የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሉቃስ ወንጌል 2:41-52

የሉቃስ ወንጌል 2:41-52 አማ05

ዮሴፍና ማርያም በየዓመቱ ለፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዱ ነበር። ኢየሱስ ዐሥራ ሁለት ዓመት በሆነውም ጊዜ እንደ ተለመደው በዓሉን ለማክበር ሄዱ። በዓሉ ከተፈጸመ በኋላ እነርሱ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀረ፤ ዮሴፍና ማርያም ግን እዚያ መቅረቱን አላወቁም ነበር። ከመንገደኞች ጋር አብሮ የሚሄድ መስሎአቸው የአንድ ቀን መንገድ ሲጓዙ ዋሉ፤ ከዚያም በኋላ ከዘመዶቻቸውና ከሚያውቋቸው ሰዎች ዘንድ ይፈልጉት ጀመር። ነገር ግን ሊያገኙት ስላልቻሉ እየፈለጉት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። ከሦስት ቀንም በኋላ በቤተ መቅደስ አገኙት፤ በዚያም በሊቃውንት መካከል ተቀምጦ ሲያዳምጣቸውና ጥያቄም ሲያቀርብላቸው ነበር። የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ይገረሙ ነበር። ዮሴፍና ማርያም በቤተ መቅደስ ባዩት ጊዜ ተደነቁ፤ በዚያን ጊዜ እናቱ፥ “ልጄ ምነው እንዲህ አደረግኸን? አባትህና እኔ ተጨንቀን ስንፈልግህ ነበር” አለችው። ኢየሱስም “ስለምን ፈለጋችሁኝ? እኔ በአባቴ ቤት መሆን እንደሚገባኝ አታውቁም ኖሮአልን?” አላቸው። እነርሱ ግን እርሱ የተናገረውን አላስተዋሉም። ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ወደ ናዝሬት ሄደ፤ ይታዘዛቸውም ነበር፤ እናቱም ይህን ሁሉ ነገር በልብዋ ትይዘው ነበር። ኢየሱስ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት የተወደደ ሆኖ፥ በጥበብና በቁመት እያደገ ይሄድ ነበር።