የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢዮብ 26

26
ኢዮብ
1ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፦
2“ይህን በመናገርህ ደካማውን የረዳኸው ይመስልህ ይሆን?
ክንዱ የዛለውንስ ያበረታኸው ይመስልህ ይሆን?
3ጥበብ ለጐደለው ምን ምክር ሰጠኸው!
ምንስ ዕውቀት ገለጥክለት!
4ለመሆኑ ይህን ቃል እንድትናገር የረዳህ ማነው?
ያነሣሣህስ የማን መንፈስ ነው?”
(ቢልዳድ)
5“ከውቅያኖስ በታች
ያሉት የሙታን ነፍሳት በከባድ መንቀጥቀጥ ላይ ናቸው።
6የሙታን ዓለም በእግዚአብሔር ፊት ግልጥልጥ ያለ ነው፤
ምንም ነገር ሊሸፍነው አይችልም።
7እግዚአብሔር የሰሜንን ሰማይ በሕዋው ላይ ዘረጋ፤
ምድርም በባዶ ቦታ እንድትንጠለጠል አደረገ።
8እግዚአብሔር፥ ደመናዎች ውሃን እንዲጠቀልሉ ያደርጋል፤
ከውሃውም የተነሣ ደመናዎቹ አይቀደዱም።
9የሙሉ ጨረቃውን ፊት ይጋርዳል፤
በደመና ይሸፍነዋል።
10ብርሃንና ጨለማን ለመለየት
በውቅያኖስ ፊት አድማስን ድንበር አድርጎ ዘረጋ።
11እርሱ በሚገሥጻቸው ጊዜ፥
የሰማይ አዕማድ በድንጋጤ ይናወጣሉ።
12በኀይሉ ባሕርን ጸጥ ያደርጋል፤
በጥበቡም ረዓብ የተባለውን ታላቅ አውሬ ያጠፋል።
13በእስትንፋሱ ሰማይን ያጠራል፤
በእጁም ተወርዋሪውን እባብ ይወጋል።
14እነዚህ ሁሉ እግዚአብሔር ከሚሠራቸው ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው፤
የምንሰማውም ሹክሹክታውን ብቻ ነው፤
የኀይሉን ነጐድጓድማ ማን ሊያስተውል ይችላል?”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ