2 ቆሮንቶስ 13:5-8
2 ቆሮንቶስ 13:5-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በእምነት መሆናችሁን ለማወቅ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ። ከፈር የወጣችሁ ካልሆነ በቀር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችሁ እንዳለ አታውቁምን? እኛ ግን ብቁ መሆናችንን እንደምትገነዘቡ ተስፋ አደርጋለሁ። አሁንም ምንም ክፉ ነገር እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ የምንጸልየውም እኛ ብቁዎች እንደ ሆንን ሰዎች እንዲያዩልን አይደለም፤ ነገር ግን እኛ ምንም እንኳ ብቁዎች ባንሆንም እናንተ መልካም የሆነውን ነገር እንድታደርጉ ነው። ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ማድረግ አንችልምና።
2 ቆሮንቶስ 13:5-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በሃይማኖት ጸንታችሁ እንደ ሆነ ራሳችሁን መርምሩ፤ እናንተ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናንተ ጋር እንዳለ አታውቁምን? እንዲህ ካልሆነ ግን እናንተ የተናቃችሁ ናችሁ። እኛም ብንሆን የተናቅን እንዳይደለን እንደምታውቁ እኔ አምናለሁ። ምንም ክፉ ሥራ እንዳትሠሩ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ መልካም ነገር እንድታደርጉ ብቻ ነው እንጂ እኛ ደጎች ልንባል አይደለም፤ እኛም እንደ ተናቁ ሰዎች እንሆናለን። ለዕውነት ጸንተን እንኖራለን እንጂ፤ ከዕውነት መውጣት አንችልምና።
2 ቆሮንቶስ 13:5-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በእምነት መሆናችሁን ለማወቅ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ። ከፈር የወጣችሁ ካልሆነ በቀር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችሁ እንዳለ አታውቁምን? እኛ ግን ብቁ መሆናችንን እንደምትገነዘቡ ተስፋ አደርጋለሁ። አሁንም ምንም ክፉ ነገር እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ የምንጸልየውም እኛ ብቁዎች እንደ ሆንን ሰዎች እንዲያዩልን አይደለም፤ ነገር ግን እኛ ምንም እንኳ ብቁዎች ባንሆንም እናንተ መልካም የሆነውን ነገር እንድታደርጉ ነው። ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ማድረግ አንችልምና።
2 ቆሮንቶስ 13:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን? እኛ ግን የማንበቃ እንዳይደለን ልታውቁ ተስፋ አደርጋለሁ። ክፉ ነገርንም ከቶ እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ እኛ የምንበቃ ሆነን እንገለጥ ዘንድ አይደለም ነገር ግን እኛ ምንም እንደማንበቃ ብንሆን፥ እናንተ መልካሙን ታደርጉ ዘንድ ነው። ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልምና።
2 ቆሮንቶስ 13:5-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በእምነታችሁ የጸናችሁ መሆናችሁን ለማረጋገጥ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችሁ መሆኑን አልተገነዘባችሁምን? አለበለዚያ በፈተና ወድቃችኋል ማለት ነው፤ እኛ በፈተና አለመውደቃችንን እንደምትገነዘቡ ተስፋ እናደርጋለን። ክፉ ነገር እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ የምንጸልየውም ምንም እንኳ እኛ ብቁዎች ሆነን ሳንታይ ብንቀር እናንተ ዘወትር መልካም የሆነውን ነገር እንድታደርጉ ነው እንጂ የእኛን ብቃት ለማሳየት አይደለም። እኛ ስለ እውነት እንሠራለን እንጂ የእውነት ተቃራኒ የሆነ ምንም ነገር አንሠራም።
2 ቆሮንቶስ 13:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
በእምነት እንደምትኖሩ ለማወቅ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ካልሆናችሁ በቀር፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ አታውቁም ኖሯል? እኛ ግን የማንበቃ እንዳልሆንን እንደምታውቁ ተስፋ አደርጋለሁ። ክፉ ነገርንም ከቶ እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ እኛ የበቃን ሆነን እንድንታይ አይደለም፤ ነገር ግን እኛ ምንም የማንበቃ እንኳን ብንሆን፥ እናንተ መልካሙን እንድታደርጉ ነው። ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልም።