ኢሳይያስ 41:19-29
ኢሳይያስ 41:19-29 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በምድረ በዳ፣ ዝግባን፣ ግራርን፣ ባርሰነትንና ወይራን አበቅላለሁ፤ በበረሓ፣ ጥድን፣ አስታንና ሸውሸዌን በአንድነት እተክላለሁ። ስለዚህ ሰዎች ያያሉ፤ ያውቃሉ፤ የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገ፣ የእስራኤል ቅዱስ እንደ ፈጠረው፣ በአንድነት ይገነዘባሉ፤ ያስተውላሉም። “ሙግታችሁን ይዛችሁ ቅረቡ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ማስረጃችሁን አምጡ” ይላል የያዕቆብ ንጉሥ። “የሚሆነውን እንዲነግሩን፣ ጣዖቶቻችሁን አምጡ፤ እንድንገነዘብ፣ ፍጻሜአቸውን እንድናውቅ፣ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደ ነበሩ ንገሩን፤ ስለሚመጡትም ነገሮች ግለጹልን። እናንተ አማልክት መሆናችሁን እናውቅ ዘንድ፣ ወደ ፊት ስለሚሆነው ንገሩን፤ እንድንደነግጥ፣ በፍርሀት እንድንዋጥ፣ መልካምም ሆነ ክፉ፣ አንድ ነገር አድርጉ። እነሆ፤ እናንተ ከምንም የማትቈጠሩ ናችሁ፤ ሥራችሁ ፈጽሞ ዋጋ ቢስ ነው፤ የመረጣችሁም አስጸያፊ ነው። “አንዱን ከሰሜን አስነሣሁት፤ እርሱም ይመጣል፤ ከፀሓይ መውጫ የሚመጣው፣ ስሜን የሚጠራ ነው፤ ሸክላ ሠሪ ዐፈር እንደሚረግጥ፣ አለቆችን እንዲሁ እንደ ጭቃ ይረግጣል። እኛ እናውቅ ዘንድ ይህን ከመጀመሪያው የተናገረ፣ ‘እርሱ ትክክል ነው’ እንልም ዘንድ ቀድሞ የተናገረ ማነው? ማንም አልተናገረም፤ ቀደም ብሎ የተናገረ የለም፤ ቃላችሁንም የሰማ የለም። በመጀመሪያ፣ ‘እነሆ፤ ተመልከቺአቸው!’ ብዬ ለጽዮን የተናገርሁ እኔ ነበርሁ፤ ለኢየሩሳሌምም የምሥራች ነጋሪን ሰጥቻለሁ። ተመለከትሁ ማንም አልነበረም፤ ከመካከላቸው አማካሪ የለም፤ ስጠይቅም መልስ የሚሰጥ የለም። እነሆ፤ ሁሉም ከንቱ ናቸው! ሥራቸውም መና ነው፤ ምስሎቻቸውም ባዶ ነፋስ ናቸው።
ኢሳይያስ 41:19-29 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
በምድረ በዳ፤ ዝግባን፤ ግራርን፤ ባርሰነትንና ወይራን አበቅላለሁ፤ በበረሃ፤ ጥድን፤ አስታንና ሸውሸዌን በአንድነት እተክላለሁ። ስለዚህ የጌታ እጅ ይህን እንዳደረገ፥ የእስራኤል ቅዱስ እንደፈጠረው፥ ሰዎች እንዲያዩና እንዲያውቁ፥ በአንድነት እንዲገነዘቡ፤ እንዲያስተውሉም። ሙግታችሁን ይዛችሁ ቅረቡ፥ ይላል ጌታ፤ ማስረጃችሁን አምጡ፥ ይላል የያዕቆብ ንጉሥ። ያምጡ፥ የሚሆነውንም ይንገሩን፤ ልብም እድናደርግ፥ ፍጻሜአቸውንም እድናውቅ፥ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ተናገሩ፥ የሚመጡትንም አሳዩን። አማልክትም መሆናችሁን እድናውቅ፥ በኋላ የሚመጡትን ተናገሩ፤ እንድንደነግጥም፥ በአንድነትም እንድናይ፥ መልካሙን ወይም ክፉውን አድርጉ። እነሆ፥ እንዳልነበረ ናችሁ፥ ሥራችሁም ከንቱ ነው፤ የሚመርጣችሁም አስጸያፊ ነው። አንዱን ከሰሜን አነሣሁ መጥቶአልም፤ አንዱም ከፀሐይ መውጫ ስሜን የሚጠራ ይመጣል፤ በጭቃ ላይ እንደሚመጣ ሰው አፈርም እንደሚረግጥ ሸክለኛ በአለቆች ላይ ይመጣል። እድናውቀው ከጥንት የተናገረው፦ እውነት ነው፥ እንድንልም ቀድሞ የተናገረው ማን ነው? የሚናገር የለም፥ የሚገልጥም የለም፥ ቃላችሁንም የሚሰማ የለም። በመጀመሪያ ለጽዮን፦ እነሆ ተመልከች፥ እላለሁ፤ ለእየሩሳሌምም የምሥራች ነጋሪን እሰጣለሁ። ብመለከት ማንም አልነበረም፤ ብጠይቃቸውም የሚመልስልኝ አማካሪ በመካከላቸው የለም። እነሆ፥ እነርሱ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው፤ ሥራቸውም ምንም ናት፤ ቀልጠው የተሠሩት ምስሎቻቸውም ባዶ ነፋስ ናቸው።
ኢሳይያስ 41:19-29 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በምድረ በዳ ዝግባውንና ግራሩን፥ ባርሰነቱንና የዘይቱን ዛፍ አበቅላለሁ፤ ይኸውም የእግዚአብሔር እጅ ይህን ሁሉ እንደ ሠራ፥ የእስራኤልም ቅዱስ ይህን እንደ አሳየ ያውቁ ዘንድ፥ ያስተውሉም ዘንድ፥ ይረዱም ዘንድ፥ ያምኑም ዘንድ ነው። ፍርዳችሁ ቀረበች፥ ይላል እግዚአብሔር አምላክ፤ ምክራችሁም ቀረበ፥ ይላል የያዕቆብ ንጉሥ። ይምጡ፤ የሚደርስባችሁንም ይንገሩን፤ ልብም እናደርግ ዘንድ፤ ፍጻሜአቸውንም እናውቅ ዘንድ፥ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ንገሩን፤ የሚመጡትንም አሳዩን። አማልክትም መሆናችሁን እናውቅ ዘንድ በኋላ የሚመጡትን ተናገሩ፤ እናደንቃችሁም ዘንድ፥ በአንድነትም እናይ ዘንድ መልካሙን ወይም ክፉውን አድርጉ። እናንተ ከየት ናችሁ? ከየትስ ሠሯችሁ? ከምድር የሚመርጧችሁም የረከሱ አይደሉምን? ከሰሜንና ከፀሐይ መውጫ የሚመጡትን አስነሣሁ፤ በስሜም ይጠራሉ፤ አለቆች ይምጡ፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃና ጭቃን እንደሚረግጥ ሸክላ ሠሪ እንዲሁ ይረግጡአቸዋል። እናውቅ ዘንድ፥ ከጥንት የተነገረው፦ እውነት ነው እንልም ዘንድ ቀድሞ የተናገረው ማን ነው? ከመሆኑ በፊት የሚናገር የለም፤ የሚገልጥም የለም፤ ቃላችሁን የሚሰማ የለም። በመጀመሪያ ለጽዮን፦ ግዛትን እሰጣታለሁ፤ ኢየሩሳሌምንም ወደ መንገድዋ እመልሳታለሁ። ከአሕዛብና ከአማልክቶቻቸው የሚናገር የለምና፥ ከየትም እንደ ሆኑ ብጠይቃቸው አይመልሱልኝም። የሚሠሩአቸውም በከንቱ ይሠሩአቸዋል።
ኢሳይያስ 41:19-29 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በምድረ በዳ፣ ዝግባን፣ ግራርን፣ ባርሰነትንና ወይራን አበቅላለሁ፤ በበረሓ፣ ጥድን፣ አስታንና ሸውሸዌን በአንድነት እተክላለሁ። ስለዚህ ሰዎች ያያሉ፤ ያውቃሉ፤ የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገ፣ የእስራኤል ቅዱስ እንደ ፈጠረው፣ በአንድነት ይገነዘባሉ፤ ያስተውላሉም። “ሙግታችሁን ይዛችሁ ቅረቡ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ማስረጃችሁን አምጡ” ይላል የያዕቆብ ንጉሥ። “የሚሆነውን እንዲነግሩን፣ ጣዖቶቻችሁን አምጡ፤ እንድንገነዘብ፣ ፍጻሜአቸውን እንድናውቅ፣ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደ ነበሩ ንገሩን፤ ስለሚመጡትም ነገሮች ግለጹልን። እናንተ አማልክት መሆናችሁን እናውቅ ዘንድ፣ ወደ ፊት ስለሚሆነው ንገሩን፤ እንድንደነግጥ፣ በፍርሀት እንድንዋጥ፣ መልካምም ሆነ ክፉ፣ አንድ ነገር አድርጉ። እነሆ፤ እናንተ ከምንም የማትቈጠሩ ናችሁ፤ ሥራችሁ ፈጽሞ ዋጋ ቢስ ነው፤ የመረጣችሁም አስጸያፊ ነው። “አንዱን ከሰሜን አስነሣሁት፤ እርሱም ይመጣል፤ ከፀሓይ መውጫ የሚመጣው፣ ስሜን የሚጠራ ነው፤ ሸክላ ሠሪ ዐፈር እንደሚረግጥ፣ አለቆችን እንዲሁ እንደ ጭቃ ይረግጣል። እኛ እናውቅ ዘንድ ይህን ከመጀመሪያው የተናገረ፣ ‘እርሱ ትክክል ነው’ እንልም ዘንድ ቀድሞ የተናገረ ማነው? ማንም አልተናገረም፤ ቀደም ብሎ የተናገረ የለም፤ ቃላችሁንም የሰማ የለም። በመጀመሪያ፣ ‘እነሆ፤ ተመልከቺአቸው!’ ብዬ ለጽዮን የተናገርሁ እኔ ነበርሁ፤ ለኢየሩሳሌምም የምሥራች ነጋሪን ሰጥቻለሁ። ተመለከትሁ ማንም አልነበረም፤ ከመካከላቸው አማካሪ የለም፤ ስጠይቅም መልስ የሚሰጥ የለም። እነሆ፤ ሁሉም ከንቱ ናቸው! ሥራቸውም መና ነው፤ ምስሎቻቸውም ባዶ ነፋስ ናቸው።
ኢሳይያስ 41:19-29 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የእግዚዘብሔር እጅ ይህን እንደ ሠራች፥ የእስራኤልም ቅዱስ እንደ ፈጠረው ያዩ ዘንድ ያውቁም ዘንድ ያስቡም ዘንድ በአንድነትም ያስተውሉ ዘንድ፥ በምድረ በዳ ዝግባውንና ግራሩን ባርሰነቱንና የዘይቱን ዛፍ አበቅላለሁ፥ በበረሃውም ጥዱንና አስታውን ወይራውንም በአንድነት አኖራለሁ። ክርክራችሁን አቅርቡ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ማስረጃችሁን አምጡ፥ ይላል የያዕቆብ ንጉሥ። ያምጡ፥ የሚሆነውንም ይንገሩን፥ ልብም እናደርግ ዘንድ ፍጻሜአቸውንም እናውቅ ዘንድ፥ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደሆኑ ተናጋሩ፥ የሚመጡትንም አሳዩን። አማልክትም መሆናችሁን እናውቅ ዘንድ በኋላ የሚመጡትን ተናገሩ፥ እንደነግጥም ዘንድ በአንድነትም እናይ ዘንድ መልካሙን ወይም ክፉውን አድርጉ። እነሆ፥ እንዳልነበረ ናችሁ፥ ሥራችሁም ከንቱ ነው፥ የሚመርጣችሁም አስጸያፊ ነው። አንዱን ከሰሜን አነሣሁ መጥቶአልም፥ አንዱም ከፀሐይ መውጫ ስሜን የሚጠራ ይመጣል፥ በጭቃ ላይ እንደሚመጣ ሰው አፈርም እንደሚረግጥ ሸክለኛ በአለቆች ላይ ይመጣል። እናውቅ ዘንድ ከጥንት የተናገረው፦ እውነት ነው እንልም ዘንድ ቀድሞ የተናገረው ማን ነው? የሚናገር የለም፥ የሚገልጥም የለም፥ ቃላችሁንም የሚሰማ የለም። በመጀመሪያ ለጽዮን፦ እነኋቸው እላለሁ፥ ለእየሩሳሌምም የምስራች ነጋሪን እሰጣለሁ። ብመለከት ማንም አልነበረም፥ ብጠይቃቸውም የሚመልስልኝ አማካሪ በመካከላቸው የለም። እነሆ፥ እነርሱ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው፥ ሥራቸውም ምንምን ናት፥ ቀልጠው የተሠሩት ምስሎቻቸውም ነፋስና ኢምንት ናቸው።
ኢሳይያስ 41:19-29 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
የሊባኖስ ዛፎችን፥ የግራር እንጨቶችን፥ ባርሰነቱንና የወይራ ዛፎችን በበረሓ አበቅላለሁ፤ በምድረ በዳ ዝግባ፥ አስታና ጥድ፥ ወይራ የሞላበት ደን አበቅላለሁ። ይህን የማደርገው የእኔ የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገና እኔም የእስራኤል ቅዱስ እንደ ፈጠርኩት ሁሉም አይተው ያውቁ ዘንድ፥ አስተውለውም ይረዱ ዘንድ ነው።” የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፦ እንዲህ ይላል፦ “ጉዳያችሁን አቅርቡ፤ ማስረጃችሁንም አምጡ። ጣዖቶቻችሁንም አምጡና በሚፈጸምበት ጊዜ እንድናውቀው ወደ ፊት የሚሆነውን ሁሉ እስቲ ይንገሩን፤ ወደፊት ውጤታቸው ምን እንደሚሆን አስተውለን እንረዳ ዘንድ የቀድሞዎቹ ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ይንገሩን፤ ወይም ወደፊት ምን እንደሚከሠት ያስረዱን። እናንተም አማልክት መሆናችሁን እንድናውቅ ወደ ፊት የሚሆነውን ሁሉ እስቲ ንገሩን፤ እስቲ መልካም ነገርን አድርጉ፤ ወይም አይተንላችሁ በመፍራት እንድንሸበር ክፉ ነገርን ለማድረስ ሞክሩ። እናንተም ሆናችሁ ድርጊታችሁ በእርግጥ ከንቱ ነው፤ እናንተን ማምለክ የሚሹም አጸያፊዎች ናቸው። “እኔ እግዚአብሔር አንድ መሪ ከሰሜን አስነሥቼአለሁ፤ መጥቶአልም። እርሱም ስሜን የሚጠራና ከፀሐይ መውጫ በኩል የሚመጣ ነው። ሸክላ ሠሪ የሸክላውን ዐፈር እንደሚረግጥ መሪዎችን ይረግጣል። እናውቀው ዘንድና ትክክል ነው እንል ዘንድ ከመጀመሪያ ጀምሮ ይህን የተናገረ ማነው? ስለዚህ ጉዳይ መግለጫ የሰጠ፥ ወይም ያወጀ፥ ከእናንተም አንድ ቃል የተናገረ የለም። በመጀመሪያ ይህን ዜና ለጽዮን የገለጥኩላት እኔ ነኝ፤ ለኢየሩሳሌምም መልካም ዜና አብሣሪ የላክሁላት እኔ ነኝ። ዞር ብዬ በተመለከትኩ ጊዜ ማንም አልነበረም፤ ከአማልክትም መካከል ምክር የሚሰጥ አልነበረም፤ ጥያቄም ስጠይቅ ማንም መልስ የሚሰጥ አልነበረም። ስለዚህ እነዚህ አማልክት ሁሉ ከንቱ ናቸው፤ ምንም ነገር ሊያደርጉ አይችሉም፤ ምስሎቻቸውም እንደ ባዶ ነፋስ ናቸው።”