ሁለተኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 7:1-3

ሁለተኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 7:1-3 አማ05

ንጉሥ ሰሎሞን ጸሎቱን እንደ ፈጸመ ወዲያውኑ እሳት ከሰማይ ወርዶ የሚቃጠለውንና ሌላውን መሥዋዕት በላ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ቤተ መቅደሱን ሞላው፤ ቤተ መቅደሱ በእግዚአብሔር ክብር ስለ ተሞላ ካህናቱ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መግባት አልቻሉም። እስራኤላውያን እሳት ከሰማይ ሲወርድና የእግዚአብሔርም ክብር በቤተ መቅደስ ላይ ማረፉን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው፦ “እግዚአብሔር ቸር ነው፤ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ነው!” እያሉ ሰገዱ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ።