2 ወደ ጢሞቴዎስ 1:15-18

2 ወደ ጢሞቴዎስ 1:15-18 አማ05

በእስያ ያሉት ሁሉ እኔን ትተውኝ እንደ ሄዱ ታውቃለህ፤ ከእነርሱም መካከል ፊጌሉስና ሄርሞጌኔስ ይገኛሉ። ጌታ ለኦኔሲፎር ቤተሰቦች ምሕረትን ይስጥ፤ እርሱ ብዙ ጊዜ አጽናንቶኛል፤ በመታሰሬም አላፈረም። እንዲያውም ወደ ሮም በመጣ ጊዜ በትጋት ፈልጎ አገኘኝ፤ በመጨረሻው ቀን ጌታ ምሕረትን ይስጠው፤ በኤፌሶን በነበርኩበት ጊዜ ምን ያኽል እንዳገለገለኝ አንተ ራስህ ደኅና አድርገህ ታውቃለህ።