መጽሐፈ ኢዮብ 25
25
ቢልዳድ
1ሹሐዊው ቢልዳድ እንዲህ ሲል መለሰ፤
2“ሥልጣንና መፈራት የእግዚአብሔር ነው፤
በላይኛው ግዛቱ በሰማይ ሰላምን ይመሠርታል።
3የሠራዊቱ ብዛት ሊቈጠር ይቻላልን?
የእርሱ ብርሃንስ የማያበራለት ማነው?
4እንዴት ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሆኖ ሊገኝ ይችላል?
ሰብአዊ ፍጡር ሆኖ እንዴት ንጹሕ ሊሆን ይችላል?
5እነሆ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጨረቃ እንኳ ደማቅ አይደለችም፤
ከዋክብትም በእርሱ ፊት ንጹሖች አይደሉም።
6በስባሽና ትል የሆነው ሟች ሰውማ
ምንኛ የባሰ ነው?”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 25: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997