2 ጢሞቴዎስ 1:15-18

2 ጢሞቴዎስ 1:15-18 NASV

በእስያ አውራጃ ያሉት ሁሉ እንደ ተዉኝ ታውቃለህ፤ ከእነርሱም መካከል ፊሎጎስና ሄርዋጌኔስ ይገኛሉ። ጌታ ለሄኔሲፎሩ ቤተ ሰዎች ምሕረትን ይስጥ፤ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ቸርነት አድርጎልኛል፤ በታሰርሁበትም ሰንሰለት አላፈረም። እንዲያውም ወደ ሮም በመጣ ጊዜ ፈልጎ ፈልጎ አገኘኝ። በዚያች ቀን ምሕረትን ከጌታ ያገኝ ዘንድ ጌታ ይስጠው፤ በኤፌሶንም የቱን ያህል እንዳገለገለኝ አንተ በሚገባ ታውቃለህ።