ዘፍጥረት 31:1-9

ዘፍጥረት 31:1-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ያዕ​ቆ​ብም የላባ ልጆች ያሉ​ትን ነገር፥ “ያዕ​ቆብ ለአ​ባ​ታ​ችን የሆ​ነ​ውን ሁሉ ወሰደ፤ ይህ​ንም ሁሉ ክብር ከአ​ባ​ታ​ችን ከብት አገኘ” ሲሉ ሰማ። ያዕ​ቆ​ብም የላ​ባን ፊት አየ፤ እነ​ሆም፥ ከእ​ርሱ ጋር እንደ ዱሮው አል​ሆ​ነም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዕ​ቆ​ብን፥ “ወደ አባ​ት​ህና ወደ ዘመ​ዶ​ችህ ሀገር ተመ​ለስ፤ እኔም ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ” አለው። ያዕ​ቆ​ብም ልኮ ራሔ​ል​ንና ልያን ወደ በጎቹ መሰ​ማ​ሪያ ወደ ሜዳ ጠራ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እነሆ፥ የአ​ባ​ታ​ችሁ ፊት እንደ ዱሮ ከእኔ ጋር እን​ዳ​ል​ሆነ አያ​ለሁ፤ ነገር ግን የአ​ባቴ አም​ላክ ከእኔ ጋር ነው። እኔ ባለኝ ጕል​በቴ ሁሉ አባ​ታ​ች​ሁን እን​ዳ​ገ​ለ​ገ​ልሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። አባ​ታ​ችሁ ግን አሳ​ዘ​ነኝ፥ ደመ​ወ​ዜ​ንም ዐሥር ጊዜ ለወጠ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ክፉን ያደ​ር​ግ​ብኝ ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደ​ለ​ትም። ደመ​ወ​ዝህ ዝን​ጕ​ር​ጕ​ሮቹ ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ዝን​ጕ​ር​ጕ​ሮ​ችን ወለዱ፤ ነጫ​ጮቹ ደመ​ወ​ዝህ ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ነጫ​ጮ​ችን ወለዱ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የአ​ባ​ታ​ች​ሁን በጎች ሁሉ ነሥቶ ለእኔ ሰጠኝ።

ዘፍጥረት 31:1-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የላባ ወንዶች ልጆች፣ “ያዕቆብ የአባታችንን ሀብት እንዳለ ወስዶታል፤ ይህ ሁሉ እርሱ ያካበተውም ሀብት ከአባታችን የተገኘ ነው” እያሉ ሲያወሩ ያዕቆብ ሰማ። የላባ አመለካከት ከቀድሞው የተለወጠበት መሆኑንም ያዕቆብ ተረዳ። እግዚአብሔርም ያዕቆብን፣ “ወደ አባቶችህና ዘመዶችህ አገር ተመለስ፤ እኔም ካንተ ጋራ እሆናለሁ” አለው። ስለዚህም ያዕቆብ መንጎቹ ወደ ተሰማሩበት መስክ እንዲመጡ፣ ራሔልንና ልያን አስጠራቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ “አባታችሁ ስለ እኔ ያለው አመለካከት እንደ ቀድሞው አለመሆኑን ተረድቻለሁ፤ ቢሆንም የአባቴ አምላክ አልተለየኝም፤ መቼም ባለኝ ዐቅም አባታችሁን ማገልገሌ ከእናንተ የተሰወረ አይደለም። አባታችሁ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ እየለዋወጠ አታልሎኛል፣ ሆኖም እንዲጐዳኝ እግዚአብሔር አልፈቀደለትም። እርሱ፣ ‘ደመወዝህ ዝንጕርጕሮቹ ይሆናሉ’ ሲለኝ፣ መንጎቹ ሁሉ ዝንጕርጕር ወለዱ፤ ደግሞም ‘ደመወዝህ ሽመልመሌዎቹ ይሆናሉ’ ሲለኝ፣ መንጎቹ ሁሉ ሽመልመሌ መልክ ያላቸውን ወለዱ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የአባታችሁን ከብቶች ወስዶ ለእኔ ሰጠኝ።

ዘፍጥረት 31:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ያዕቆብም የላባ ልጆች ያሉትን ነገር፦ ያዕቆብ ለአባታችን የሆነውን ሁሉ ወሰደ ይህንም ሁሉ ክብር ከአባታችን ከብት አገኘ ሲሉ ሰማ። ያዕቆብም የላባን ፊት አየ እነሆም ከእርሱ ጋር እንደ ዱሮው አልሆነም። እግዚአብሔርም ያዕቆብን፦ ወደ አባትህ ምድር ወደ ዘመዶችህም ተመለስ ከአንተም ጋር እሆናለሁ አለው። ያዕቆብም ልኮ ራሔልንና ልያን ወደ በጎቹ ስፍራ ወደ ሜዳ ጠራቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ የአባታችሁ ፊት ከእኔ ጋር እንደ ዱሮ እንዳልሆን አያለሁ ነገር ግን የአባቴ አምላክ ከእኔ ጋር ነው። እኔ ባለኝ ጕልበቴ ሁሉ እንዳገለገልሁ ታውቃላችሁ። አባታችሁ ግን አታለለኝ ደመወዜንም አሥር ጊዜ ለወጠ እግዚአብሔር ግን ክፋን ያደርግብኝ ዘንድ አልፈቀደለትም። ደመወዝህ ዝንጕርጕሮች ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ዝንጕርጕሮችን ወለዱ ሽመልመሌ መሳዮቹ ደመወዝህ ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ሽመልመሌ መሳዮችን ወለዱ። እግዚአብሔርም የአባታችሁን በጎቹ ሁሉ ነሥቶ ለእኔ ሰጠኝ

ዘፍጥረት 31:1-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የላባ ወንዶች ልጆች “ያዕቆብ የአባታችንን ሀብት ወሰደ፤ ይህን ሁሉ ሀብት ያገኘው ከአባታችን ነው” እያሉ መናገራቸውን ያዕቆብ ሰማ። በላባም ዘንድ እንደ ቀድሞው ተወዳጅ አለመሆኑን ተረዳ። በዚህን ጊዜ እግዚአብሔር ያዕቆብን “ወደ አባቶችህና ወደ ዘመዶችህ አገር ተመለስ፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ” አለው። ስለዚህ ያዕቆብ መንጋዎቹ ወደ ተሰማሩበት መስክ እንዲመጡ ራሔልንና ልያን አስጠራቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ “አባታችሁ እንደ ቀድሞው ጊዜ እንደማይወደኝ ተረድቼአለሁ፤ ነገር ግን የአባቴ አምላክ ከእኔ ጋር አለ፤ ጒልበቴን ሳልቈጥብ በትጋት አባታችሁን እንዳገለገልኩ እናንተም ታውቃላችሁ፤ እርሱ ግን ዐሥር ጊዜ ደመወዜን በመለዋወጥ አታለለኝ፤ ሆኖም እኔን ለመጒዳት እግዚአብሔር አልፈቀደለትም፤ ላባ ‘ዝንጒርጒሮቹ ሁሉ ለአንተ ደመወዝ ይሁኑ’ ባለኝ ጊዜ፥ መንጋዎቹ ሁሉ ዝንጒርጒር ወለዱ፤ ደግሞም ‘ሽመልመሌ መሳዮቹ ሁሉ ለአንተ ደመወዝ ይሁኑ’ ባለኝ ጊዜ፥ መንጋዎቹ ሁሉ ሽመልመሌ መሳዮች ወለዱ። እግዚአብሔር የአባታችሁን የላባን መንጋዎች ወስዶ ለእኔ የሰጠኝ በዚህ ዐይነት ነው።

ዘፍጥረት 31:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ያዕቆብም፥ የላባ ልጆች፦ “ያዕቆብ የአባታችን የሆነውን ሁሉ ወሰደ፥ የአባታችን ከነበረውም ይህንም ሁሉ ሀብት አገኘ” ሲሉ ሰማ። እንደ ቀድሞው በላባ ተወዳጅ አለመሆኑን ያዕቆብም አየ። በዚህን ጊዜ ጌታ ያዕቆብን፥ “ወደ አባቶችህ ምድር እና ወደ ዘመዶችህ ተመለስ፥ ከአንተም ጋር እሆናለሁ” አለው። ያዕቆብም ላከና ራሔልንና ልያን በጎቹ ወደ ነበሩበት መስክ ጠራቸው፥ እንዲህም አላቸው፥ “አባታችሁ ከእኔ ጋር እንደ ቀድሞው እንደማይወደኝ አያለሁ፥ ነገር ግን የአባቴ አምላክ ከእኔ ጋር ነው። እኔ ባለኝ ጉልበቴ ሁሉ አባታችሁን እንዳገለገልኩ እናንተም ታውቃላችሁ። አባታችሁ ግን አታለለኝ፥ ደመወዜንም ዐሥር ጊዜ ለወጠ፥ እግዚአብሔር ግን ይጎዳኝ ዘንድ አልፈቀደለትም። ‘ዝንጉርጉሮቹ ሁሉ ለአንተ ደመወዝ ይሁኑ’ ቢለኝ፥ መንጋዎቹ ሁሉ ዝንጉርጉሮችን ወለዱ፤ ደግሞም ‘ሽመልመሌ መሳዮቹ ሁሉ ለአንተ ደመወዝ ይሁኑ’ ቢለኝ፥ መንጋዎቹ ሁሉ ሽመልመሌ ወለዱ። እግዚአብሔርም የአባታችሁን በጎች ሁሉ ነሥቶ ለእኔ ሰጠኝ።