ዘኍልቍ 10:29-36

ዘኍልቍ 10:29-36 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ሙሴም የሚ​ስ​ቱን አባት የም​ድ​ያ​ማ​ዊ​ውን የራ​ጉ​ኤ​ልን ልጅ ኦባ​ብን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ለእ​ና​ንተ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ ወዳ​ለው ስፍራ እን​ሄ​ዳ​ለን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እስ​ራ​ኤል መል​ካ​ምን ነገር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና አንተ ከእኛ ጋር ና፥ መል​ካ​ምን እና​ደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለን” አለው። እር​ሱም፥ “አል​ሄ​ድም፥ ነገር ግን ወደ ሀገ​ሬና ወደ ዘመ​ዶች እመ​ለ​ሳ​ለሁ” አለው። እር​ሱም፥ “እባ​ክህ፥ በም​ድረ በዳ ከእኛ ጋር ኑረ​ሃ​ልና በእ​ኛም ዘንድ አር​ጅ​ተ​ሃ​ልና አት​ተ​ወን፤ ከእ​ኛም ጋር ብት​ሄድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ልን መል​ካም ነገር ሁሉ እኛ ለአ​ንተ እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አለው። ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተራራ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ያህል ተጓዙ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የኪ​ዳኑ ታቦት የሚ​ያ​ድ​ሩ​በ​ትን ቦታ ታገ​ኝ​ላ​ቸው ዘንድ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ትቀ​ድ​ማ​ቸው ነበር። ሙሴም ታቦቷ በተ​ጓ​ዘች ጊዜ፥ “አቤቱ፥ ተነሣ፤ ጠላ​ቶ​ችህ ይበ​ተኑ፤ የሚ​ጠ​ሉ​ህም ከፊ​ትህ ይሽሹ” ይል ነበር። ባረ​ፈም ጊዜ፥ “አቤቱ፥ ወደ እስ​ራ​ኤል እልፍ አእ​ላ​ፋት ተመ​ለስ” ይል ነበር። ከሰ​ፈ​ራ​ቸ​ውም በተ​ጓዙ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደመና ቀን ቀን በላ​ያ​ቸው ላይ ነበረ።

ዘኍልቍ 10:29-36 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በዚህ ጊዜ ሙሴ የሚስቱን አባት የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ ኦባብን፣ “እነሆ፤ እግዚአብሔር፣ ‘እሰጣችኋለሁ’ ወዳለን ምድር ጕዞ ጀምረናል፤ በመልካም ሁኔታ ስለምናኖርህ ከእኛ ጋራ ሂድ፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል በጎ ነገር ለማድረግ ቃል ገብቷልና አለው።” እርሱም መልሶ፣ “ይህስ አይሆንም፤ አልሄድም፤ ወደ አገሬና ወደ ወገኖቼ ተመልሼ እሄዳለሁ” አለው። ሙሴ ግን እንዲህ አለ፤ “እባክህ አትለየን፤ በምድር በዳ ውስጥ የት መስፈር እንደሚገባን አንተ ታውቃለህ፤ ዐይናችንም ትሆናለህ። ከእኛ ጋራ ብትሄድ እግዚአብሔር ከሚያደርግልን መልካም ነገር ሁሉ እኛም እናደርግልሃለን።” ስለዚህ ከእግዚአብሔር ተራራ ተነሥተው የሦስት ቀን መንገድ ተጓዙ፤ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦትም በእነዚያ ሦስት ቀናት ውስጥ የሚያርፉበትን ቦታ በመፈለግ ፊት ፊታቸው ይሄድ ነበር። ከሰፈራቸው በሚነሡበት ጊዜ የእግዚአብሔር ደመና ቀን ቀን ከላያቸው ነበር። ታቦቱ ለጕዞ በተነሣ ጊዜ ሁሉ ሙሴ፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥ! ጠላቶችህ ይበተኑ፤ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ” ይል ነበር። ባረፉ ጊዜም፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ በብዙ ሺሕ ወደሚቈጠሩት እስራኤላውያን ተመለስ” ይል ነበር።

ዘኍልቍ 10:29-36 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ሙሴም የሚስቱን አባት የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ ኦባብን፦ እግዚአብሔር፦ ለእናንተ እሰጠዋለሁ ወዳለው ስፍራ እንሄዳለን፤ እግዚአብሔር ስለ እስራኤል መልካምን ነገር ተናግሮአልና አንተ ከእኛ ጋር ና፥ መልካምን እናደርግልሃለን አለው። እርሱም፦ አልሄድም፥ ነገር ግን ወደ አገሬና ወደ ዘመዶቼ እሄዳለሁ አለው። እርሱም፦ እባክህ፥ በምድረ በዳ የምንሰፍርበትን አንተ ታውቃለህና፥ እንደ ዓይኖቻችንም ትሆንልናለህና አትተወን፤ ከእኛም ጋር ብትሄድ እግዚአብሔር ከሚያደርግልን መልካም ነገር ሁሉ እኛ ለአንተ እናደርጋለን አለ። ከእግዚአብሔርም ተራራ የሦስት ቀን መንገድ ያህል ተጓዙ፤ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት የሚያድርበትን ስፍራ ይፈልግላቸው ዘንድ የሦስት ቀን መንገድ ቀደማቸው። ከሰፈራቸውም በተጓዙ ጊዜ የእግዚአብሔር ደመና ቀን ቀን በላያቸው ነበረ። ሙሴም ታቦቱ በተጓዘ ጊዜ፦ አቤቱ፥ ተነሣ፥ ጠላቶችህም ይበተኑ፥ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ ይል ነበር። ባረፈም ጊዜ፦ አቤቱ፥ ወደ እስራኤል እልፍ አእላፋት ተመለስ ይል ነበር።

ዘኍልቍ 10:29-36 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ሙሴ የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ፥ ሆባብን “እነሆ፥ እግዚአብሔር ሊሰጠን ቃል ወደገባልን ምድር ለመሄድ ተዘጋጅተናል፤ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደሚያበለጽግ ቃል ገብቶልናል፤ ስለዚህ አንተም ከእኛ ጋር አብረህ ሂድ፤ መልካም እናደርግልሃለን” አለው። ሖባብም “አይሆንም፤ እኔ ወደ ትውልድ አገሬና ወደ ዘመዶቼ እሄዳለሁ” አለው። ሙሴም እንዲህ አለው፤ “እባክህ ከእኛ ተለይተህ አትሂድ፤ በበረሓ ጒዞአችን የት መስፈር እንደሚገባን ታውቃለህ፤ የመንገድ መሪ ትሆንልናለህ፤ ከእኛ ጋር አብረህ ብትሄድ እግዚአብሔር የሚያደርግልንን መልካም ነገር ሁሉ ለአንተም እናካፍልሃለን።” ሕዝቡ የተቀደሰው ተራራ ያለበትን የሲናን ምድረ በዳ ትተው የሦስት ቀን መንገድ ተጓዙ፤ የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት የሚሰፍሩበትን ቦታ ለመፈለግ በፊታቸው ተጓዘ። ከእያንዳንዱ ሰፈር ሲለቁ የእግዚአብሔር ደመና በቀን ይጋርዳቸው ነበር። የቃል ኪዳኑ ታቦት በተንቀሳቀሰ ጊዜ ሁሉ ሙሴ “እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ጠላቶችህ ይበተኑ፤ የሚጠሉህም ሁሉ ከፊትህ ይባረሩ!” ይል ነበር። የቃል ኪዳኑም ታቦት ጒዞውን ባቆመ ጊዜ “በብዙ ሺህ ወደሚቈጠሩት ወደ እስራኤላውያን ሕዝብ ተመለስ” ይል ነበር።

ዘኍልቍ 10:29-36 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ሙሴም የሚስቱን አባት የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ ኦባብን እንዲህ አለው፦ “ጌታ፦ ‘ለእናንተ እሰጣችኋለሁ’ ወዳለው ስፍራ እንሄዳለን፤ ጌታ ለእስራኤል መልካምን ነገር ተናግሮአልና አንተ ከእኛ ጋር ና፥ መልካምን እናደርግልሃለን።” እርሱም፦ “አልሄድም፥ ነገር ግን ወደ አገሬና ወደ ዘመዶቼ እሄዳለሁ” አለው። ሙሴም እንዲህ አለው፦ “እባክህ፥ በምድረ በዳ የምንሰፍርበትን አንተ ታውቃለህና፥ እንደ ዐይኖቻችንም ትሆንልናለህና አትተወን፤ ከእኛም ጋር ብትሄድ ጌታ ከሚያደርግልን መልካም ነገር ሁሉ እኛ ለአንተ እናደርጋለን።” ከጌታም ተራራ ተነሥተው የሦስት ቀን መንገድ ያህል ተጓዙ፤ የጌታም የኪዳኑ ታቦት የሚያርፉበትን ስፍራ ለመፈለግ የሦስት ቀን መንገድ ቀድሞአቸው ተጓዘ። ከሰፈራቸውም በተጓዙ ጊዜ የጌታ ደመና ቀን ቀን በእነርሱ ላይ ነበረ። ሙሴም ታቦቱ በተጓዘ ጊዜ ሁሉ እንዲህ ይል ነበር፦ “አቤቱ፥ ተነሣ፥ ጠላቶችህም ይበተኑ፥ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ።” ባረፈም ጊዜ ሁሉ እንዲህ ይል ነበር፦ “አቤቱ፥ በብዙ ሺህ ወደሚቈጠሩት ወደ እስራኤል ልጆች ተመለስ።”