1
2ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 20:15
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
እንዲህም አለ፦ “ይሁዳ ሁሉ፥ በኢየሩሳሌም የምትኖሩ፥ አንተም ንጉሡ ኢዮሣፍጥ፥ ስሙ፤ ጌታ እንዲህ ይላችኋል፦ ‘ውግያው የጌታ ነው እንጂ የእናንተ አይደለምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተነሣ አትፍሩ፥ አትደንግጡም።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
2ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 20:17
እናንተ በዚህ ውግያ ላይ የምትዋጉ አይደላችሁም፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ! ተሰለፉ፥ ጸንታችሁም ቁሙ፥ የሚሆነውንም የጌታን ድል አድራጊነት እዩ፤’ ጌታም ከእናንተ ጋር ነውና አትፍሩ፥ አትደንግጡም፥ ነገም በእነርሱ ላይ ውጡ።”
3
2ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 20:12
አምላካችን ሆይ! አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን ልንቋቋመው አንችልም፤ ዐይኖቻችን ወደ አንተ ከማንሣት በቀር የምናደርገውን ነገር አናውቅም።”
4
2ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 20:21
ከሕዝቡም ጋር ተማክሮ በሠራዊቱ ፊት የሚሄዱትን፦ “ጽኑ ፍቅሩ ለዘዓለም ነውና ጌታን አመስግኑ” የሚሉትንም ጌጠኛ ልብስም ለብሰው የሚያመሰግኑትን፥ ለጌታም የሚዘምሩትን መዘምራን አቆመ።
5
2ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 20:22
ዝማሬውንና ምስጋናውንም በጀመሩ ጊዜ ይሁዳን ሊወጉ በመጡ በአሞንና በሙዓብ ልጆች በሴይርም ተራራ ሰዎች ላይ ጌታ ድብቅ ጦርን አመጣባቸው፤ እነርሱም ተሸነፉ።
6
2ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 20:3
ኢዮሣፍጥም ፈራ፥ ጌታንም ሊፈልግ ፊቱን አቀና፤ በይሁዳም ሁሉ ጾም አወጀ።
7
2ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 20:9
‘ክፉ ነገር፥ ሰይፍ ወይም ፍርድ ወይም ቸነፈር ወይም ራብ፥ ቢመጣብን ስምህ ባለበት በዚህ ቤት ፊትና በፊትህ ቆመን በመከራችን ወደ አንተ እንጮሃለን፥ አንተም ሰምተህ ታድነናለህ።’
8
2ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 20:16
ነገ በእነርሱ ላይ ውረዱ፤ እነሆ፥ በጺጽ አቀበት ይወጣሉ፤ በሸለቆውም መጨረሻ በይሩኤል ምድረ በዳ ፊት ለፊት ታገኙአቸዋላችሁ።
9
2ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 20:4
ይሁዳም ጌታን ይፈልግ ዘንድ ተሰበሰበ፤ ከይሁዳ ከተሞች ሁሉ ጌታን ለመሻት መጡ።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች