አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 8
8
የብንያም ትውልድ
1ብንያም አምስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም በየዕድሜአቸው ተራ፥ ቤላዕ፥ አሽቤል፥ አሕራሕ፥ 2ኖሐና ራፋ ተብለው የሚጠሩት ናቸው።
3የቤላዕ ዘሮች አዳር፥ ጌራ፥ አቢሁ፥ 4አቢሹዓ፥ ናዕማን፥ አሖሐ፥ 5ጌራ፥ ሸፉፋንና ሑራም ተብለው የሚጠሩት ናቸው።
6-7የኤሁድ ዘሮች ናዕማን፥ አሒያና ጌራ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ እነርሱም በጌባዕ ይኖሩ ለነበሩት በኋላ ግን ከዚያ ተባረው ወደ ማናሐት ሄደው በዚያ ለኖሩ ቤተሰቦች አለቆች ነበሩ፤ ወደዚያም የመራቸው የዑዛና የአሒሑድ አባት ጌራ ነበር።
8-9ሻሐራም፥ ሑሺምና ባዕራ ተብለው የሚጠሩትን ሁለት ሚስቶቹን ፈታ፤ ዘግየት ብሎም በሞአብ አገር ሲኖር ሖዴሽ ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት አግብቶ ሰባት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ዮባብ፥ ጺብያ፥ ሜሻ፥ ማልካም፥ 10የዑጽ፥ ሳክያና ሚርማ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ የእርሱ ወንዶች ልጆች በሙሉ የቤተሰብ አለቆች ሆኑ።
11በተጨማሪም ሑሺም ከተባለችው ሚስቱ አሂቱብና ኤልፓዓል ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ።
12ኤልፓዓልም ዔቤር፥ ሚሸዓምና ሼሜድ ተብለው የሚጠሩ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ሼሜድም ኦኖና ሎድ ተብለው የሚጠሩትን ከተሞችና በዙሪያቸው የሚገኙትን መንደሮች የሠራ ነው።
በጋትና በአያሎን ይኖሩ የነበሩ ብንያማውያን
13በሪዓና ሴማዕ በአያሎን ከተማ ለሰፈሩት ቤተሰቦች አለቆች ነበሩ፤ እነርሱም በጋት ከተማ የሚኖረውን ሕዝብ አባረሩ፤ 14የበሪዓ ዘሮች አሕዮ፥ ሻሻቅ፥ ይሬሞት፥ 15ዘባድያ፥ ዐራድ፥ ዔዴር፥ 16ሚካኤል፥ ዩሽፓና ዮሐ ተብለው የሚጠሩት ናቸው።
በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ ብንያማውያን
17የኤልፓዓል ልጆች ዘባድያ፥ መሹላም፥ ሒዝቂ፥ ሔቤር፥ 18ዩሽመራይ፥ ዩዝሊአና ዮባብ ተብለው የሚጠሩት ናቸው።
19የሺምዒ ልጆች ያቂም፥ ዚክሪ፥ ዛብዲ፥ 20ኤሊዔናይ፥ ጺልታይ፥ ኤሊኤል፥ 21ዐዳያ፥ በራያና ሺምራት ተብለው የሚጠሩት ናቸው።
22የሻሻቅ ልጆች ኢሽጳን፥ ዔቤር፥ ኤሊኤል፥ 23ዓብዶን፥ ዚክሪ፥ ሐናን፥ 24ሐናንያ፥ ዔላም፥ ዓንቶቲያ፥ 25ዩፍደያና ፋኑኤል ተብለው የሚጠሩ ናቸው።
26የይሮሐም ልጆች ሻምሸራይ፥ ሸሐርያ፥ ዐታልያ፥ 27ያዕሬሽያ፥ ኤሊያና ዚክሪ ተብለው የሚጠሩት ናቸው።
28እነዚህ ሁሉ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ለነበሩት ቀደም ያሉ የቤተሰብ አለቆችና የእነርሱም ዋና ዋና ዘሮች ናቸው።
በገባዖንና በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ ብንያማውያን
29ይዒኤል የገባዖንን ከተማ ቈርቊሮ በዚያው ኖረ፤ ሚስቱ ማዕካ ተብላ የምትጠራ ስትሆን፥ 30የበኲር ልጁም ዓብዶን ይባል ነበር፤ ሌሎቹ የእርሱ ወንዶች ልጆች ጹር፥ ቂሽ፥ ባዓል፥ ኔር፥ ናዳብ፥ 31ገዶር፥ አሕዮ፥ ዜኬርና፥ 32የሺምዓ አባት ሚቅሎት ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ የእነርሱም ዘሮች በሌሎቹ የጐሣቸው ቤተሰቦች አቅራቢያ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር።
የንጉሥ ሳኦል ቤተሰብ
33ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስ ንጉሥ ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታን፥ ማልኪሹዓ፥ አቢናዳብና ኤሽባዓል ተብለው የሚጠሩትን አራት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ 34ዮናታንም መሪባዓልን ወለደ፤ መሪባዓልም ሚካን ወለደ።
35ሚካም ፒቶን፥ ሜሌክ፥ ታሬዓና አሐዝ ተብለው የሚጠሩትን ወንዶች ልጆች ወለደ። #8፥35 መሪባዓል፦ በ 2ኛ ሳሙኤል 4፥4 መፊቦሼት ተብሏል። 36አሐዝ የሆዓዳን ወለደ፤ የሆዓዳም ዓሌሜት፥ ዓዝማዌትና ዚምሪ ተብለው የሚጠሩትን ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ዚምሪም ሞጻን ወለደ፤ 37ሞጻም ቢንዓን ወለደ፤ ቢንዓ ራፋን ወለደ፤ ራፋ ኤልዓሳን ወለደ፤ ኤልዓሳም አጼልን ወለደ።
38አጼልም ዓዝሪቃም፥ ቦከሩ፥ እስማኤል፥ ሸዓርያ፥ አብድዩና ሐናን ተብለው የሚጠሩትን ስድስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ 39የአጼል ወንድም ዔሼቅም በኲሩ ኡላም፥ ሁለተኛው ያዑሽና ሦስተኛ ኤሊፌሌጥ ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ።
40የኡላም ወንዶች ልጆች ዝነኛ ወታደሮችና ቀስት ወርዋሪዎች ነበሩ፤ የእነርሱም ዘሮች በአጠቃላይ አንድ መቶ ኀምሳ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩ፤ እንግዲህ ከዚህ በላይ ስሞቻቸው የተጠቀሱት ሁሉ የብንያም ነገድ ነበሩ።
Currently Selected:
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 8: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997