የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢዮብ 36

36
1ኤሊሁ አሁንም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦
2“ ስለ እግዚአብሔር የምናገረው ገና ሌላ ነገር ስላለ፥
እንዳብራራልህ ጥቂት ታገሠኝ።
3ከእግዚአብሔር ባገኘሁት ዕውቀት
ፈጣሪዬ እግዚአብሔር እውነተኛ መሆኑን አስረዳለሁ።
4ንግግሬ ሐሰት ላለመሆኑ እርግጠኛ ሁን፤
ከአንተ ጋር የምነጋገረው እኔ የተሟላ ዕውቀት እንዳለኝ ዕወቅ።
5“በእርግጥ እግዚአብሔር ኀያል ነው፤
ማንንም አይንቅም፤
እርሱም ሁሉንም ነገር ያስተውላል።
6እርሱ ክፉ ሰዎች በሕይወት እንዲኖሩ አያደርግም፤
ለተጨቈኑ ሰዎች ግን በቅንነት ይፈርድላቸዋል።
7እግዚአብሔር ደጋግ ሰዎችን ይጠብቃል፤
እንደ ነገሥታትም በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል፤
ለዘለዓለምም ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል።
8ነገር ግን ሰዎች በሰንሰለት ቢታሰሩ፥
ወይም በችግር ወጥመድ ቢያዙ፥
9እነርሱ በትዕቢታቸው፥
የሠሩትን ኃጢአት ይገልጥባቸዋል።
10ተግሣጽን እንዲሰሙ ጆሮአቸውን ይከፍትላቸዋል፤
ከክፉ ሥራቸውም ተመልሰው ንስሓ እንዲገቡ ያዛቸዋል።
11ለእግዚአብሔር ቢታዘዙና ቢያገለግሉ፥
ቀሪ ዘመናቸውን በብልጽግናና በደስታ ያሳልፋሉ።
12እርሱን ካልሰሙት በሰይፍ ይጠፋሉ፤
በድንቊርና እንዳሉም ይሞታሉ።
13“በልባቸው እግዚአብሔርን የሚክዱ ዘወትር እንደ ተቈጡ ይኖራሉ፥
ሲቀጣቸው እንኳ ይቅርታ ለማግኘት አይጸልዩም።
14በሚፈጽሙትም ግብረ ሰዶም ይቀሠፋሉ።
በወጣትነታቸውም በሞት ይቀጫሉ።
15እግዚአብሔር በሥቃይ ላይ ያሉትን፥ ከሥቃይ ያድናቸዋል።
በደረሰባቸውም መከራ ትምህርት ይሰጣቸዋል።
16“በአሁኑም ወቅት እግዚአብሔር የሚፈቅደው፥
አንተን ከችግር አውጥቶ ምርጥ በሆነ ምግብ
ወደተሞላ ማእድ ሊመራህ ነው።
17አሁን ግን የበደለኛ ፍርድ ስለ ተፈረደብህ፥
ተገቢ ቅጣትህን በመቀበል ላይ ነህ።
18ማንም ሰው በሀብት ብዛት እንዳያስትህ፥
በጉቦም እንዳይደልልህ ተጠንቀቅ።
19ሀብትህና ሥልጣንህ ምንም ያህል ከፍተኞች ቢሆኑ፥
ከጭንቀት አያድኑህም።
20ሕዝቦች ከስፍራቸው የሚጠፉበት
የጨለማ ጊዜ እንዲመጣ አትመኝ።
21በችግር የምትፈተነው በዚህ ምክንያት ስለ ሆነ
ተመልሰህ ክፉ ከመሥራት ተጠንቀቅ።
22የእግዚአብሔር ኀይል ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን አስተውል፤
እግዚአብሔር ከሁሉ የበለጠ አስተማሪ ነው።
23‘ይህን አድርግ’ ብሎ የሚያዘው፥
ወይም ‘ክፉ ሥራ ሠርተሃል’ ብሎ የሚወቅሰው ማነው?
24ሰዎች ሁልጊዜ በሚሠራው ሥራ በመዝሙር እንደሚያመሰግኑት።
አንተም የእርሱን ሥራ በመዝሙር አመስግን።
25የእግዚአብሔርን ሥራ የሰው ዘር ሁሉ አይቶታል፤
ሰዎች በሩቅ ይመለከቱታል።
26የእግዚአብሔርን ታላቅነት መርምረን ልንደርስበት አንችልም፤
የዘመኑንም ልክ መመርመር አይቻልም።
27“እግዚአብሔር ውሃን ከባሕር ወደ ላይ ይስባል፤
ከሰማይም ያዘንበዋል።
28ከደመናው ዝናብ እየጐረፈ ይወርዳል፤
በሰዎችም ላይ በብዛት ይዘንባል።
29ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ደመናውን እንዴት እንደሚዘረጋና
በነጐድጓድም ውስጥ ሆኖ እንዴት እንደሚናገር፥
ማን ሊረዳ ይችላል?
30እግዚአብሔር የባሕሩን ጥልቀት እየሸፈነ
መብረቁን በዙሪያው እንዴት እንደሚበትን ተመልከት።
31በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ሕዝብን ያስተዳድራል፤
ምግብንም በብዛት ያዘጋጅላቸዋል።
32መብረቅን በእጁ ይይዛል፤
ወደተወሰነለትም አቅጣጫ እንዲሄድ ያዘዋል።
33ነጐድጓድ፥ ኀይለኛ ዝናብ መምጣቱን ያመለክታል፤
እንስሶችም ውሽንፍር መምጣቱን ያውቃሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ