2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13:5-8

2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13:5-8 አማ05

በእምነታችሁ የጸናችሁ መሆናችሁን ለማረጋገጥ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችሁ መሆኑን አልተገነዘባችሁምን? አለበለዚያ በፈተና ወድቃችኋል ማለት ነው፤ እኛ በፈተና አለመውደቃችንን እንደምትገነዘቡ ተስፋ እናደርጋለን። ክፉ ነገር እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ የምንጸልየውም ምንም እንኳ እኛ ብቁዎች ሆነን ሳንታይ ብንቀር እናንተ ዘወትር መልካም የሆነውን ነገር እንድታደርጉ ነው እንጂ የእኛን ብቃት ለማሳየት አይደለም። እኛ ስለ እውነት እንሠራለን እንጂ የእውነት ተቃራኒ የሆነ ምንም ነገር አንሠራም።