የሊባኖስ ዛፎችን፥ የግራር እንጨቶችን፥ ባርሰነቱንና የወይራ ዛፎችን በበረሓ አበቅላለሁ፤ በምድረ በዳ ዝግባ፥ አስታና ጥድ፥ ወይራ የሞላበት ደን አበቅላለሁ። ይህን የማደርገው የእኔ የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገና እኔም የእስራኤል ቅዱስ እንደ ፈጠርኩት ሁሉም አይተው ያውቁ ዘንድ፥ አስተውለውም ይረዱ ዘንድ ነው።” የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፦ እንዲህ ይላል፦ “ጉዳያችሁን አቅርቡ፤ ማስረጃችሁንም አምጡ። ጣዖቶቻችሁንም አምጡና በሚፈጸምበት ጊዜ እንድናውቀው ወደ ፊት የሚሆነውን ሁሉ እስቲ ይንገሩን፤ ወደፊት ውጤታቸው ምን እንደሚሆን አስተውለን እንረዳ ዘንድ የቀድሞዎቹ ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ይንገሩን፤ ወይም ወደፊት ምን እንደሚከሠት ያስረዱን። እናንተም አማልክት መሆናችሁን እንድናውቅ ወደ ፊት የሚሆነውን ሁሉ እስቲ ንገሩን፤ እስቲ መልካም ነገርን አድርጉ፤ ወይም አይተንላችሁ በመፍራት እንድንሸበር ክፉ ነገርን ለማድረስ ሞክሩ። እናንተም ሆናችሁ ድርጊታችሁ በእርግጥ ከንቱ ነው፤ እናንተን ማምለክ የሚሹም አጸያፊዎች ናቸው። “እኔ እግዚአብሔር አንድ መሪ ከሰሜን አስነሥቼአለሁ፤ መጥቶአልም። እርሱም ስሜን የሚጠራና ከፀሐይ መውጫ በኩል የሚመጣ ነው። ሸክላ ሠሪ የሸክላውን ዐፈር እንደሚረግጥ መሪዎችን ይረግጣል። እናውቀው ዘንድና ትክክል ነው እንል ዘንድ ከመጀመሪያ ጀምሮ ይህን የተናገረ ማነው? ስለዚህ ጉዳይ መግለጫ የሰጠ፥ ወይም ያወጀ፥ ከእናንተም አንድ ቃል የተናገረ የለም። በመጀመሪያ ይህን ዜና ለጽዮን የገለጥኩላት እኔ ነኝ፤ ለኢየሩሳሌምም መልካም ዜና አብሣሪ የላክሁላት እኔ ነኝ። ዞር ብዬ በተመለከትኩ ጊዜ ማንም አልነበረም፤ ከአማልክትም መካከል ምክር የሚሰጥ አልነበረም፤ ጥያቄም ስጠይቅ ማንም መልስ የሚሰጥ አልነበረም። ስለዚህ እነዚህ አማልክት ሁሉ ከንቱ ናቸው፤ ምንም ነገር ሊያደርጉ አይችሉም፤ ምስሎቻቸውም እንደ ባዶ ነፋስ ናቸው።”
ትንቢተ ኢሳይያስ 41 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ትንቢተ ኢሳይያስ 41:19-29
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች