የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢዮብ 35

35
1ኤሊሁም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦
2“ኢዮብ ሆይ! በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ነኝ ማለትህ
ትክክል ነውን?
3‘ኃጢአት ባልሠራ ምን እጠቀማለሁ?
ምንስ አተርፋለሁ?’
ብለህ ትጠይቅ ይሆናል።
4አሁን እኔ ለአንተና ከአንተ ጋር ላሉ ለባልንጀሮችህ፥
መልስ እሰጣለሁ።
5“ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት፤
ከአንተ በላይ ከፍ ብሎ የሚታየውንም ደመና አስተውል።
6ኃጢአትን ብትሠራ እግዚአብሔርን በምን ትጐዳዋለህ?
በደልስ ብታበዛ ምን ታደርገዋለህ?
7ጻድቅ ብትሆን ለእግዚአብሔር ምን ትሰጠዋለህ?
እርሱ ከአንተ ምንም አይፈልግም።
8ኃጢአት ብትሠራ የምትጐዳው እንደ አንተ ያለውን ሰው ነው፤
መልካም ሥራ ብትሠራ፥ የምትጠቅመው ሰውን ነው። #ኢዮብ 22፥2-3።
9ሰዎች ጭቈና ሲበዛባቸው ይጮኻሉ፤
ከሚበረታባቸውም እጅ የሚታደጋቸውን ለማግኘት፥ አቤቱታ ያሰማሉ።
10ነገር ግን ከእነርሱ አንዳቸው እንኳ
በሌሊት ጥበቃ የሚያደርገው ፈጣሪ አምላክ
ወዴት ነው ብሎ አይጠይቅም።
11ከእንስሶች አብልጦ ያስተማረን
ከወፎችም ይልቅ ጥበበኞች ያደረገን እርሱ ነው።
12እነርሱ ይጮኻሉ
እርሱ ግን ትዕቢተኞችና ክፉዎች ስለ ሆኑ
መልስ አይሰጣቸውም።
13በእርግጥ እግዚአብሔር ከልብ ያልሆነ ጩኸትን አይሰማም፤
ሁሉን የሚችል አምላክም አያተኲርበትም።
14“ምንም እንኳ እግዚአብሔርን አላየውም ብትል
ጉዳይህ በእርሱ ፊት ስለ ሆነ
በትዕግሥት ልትጠብቀው ይገባል።
15እንዲሁም እግዚአብሔር በቊጣው የማይቀጣ፥
የሰውንም ክፋት በቸልታ የሚያልፍ ይመስልሃል?
16ኢዮብ ሆይ! በከንቱ ንግግር ታበዛለህ፤
ያለ ዕውቀትም ባዶ ቃላትን ትለፈልፋለህ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ