጠን ቃል ወደገባልን ምድር ለመሄድ ተዘጋጅተናል፤ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደሚያበለጽግ ቃል ገብቶልናል፤ ስለዚህ አንተም ከእኛ ጋር አብረህ ሂድ፤ መልካም እናደርግልሃለን” አለው። ሖባብም “አይሆንም፤ እኔ ወደ ትውልድ አገሬና ወደ ዘመዶቼ እሄዳለሁ” አለው። ሙሴም እንዲህ አለው፤ “እባክህ ከእኛ ተለይተህ አትሂድ፤ በበረሓ ጒዞአችን የት መስፈር እንደሚገባን ታውቃለህ፤ የመንገድ መሪ ትሆንልናለህ፤ ከእኛ ጋር አብረህ ብትሄድ እግዚአብሔር የሚያደርግልንን መልካም ነገር ሁሉ ለአንተም እናካፍልሃለን።” ሕዝቡ የተቀደሰው ተራራ ያለበትን የሲናን ምድረ በዳ ትተው የሦስት ቀን መንገድ ተጓዙ፤ የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት የሚሰፍሩበትን ቦታ ለመፈለግ በፊታቸው ተጓዘ። ከእያንዳንዱ ሰፈር ሲለቁ የእግዚአብሔር ደመና በቀን ይጋርዳቸው ነበር። የቃል ኪዳኑ ታቦት በተንቀሳቀሰ ጊዜ ሁሉ ሙሴ “እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ጠላቶችህ ይበተኑ፤ የሚጠሉህም ሁሉ ከፊትህ ይባረሩ!” ይል ነበር። የቃል ኪዳኑም ታቦት ጒዞውን ባቆመ ጊዜ “በብዙ ሺህ ወደሚቈጠሩት ወደ እስራኤላውያን ሕዝብ ተመለስ” ይል ነበር።
ኦሪት ዘኊልቊ 10 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘኊልቊ 10:29-36
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች