1
ትንቢተ ኤርምያስ 7:22-23
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ከግብጽ ምድር ባወጣኋችሁ ቀን ስለሚቃጠል መሥዋዕትና ስለ ሌላ መሥዋዕት ለአባቶቻችሁ አልተናገርሁምና፥ አላዘዝኋቸውምም። ነገር ግን፦ “ድምፄን ስሙ፥ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤ መልካምም እንዲሆንላችሁ ባዘዝኋችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ” ብዬ በዚህ ነገር አዘዝኋቸው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ኤርምያስ 7:24
ነገር ግን በክፉ ልባቸው ሐሳብና እልከኝነት ሄዱ ወደፊትም ሳይሆን ወደ ኋላቸው ሄዱ እንጂ አልሰሙም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም።
3
ትንቢተ ኤርምያስ 7:5-7
መንገዳችሁንና ሥራችሁን ፈጽማችሁ ብታሳምሩ፥ በሰውና በጎረቤቱ መካከል ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፥ መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም ባትጨቊኑ፥ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን ባታፈስሱ፥ ክፉም እንዳይሆንባችሁ እንግዶችን አማልክት ባትከተሉ፥ ከጥንት ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለአባቶቻችሁ በሰጠኋቸው ምድር፥ በዚህ ስፍራ እንድትቀመጡ አደርጋችኋለሁ።
4
ትንቢተ ኤርምያስ 7:3
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ መንገዳችሁንና ሥራችሁን አሳምሩ በዚህም ስፍራ እንድትቀመጡ አደርጋችኋለሁ።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች