መጽሐፈ መክብብ መግቢያ
መግቢያ
በመጽሐፈ መክብብ ሰፍረው የሚገኙት የሰው ሕይወት አጭር ከመሆኑም በላይ ውጣ ውረድና ውዝግብ፥ የተወሳሰበ ፍርደ ገምድልነትና መታከት የሞላበት መሆኑን ከመረዳቱ የተነሣ “የሰው ሕይወት ከንቱ ነው” ብሎ የደመደመ የአንድ ፈላስፋ ሐሳቦች ናቸው። ይህ ፈላስፋ የሰዎችን የኑሮ አቅጣጫ የሚቈጣጠረውን የእግዚአብሔርን አሠራር ለመረዳት ተስኖታል፤ ይሁን እንጂ በሚኖሩበት ዘመን ሁሉና በተቻላቸውም አቅም በትጋት መሥራትና በእግዚአብሔርም ስጦታዎች መደሰት እንዳለባቸው ለሰዎች ምክር ይለግሣል።
ከፈላስፋው ሐሳቦች አብዛኞቹ ተቃራኒ አመለካከት ያላቸውና በተስፋ መቊረጥ ስሜት የተሞሉ ናቸው፤ ይሁን እንጂ ይህ መጽሐፍ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መገኘቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተው እምነት ሌላው ቀርቶ ይህን ተቃራኒ ሐሳብና ጥርጣሬ የተሞላበትን መጽሐፍ ጨምሮ እስከሚይዝ ድረስ ሰፊ መሆኑን ያስገነዝባል። ይህ መጽሐፍ የሰውን ሕይወት እንደ መስተዋት ስለሚያሳይ ብዙ ሰዎች ከዚህ መጽሐፍ መጽናናትን አግኝተዋል፤ እንዲሁም እነዚሁኑ ሐሳቦች የሚያሳየው፥ ይኸው አንዱ መጽሐፍ ቅዱስ፥ ለሕይወት ታላቅ ትርጒም በሚሰጠው እግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ እንደሚችሉ የሚመክር መሆኑን ተረድተዋል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
የመኖር ትርጒሙ 1፥1—2፥26
ለሁሉ ጊዜ አለው 3፥1-8
ሕይወት ሁልጊዜ በጎ ስለማይሆን በጥበብ መኖር 3፥9—6፥12
ወደ ፊት ምን እንደሚሆን የሚያውቅ የለም 9፥1—11፥6
እግዚአብሔርን ማክበርና ለእርሱ መታዘዝ 11፥7—12፥14
Currently Selected:
መጽሐፈ መክብብ መግቢያ: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997