የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

2 ወደ ጢሞቴዎስ 1

1
1በኢየሱስ ክርስቶስ በተገኘው የሕይወት ተስፋ መሠረት በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ የተላከ፥
2ለተወደድከው ልጄ ለጢሞቴዎስ፥
ከእግዚአብሔር አብና ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ለአንተ ይሁን። #ሐ.ሥ. 16፥1።
ለጢሞቴዎስ የተሰጠ ምክር
3ዘወትር ሌሊትና ቀን አንተን በጸሎቴ ሳስታውስ አባቶቼ እንደ አደረጉት እኔም በንጹሕ ኅሊና የማገለግለውን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። 4እንባህን አስታውሳለሁ፤ ስለዚህ በጣም ደስ እንዲለኝ አንተን ለማየት እመኛለሁ። 5በአንተ ያለውን እውነተኛ እምነት አስታውሳለሁ፤ እንዲህ ዐይነቱ እምነት በመጀመሪያ በአያትህ በሎይድና በእናትህ በኤውኒቄ የነበረ ነው፤ በአንተም እንዳለ ተረድቼአለሁ። #ሐ.ሥ. 16፥1። 6በዚህ ምክንያት እጆቼን በአንተ ላይ በጫንኩ ጊዜ የተሰጠህንና እንደ እሳት ሆኖ በአንተ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንደገና እንድታቀጣጥለው አሳስብሃለሁ። 7እግዚአብሔር የሰጠን የኀይልና የፍቅር፥ ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አይደለም።
8እንግዲህ ስለ ጌታችን ለመመስከር አትፈር፤ ስለ እርሱ በታሰርኩት በእኔም አትፈር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በሚሰጥህ ኀይል ስለ ወንጌል ከእኔ ጋር መከራን ተቀበል። 9እርሱ እኛ ስላደረግነው መልካም ሥራ ሳይሆን በራሱ ፈቃድና በጸጋው አዳነን፤ ለቅድስናም ጠራን፤ ይህንንም ጸጋ ከዘመናት በፊት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሰጠን። 10ይህም ጸጋ አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመምጣቱ አሁን ተገለጠ። እርሱ የሞትን ኀይል ደምስሶ በወንጌል አማካይነት ሞት የሌለበትን ዘለዓለማዊ ሕይወት ገለጠልን።
11እኔም የዚህ ወንጌል አብሣሪ፥ ሐዋርያ፥ አስተማሪ ሆኜ ተሾሜአለሁ። #1ጢሞ. 2፥7። 12ይህን መከራ የምቀበለውም በዚህ ምክንያት ነው፤ ነገር ግን ማንን እንዳመንኩ ስለማውቅ አላፍርበትም፤ የተሰጠኝንም ዐደራ እስከዚያ ቀን ድረስ መጠበቅ እንደምችል ተረድቼአለሁ። 13ከእኔ የተማርከውን አስተማማኝ ቃል እንደ ምሳሌ አድርገህ በኢየሱስ ክርስቶስ ባለን እምነትና ፍቅር ጠብቅ። 14በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የተሰጠህን መልካም ዐደራ ጠብቅ።
15በእስያ ያሉት ሁሉ እኔን ትተውኝ እንደ ሄዱ ታውቃለህ፤ ከእነርሱም መካከል ፊጌሉስና ሄርሞጌኔስ ይገኛሉ። 16ጌታ ለኦኔሲፎር ቤተሰቦች ምሕረትን ይስጥ፤ እርሱ ብዙ ጊዜ አጽናንቶኛል፤ በመታሰሬም አላፈረም። 17እንዲያውም ወደ ሮም በመጣ ጊዜ በትጋት ፈልጎ አገኘኝ፤ 18በመጨረሻው ቀን ጌታ ምሕረትን ይስጠው፤ በኤፌሶን በነበርኩበት ጊዜ ምን ያኽል እንዳገለገለኝ አንተ ራስህ ደኅና አድርገህ ታውቃለህ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ