የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 7

7
የይሳኮር ትውልድ
1ይሳኮር አራት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ቶላዕ፥ ፉዋ፥ ያሹብና ሺምሮን ተብለው የሚጠሩት ናቸው።
2ቶላዕ ስድስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ዑዚ፥ ረፋያ፥ ይሪኤል፥ ያሕማይ፥ ዩብሳምና ሸሙኤል ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ እነርሱም የቶላዕ ጐሣ ቤተሰቦች አለቆችና ዝነኛ ወታደሮች ነበሩ፤ በንጉሥ ዳዊት ዘመነ መንግሥት የእነርሱ ዘሮች ብዛት ኻያ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበር።
3ዑዚ፥ ዩዝራሕያ ተብሎ የሚጠራ አንድ ወንድ ልጅ ወለደ፤ ዩዝራሕያና የእርሱ አራት ወንዶች ልጆች ሚካኤል፥ አብድዩ፥ ዮኤልና ዩሺያ የቤተሰብ አለቆች ነበሩ። 4እነርሱ ብዙ ሚስቶችና ብዙ ልጆች ስለ ነበሩአቸው ዘሮቻቸው ለወታደራዊ አገልግሎት የደረሱ ሠላሳ ስድስት ሺህ ወንዶች ማቅረብ ይችሉ ነበር።
5ከይሳኮር ነገድ ቤተሰቦች ዕድሜአቸው ለወታደራዊ አገልግሎት የደረሰ ሰማኒያ ሰባት ሺህ ወንዶች መሆናቸው የትውልድ መዝገባቸው ያስረዳል።
የብንያምና የዳን ትውልድ
6ብንያም ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ቤላዕ፥ ቤኬርና ይዲዕኤል ተብለው የሚጠሩት ናቸው።
7ቤላዕ አምስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ኤጽቦን፥ ዑዚ፥ ዑዚኤል፥ ያሪሞትና ዒሪ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ እነርሱም በጐሣዎቻቸው ውስጥ የቤተሰብ አለቆችና ዝነኛ ወታደሮች ነበሩ፤ ከእነርሱ ተወላጆች መካከል ዕድሜአቸው ለውትድርና አገልግሎት የደረሰ ኻያ ሁለት ሺህ ሠላሳ አራት ወንዶች ነበሩ።
8ቤኬር ዘጠኝ ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ዘሚራ፥ ዮዓሽ፥ ኤሊዔዘር፥ ኤልዮዔናይ፥ ዖምሪ፥ ይሬሞት፥ አቢያ፥ ዐናቶትና ዓሌሜት ተብለው የሚጠሩ ናቸው። 9ከተወላጆቻቸው ቤተሰቦች ዕድሜአቸው ለውትድርና አገልግሎት የደረሰ ኻያ ሺህ ሁለት መቶ ወንዶች መሆናቸው መዝገቡ ያስረዳል።
10ይዲዕኤል፥ ቢልሃን ተብሎ የሚጠራ ወንድ ልጅ ወለደ፤ ቢልሃም ያዑሽ፥ ብንያም፥ ኤሁድ፥ ከናዕና፥ ዜታን፥ ታርሺሽና አሒሻሐር ተብለው የሚጠሩ ሰባት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ 11እነርሱም በጐሣቸው ውስጥ የቤተሰብ አለቆችና ዝነኛ ወታደሮች ነበሩ፤ የትውልዳቸው ቤተሰቦች ዕድሜአቸው ለውትድርና አገልግሎት የደረሰ ዐሥራ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ወንዶች ነበሩአቸው። 12ሹፊምና ሑፊምም የአሒር ልጆች ነበሩ፤ ሑሺምም የአሄር ልጅ ነበር።
የንፍታሌም ትውልድ
13ንፍታሌም አራት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ያሐጺኤል፥ ጉኒ፥ ዬጼርና ሻሉም ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ እነርሱም የቢልሃ ዘሮች ነበሩ።
የምናሴ ትውልድ
14ምናሴ ከሶርያዊት ቊባቱ አስሪኤልና ማኪር ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ማኪርም ገለዓድን ወለደ፤ 15ማኪር፥ ሑፊምና ሺፊም አንዳንድ ሴት እንዲያገቡ አደረገ፤ ማኪር ማዕካ ተብላ የምትጠራ እኅት ነበረችው፤ ጸሎፍሐድ ተብሎ የሚጠራው የማኪር ሁለተኛ ልጅ ሴቶች ልጆችን ብቻ ወለደ።
16የማኪር ሚስት ማዕካ ፔሬሽና ሼሬሽ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደች፤ ጴሬሽ የሚል ስም ያወጣችለትም እርስዋ ናት። 17ኡላም ደግሞ ባዳን ተብሎ የሚጠራ አንድ ልጅ ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የምናሴ የልጅ ልጅ የማኪር ልጅ የገለዓድ ዘሮች ናቸው።
18የገለዓድ እኅት ሃሞሌኬት ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደች፤ እነርሱም ኢሾድ፥ አቢዔዜርና ማሕላ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ 19የሸሚዳዕም ልጆች አሕያን፥ ሼኬም፥ ሊቅሒና አኒዓም ነበሩ።
የኤፍሬም ትውልድ
20ኤፍሬም ሹቴላሕን ወለደ፤ ሹቴላሕም ቤሬድን ወለደ፤ ቤሬድ ታሐትን ወለደ፤ ታሐት ኤልዓዳን ወለደ፤ ኤልዓዳ ታሐትን ወለደ፤ 21ታሐት ዛባድን ወለደ፤ ዛባድ ሹቴላሕን ወለደ፤ ኤፍሬም ከሹቴላሕ ሌላ ዔዜርና ኤልዓድ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም የጋት ነዋሪዎችን የቀንድ ከብቶች ሲሰርቁ ተይዘው ተገደሉ፤ 22አባታቸው ኤፍሬም ብዙ ቀን አዝኖላቸው ስለ ነበር ወንድሞቹ ሊያጽናኑት መጡ፤ 23ከዚህ በኋላ ኤፍሬም ከሚስቱ ጋር ግንኙነት አደረገ፤ እርስዋም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ በቤተሰባቸው ላይ በደረሰው መከራ ምክንያት በሪዓ የሚል ስም አወጣለት። #7፥23 በሪዓ፦ በዕብራይስጥ በመከራ ማለት ነው።
24ኤፍሬም፥ ሼኢራ ተብላ የምትጠራ ሴት ልጅ ወለደ፤ እርስዋም የላይኛውንና የታችኛውን ቤትሖሮን፥ እንዲሁም ዑዜንሼኢራ ተብለው የሚጠሩትን ከተማዎች አሠራች።
25ኤፍሬም፥ ሬፋሕ ተብሎ የሚጠራ ሌላ ወንድ ልጅ ወለደ፤ የሬፋሕም ዘሮች ሬሼፍ፥ ቴላሕ፥ ታሐን፥ 26ላዕዳን፥ ዓሚሁድ፥ ኤሊሻማዕ፥ 27ነዌና ኢያሱ ናቸው።
28የኤፍሬም ዘሮች በሙሉ ወስደው የራሳቸው መኖሪያ ያደረጉት ግዛት ቤትኤልና በዙሪያዋ የሚገኙትን ታናናሽ ከተሞችን ሲሆን፥ በምሥራቅ በኩል እስከ ናዕራን፥ በምዕራብ እስከ ጌዜር፥ እንዲሁም በጌዜር ዙሪያ የሚገኙትን ታናናሽ ከተሞችን ያጠቃልል ነበር፤ እንዲሁም ሴኬምንና ዓያን በዙሪያቸው የሚገኙትንም ታናናሽ ከተሞች ይጨምራል።
29የምናሴ ዘሮች ቤትሻንን፥ ታዕናክን፥ መጊዶንና ዶርን እንዲሁም በእነርሱ ዙሪያ የሚገኙትን ታናናሽ ከተሞች በቊጥጥራቸው ሥር አድርገው ነበር።
እነዚህ ሁሉ የያዕቆብ ልጅ የዮሴፍ ዘሮች ይኖሩባቸው የነበሩ ስፍራዎች ናቸው።
የአሴር ትውልድ
30አሴር አራት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ይምና፥ ይሽዋ፥ ይሽዊና በሪዓ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ እንዲሁም ሤራሕ ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት ልጅ ወለደ።
31በሪዓም ሔቤርና ማልኪኤል ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ማልኪኤል፥ ቢርዛዊ ተብሎ የሚጠራ ልጅ ወለደ።
32ሔቤር ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ያፍሌጥ፥ ሾሜርና ሖታም ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ እንዲሁም ሹዓ ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት ልጅ ወለደ።
33ያፍሌጥም ፓሳክ፥ ቢምሃልና ዓሽዋት ተብለው የሚጠሩ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ።
34የያፍሌት ወንድም የሾሜርም አሒ፥ ሮህጋ፥ የሑባና አራም ተብለው የሚጠሩ ልጆችን ወለደ።
35የያፍሌጥ ወንድም ሖታምም ጾፋሕ፥ ዩምናዕ፥ ሼሌሽና ዓማል ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ።
36የጾፋሕ ዘሮች ሱሐ፥ ሐርኔፌር፥ ሹዓል፥ ቤሪ፥ ዩምራ፥ 37ቤጼር፥ ሆድ፥ ሻማ፥ ሺልሻ፥ ዩትራንና በኤራ ተብለው የሚጠሩት ናቸው።
38የዬቴር ዘሮች ይፉኔ፥ ፒስፓና አራ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ 39የዑላ ዘሮች አራሕ፥ ሐኒኤልና ሪጽያ ተብለው የሚጠሩት ናቸው።
40እነዚህ ሁሉ የአሴር ዘሮች ናቸው፤ እነርሱም የቤተሰብ አለቆች፥ ዝነኛ ጦረኞችና ምርጥ የሆኑ መሪዎች ነበሩ፤ የአሴር ዘሮች ለውትድርና አገልግሎት ብቁ የሆኑ ኻያ ስድስት ሺህ ወንዶች ነበሩአቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ