1
መጽሐፈ መዝሙር 91:2
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እግዚአብሔርን “አንተ መከታዬና መጠጊያዬ ነህ፤ አንተ የምተማመንብህ አምላኬ ነህ” ይለዋል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ መዝሙር 91:1
መጠለያ በመፈለግ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ፥ ሁሉን የሚችለውን አምላክ መጠጊያ የሚያደርግ፥
3
መጽሐፈ መዝሙር 91:15
በሚጠራኝም ጊዜ እሰማዋለሁ፤ በመከራው ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁም።
4
መጽሐፈ መዝሙር 91:11
ይህም የሚሆነው በምትሄድበት ሁሉ እንዲጠብቁህ እግዚአብሔር መላእክቱን ስለሚያዛቸው ነው።
5
መጽሐፈ መዝሙር 91:4
በጥበቃው ሥር ያደርግሃል። እርሱ ስለሚንከባከብህ በሰላም ትኖራለህ፤ የእርሱ ታማኝነት እንደ ጋሻ ወይም እንደ ከተማ ቅጽር ይሆንልሃል።
6
መጽሐፈ መዝሙር 91:9-10
አንተ እግዚአብሔርን መከታህ፥ ልዑል አምላክንም ጠባቂህ አድርገሃል። ስለዚህ ብርቱ አደጋ አይደርስብህም፤ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይጠጋም።
7
መጽሐፈ መዝሙር 91:3
እግዚአብሔር ከተሰወሩ ወጥመዶችና ለሞት ከሚያደርሱ በሽታዎች ይጠብቅሃል።
8
መጽሐፈ መዝሙር 91:7
አንድ ሺህ በአጠገብህ፥ ዐሥር ሺህ በስተቀኝህ ይወድቃሉ፤ አንተ ግን ከቶ አትጐዳም።
9
መጽሐፈ መዝሙር 91:5-6
“በሌሊት ሽብር ይደርስብኛል፤ በቀን ፍላጻ ይወረወርብኛል” ብለህ አትፈራም። በጨለማ ከሚመጣ ተላላፊ በሽታና በቀትር ከሚወርድ መቅሠፍት አትሰጋም።
Home
Bible
Plans
Videos