ኦሪት ዘፍጥረት 31:1-9

ኦሪት ዘፍጥረት 31:1-9 አማ05

የላባ ወንዶች ልጆች “ያዕቆብ የአባታችንን ሀብት ወሰደ፤ ይህን ሁሉ ሀብት ያገኘው ከአባታችን ነው” እያሉ መናገራቸውን ያዕቆብ ሰማ። በላባም ዘንድ እንደ ቀድሞው ተወዳጅ አለመሆኑን ተረዳ። በዚህን ጊዜ እግዚአብሔር ያዕቆብን “ወደ አባቶችህና ወደ ዘመዶችህ አገር ተመለስ፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ” አለው። ስለዚህ ያዕቆብ መንጋዎቹ ወደ ተሰማሩበት መስክ እንዲመጡ ራሔልንና ልያን አስጠራቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ “አባታችሁ እንደ ቀድሞው ጊዜ እንደማይወደኝ ተረድቼአለሁ፤ ነገር ግን የአባቴ አምላክ ከእኔ ጋር አለ፤ ጒልበቴን ሳልቈጥብ በትጋት አባታችሁን እንዳገለገልኩ እናንተም ታውቃላችሁ፤ እርሱ ግን ዐሥር ጊዜ ደመወዜን በመለዋወጥ አታለለኝ፤ ሆኖም እኔን ለመጒዳት እግዚአብሔር አልፈቀደለትም፤ ላባ ‘ዝንጒርጒሮቹ ሁሉ ለአንተ ደመወዝ ይሁኑ’ ባለኝ ጊዜ፥ መንጋዎቹ ሁሉ ዝንጒርጒር ወለዱ፤ ደግሞም ‘ሽመልመሌ መሳዮቹ ሁሉ ለአንተ ደመወዝ ይሁኑ’ ባለኝ ጊዜ፥ መንጋዎቹ ሁሉ ሽመልመሌ መሳዮች ወለዱ። እግዚአብሔር የአባታችሁን የላባን መንጋዎች ወስዶ ለእኔ የሰጠኝ በዚህ ዐይነት ነው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}