ሁለተኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 7:1-3

ሁለተኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 7:1-3 አማ54

ሰሎሞንም ጸሎቱን በፈጸመ ጊዜ እሳት ከሰማይ ወርዶ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕቱን በላ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ቤቱን ሞላ። የእግዚአብሔርም ክብር የእግዚአብሔርን ቤት ሞልቶት ነበርና ካህናቱ ወደ እግዚአብሔር ቤት መግባት አልቻሉም። የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወርድ የእግዚአብሔርም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር፤ በወለሉም ላይ በግምባራቸው ወደ ምድር ተደፍተው ሰገዱ “እርሱ መልካም ነውና፥ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና” ብለውም እግዚአብሔርን አመሰገኑ።