“ደቀ መዝሙር ከመምህሩ፣ ባሪያም ከጌታው አይበልጥም፤ ደቀ መዝሙር መምህሩን፣ ባሪያም ጌታውን ከመሰለ ይበቃዋል። ባለቤቱን ‘ብዔልዜቡል’ ካሉት፣ ቤተ ሰዎቹንማ እንዴት አብልጠው አይሏቸውም! “ስለዚህ አትፍሯቸው፤ የተሸፈነ መገለጡ፣ የተደበቀ መውጣቱ አይቀርምና። በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን አውሩት፤ በጆሯችሁ የሰማችሁትን በአደባባይ ዐውጁት፤ ሥጋን መግደል እንጂ ነፍስን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤ ይልቁንስ ነፍስንና ሥጋን በገሃነም ማጥፋት የሚቻለውን ፍሩ። በአንድ ሳንቲም ከሚሸጡት ሁለት ድንቢጦች አንዲቷ እንኳ ያለ አባታችሁ ፈቃድ ምድር ላይ አትወድቅም። የራስ ጠጕራችሁ እንኳ አንድ ሳይቀር የተቈጠረ ነው። ስለዚህ አትፍሩ፤ ከብዙ ድንቢጦች የበለጠ ዋጋ አላችሁ። “በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ፣ እኔም በሰማይ ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ ነገር ግን በሰው ፊት የሚክደኝን፣ እኔም በሰማይ ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ። “እኔ የመጣሁት ሰላምን በምድር ለማስፈን አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማውረድ አልመጣሁም። እኔ የመጣሁት “ ‘ልጅን ከአባት፣ ሴት ልጅን ከእናቷ ምራትንም ከዐማቷ ለመለያየት ነው፤ የሰው ጠላቶቹ፣ የገዛ ቤተ ሰዎቹ ይሆናሉ።’ “ከእኔ ይልቅ እናቱን ወይም አባቱን የሚወድድ ለእኔ ሊሆን አይገባም፤ ከእኔ ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድድ ለእኔ ሊሆን አይገባም። መስቀሉን ተሸክሞ የማይከተለኝ የእኔ ሊሆን አይገባውም። ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፤ ነፍሱን ስለ እኔ የሚያጠፋት ግን ያገኛታል። “እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል፤ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቅን ዋጋ ያገኛል። ስለዚህ እውነት እላችኋለሁ፣ ማንም ሰው ከእነዚህ ከታናናሾች ለአንዱ ደቀ መዝሙሬ በመሆኑ አንድ ጽዋ ቀዝቃዛ ውሃ ቢሰጠው ዋጋውን አያጣም።”
ማቴዎስ 10 ያንብቡ
ያዳምጡ ማቴዎስ 10
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ማቴዎስ 10:24-42
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos