“ነገር ግን የእናንተ ዘሮች የራሳቸውን ኃጢአት፥ እንዲሁም በእኔ ላይ ያመፁትንና የተቃወሙኝን የቀድሞ አባቶቻቸውን ኃጢአት ይናዘዛሉ፤ እነርሱን ተቃውሜ ወደ ጠላቶቻቸው አገር እንዲሰደዱ አደረግሁ፤ ሆኖም እልኸኛ ልባቸው በትሕትና ተሰብሮ ከኃጢአታቸው ቢታረሙ፥ ከያዕቆብ፥ ከይስሐቅና ከአብርሃም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስባለሁ፤ ምድሪቱንም ለሕዝቤ ለመስጠት የሰጠሁትን የተስፋ ቃል አድሳለሁ። ከሕዝብዋ ባዶ የሆነችው ምድር ውድማ ሆና ሰንበቶችን ታከብራለች፤ እነርሱም ሥርዓቴን ስላልተቀበሉና ሕጌን ስላላከበሩ፥ በኃጢአታቸው ምክንያት ቅጣቱን በሙሉ ይቀበላሉ። ይሁን እንጂ በጠላቶቻቸው አገር ሳሉ እንኳ እስከ መጨረሻ አልተዋቸውም ወይም አልደመስሳቸውም፤ ይህማ ቢሆን ኖሮ ከእነርሱ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን እስከ መጨረሻ ባልጠበቅሁም ነበር፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ነኝ። ነገር ግን አምላካቸው እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው ከአባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ስለ እነርሱ አስታውሳለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።” እግዚአብሔር በእርሱና በእስራኤል ሕዝብ መካከል በሙሴ አማካይነት በሲና ተራራ ላይ የሰጣቸው ደንቦች፥ ሥርዓቶችና ሕጎች እነዚህ ናቸው።
ኦሪት ዘሌዋውያን 26 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘሌዋውያን 26:40-46
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች