1
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 18:37
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አንተ፥ አቤቱ፥ አምላክ እንደ ሆንህ፥ ልባቸውንም ደግሞ እንደ መለስህ፤ ይህ ሕዝብ ያውቅ ዘንድ ስማኝ፤ አቤቱ፥ ስማኝ” አለ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 18:36
ነቢዩ ኤልያስም ወደ ሰማይ አቅንቶ ጮኸ፤ እንዲህም አለ፥ “አቤቱ፥ የአብርሃምና የይስሐቅ የእስራኤልም አምላክ ሆይ፥ ስማኝ፤ ጌታዬ ሆይ፥ ዛሬ በእሳት ስማኝ፤ አንተ በእስራኤል ላይ አምላክ እንደ ሆንህ፥ እኔም ባሪያህ እንደ ሆንሁ፤ ይህንም ሥራ ስለ አንተ እንዳደረግሁ እነዚህ ሕዝቦች ይወቁ።
3
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 18:21
ኤልያስም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ፥ “እስከ መቼ በሁለት አሳብ ታነክሳላችሁ? እግዚአብሔር አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ፤ በዓልም አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ” አለ። ሕዝቡም አንዲት ቃል አልመለሱለትም።
4
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 18:38
እሳትም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወረደች፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ እንጨቱንም፥ ድንጋዮቹንም በላች፤ በጕድጓዱም ውስጥ ያለውን ውኃ፥ አፈሩንም ላሰች።
5
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 18:39
ሕዝቡም ሁሉ ያን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው ተደፍተው፥ “እግዚአብሔር በእውነት እርሱ አምላክ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው” አሉ።
6
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 18:44
በሰባተኛውም ጊዜ፥ “እነሆ፥ የሰው ጫማ የምታህል ትንሽ ደመና ከባሕር ውኃ ቋጥራ ስትወጣ አየሁ” አለ። እርሱም፥ “ወጥተህ አክዓብን፦ ዝናብ እንዳይዝህ ሰረገላህን ጭነህ ውረድ በለው” አለ።
7
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 18:46
የእግዚአብሔርም እጅ በኤልያስ ላይ ነበረች፤ ወገቡንም ታጥቆ ወደ ኢይዝራኤል እስኪገባ ድረስ በአክዓብ ፊት ይሮጥ ነበር።
8
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 18:41
ኤልያስም አክዓብን፥ “የዝናቡ ውሽንፍር እጅግ ነውና ተነሥተህ ውጣ፤ ብላም፤ ጠጣም” አለው።
9
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 18:43
ብላቴናውንም፥ “ወጥተህ ወደ ባሕሩ ተመልከት” አለው። ብላቴናውም ተመልክቶ፥ “ምንም የለም” አለ። ኤልያስም፥ “ሰባት ጊዜ ተመላለስ” አለው። ብላቴናውም ሰባት ጊዜ ተመላለሰ።
10
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 18:30
ኤልያስም ሕዝቡን ሁሉ፥ “ወደ እኔ ቅረቡ” አላቸው። ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ ቀረቡ።
11
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 18:24
እናንተም የአምላካችሁን ስም ጥሩ፤ እኔም የፈጣሪዬን የእግዚአብሔርን ስም እጠራለሁ፤ ሰምቶም በእሳት የሚመልስ አምላክ፥ እርሱ አምላክ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፥ “ይህ ነገር መልካም ነው” ብለው መለሱ።
12
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 18:31
ኤልያስም፦ ስምህ እስራኤል ይሆናል የሚል የእግዚአብሔር ቃል እንደ ደረሰለት እንደ እስራኤል ልጆች ነገድ ቍጥር ዐሥራ ሁለት ድንጋዮችን ወሰደ።
13
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 18:27
በቀትርም ጊዜ ቴስብያዊው ኤልያስ፥ “አምላክ ነውና በታላቅ ቃል ጩኹ፤ ምናልባት ይጫወት ይሆናል፥ ወይም አሳብ ይዞት ይሆናል፥ ወይም ተኝቶ እንደ ሆነ መቀስቀስ ያስፈልገዋል” እያለ ይዘባበትባቸው ጀመር።
14
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 18:32
ድንጋዮችንም በእግዚአብሔር ስም መሠዊያ አድርጎ ሠራቸው፤ የፈረሰውንም መሠዊያ አደሰ፤ በመሠዊያውም ዙሪያ ሁለት መስፈሪያ እህል የሚይዝ ጕድጓድ ቈፈረ።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች