2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13
13
የመጨረሻ ምክርና ሰላምታ
1እንግዲህ ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ ነው፤ መቼም ሁሉ ነገር የሚረጋገጠው በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች ነው። #ዘዳ. 17፥6፤ 19፥15። 2በሁለተኛው ጒብኝቴ ከእናንተ ጋር በነበርኩ ጊዜ በማስጠንቀቅ ተናግሬ ነበር፤ አሁንም ደግሞ በሩቅ ሆኜ ከዚህ ቀደም ኃጢአት ለሠሩትና ለሌሎችም በማስጠንቀቅ እናገራለሁ፤ አሁን ወደ እናንተ ተመልሼ በምመጣበት ጊዜ ለማንም አልራራም፤ 3እናንተ በእኔ ዐድሮ የሚናገረው ክርስቶስ መሆኑን ለማረጋገጥ ትፈልጋላችሁ፤ በእናንተ ዘንድ የሚታየውም የእርሱ ኀይል ነው እንጂ ድካሙ አይደለም። 4እርሱ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የሞተው በደካማነት ቢሆንም አሁን በእግዚአብሔር ኀይል በሕይወት ይኖራል፤ እኛም ከእርሱ ጋር ደካሞች ሆነናል፤ ከእናንተ ጋር ባለን ግንኙነት ግን ከእርሱ ጋር በእግዚአብሔር ኀይል እንኖራለን።
5በእምነታችሁ የጸናችሁ መሆናችሁን ለማረጋገጥ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችሁ መሆኑን አልተገነዘባችሁምን? አለበለዚያ በፈተና ወድቃችኋል ማለት ነው፤ 6እኛ በፈተና አለመውደቃችንን እንደምትገነዘቡ ተስፋ እናደርጋለን። 7ክፉ ነገር እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ የምንጸልየውም ምንም እንኳ እኛ ብቁዎች ሆነን ሳንታይ ብንቀር እናንተ ዘወትር መልካም የሆነውን ነገር እንድታደርጉ ነው እንጂ የእኛን ብቃት ለማሳየት አይደለም። 8እኛ ስለ እውነት እንሠራለን እንጂ የእውነት ተቃራኒ የሆነ ምንም ነገር አንሠራም። 9እኛ ደካሞች ሆነን እናንተ ግን ብርቱዎች ስትሆኑ ደስ ይለናል፤ የእኛ ጸሎት እናንተ ፍጹሞች እንድትሆኑ ነው። 10ይህን መልእክት ከእናንተ ርቄ ሳለሁ የጻፍኩላችሁ በዚሁ ምክንያት ነው፤ በዚህ ዐይነት ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ጌታም በሰጠኝ ሥልጣን አላስጨንቃችሁም፤ ጌታ ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ እናንተን ለማፍረስ አይደለም።
11በተረፈውስ ወንድሞቼ ሆይ! ደኅና ሁኑ! አኗኗራችሁን አስተካክሉ፤ ምክሬን ተከተሉ፤ እርስ በእርሳችሁ ተስማሙ፤ በሰላምም ኑሩ፤ የፍቅርና የሰላም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
12በተቀደሰ መሳሳም እየተሳሳማችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ፤
13ምእመናን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
14የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፥ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የመንፈስ ቅዱስ ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
Currently Selected:
2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997