ኦሪት ዘፍጥረት 7
7
ማየ አይኅ
1እግዚአብሔር አምላክም ኖኅን አለው፥ “አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ፤ በዚህ ትውልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይችሃለሁና። 2ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ ሰባት ስባት ተባትና እንስት፥ ንጹሕ ካልሆነም እንስሳ ሁለት ሁለት ተባትና እንስት፤ 3ከንጹሕ የሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት፥ ንጹሕ ካልሆነ የሰማይ ወፍም ሁለት ሁለት ተባትና እንስት እያደረግህ በምድር ላይ ለምግብና ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትወስዳለህ። 4ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁና፤ የፈጠርሁትንም ፍጥረት ሁሉ ከምድር ሁሉ ላይ አጠፋለሁና።” 5ኖኅም እግዚአብሔር አምላክ ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። 6ኖኅም የጥፋት ውኃ በምድር ላይ በሆነ ጊዜ የስድስት መቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ።
7ኖኅም ስለ ጥፋት ውኃ ልጆቹንና ሚስቱን፥ የልጆቹንም ሚስቶች ይዞ ወደ መርከብ ገባ። 8ከንጹሓን ወፎችና ንጹሓን ካልሆኑ ወፎች፥ ከንጹሕ እንስሳ፥ ንጹሕም ካልሆነው እንስሳ፥ በምድር ላይ ከሚንቀሳቀሰው ሁሉ፥ 9እግዚአብሔር ኖኅን እንዳዘዘው፥ ሁለት ሁለት ተባትና እንስት እየሆኑ ወደ ኖኅ ወደ መርከብ ውስጥ ገቡ። 10ከሰባት ቀን በኋላም የጥፋት ውኃ በምድር ላይ ሆነ። 11በኖኅ ዕድሜ በስድስተኛው መቶ ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በዐሥራ ሰባተኛው ዕለት፥#ግዕዙ “አመ 10ወ2 ለጽልመት” ግሪክ ሰባ. ሊ. “በሃያ ሰባተኛው ዕለት” ይላል። በዚያው ቀን የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፤ የሰማይ መስኮቶችም ተከፈቱ፤ 12ዝናቡም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ሆነ።
13በዚያውም ቀን ኖኅ ወደ መርከብ ገባ፤ የኖኅ ልጆችም ሴም፥ ካም፥ ያፌትና የኖኅ ሚስት፥ ሦስቱም የልጆቹ ሚስቶች ከእርሱ ጋር ገቡ። 14አራዊትም ሁሉ በየወገናቸው፥ እንስሳትም ሁሉ በየወገናቸው፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾችም ሁሉ በየወገናቸው፥ ወፎችም ሁሉ በየወገናቸው፥ የሚበሩ ወፎችም ሁሉ፥ 15ሥጋ ያላቸው ሕያዋን ሁሉ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ ኖኅ መርከብ ውስጥ ገቡ። 16ሥጋ ካለው ሁሉ የገቡትም ተባትና እንስት እግዚአብሔር ኖኅን እንዳዘዘው ገቡ፤ እግዚአብሔር አምላክም መርከብዋን በስተውጭ ዘጋት። 17የጥፋት ውኃ በምድር ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ነበረ፤ ውኃውም በዛ፤ መርከቢቱንም አነሣ፤ ከምድርም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለች። 18ውኃውም አሸነፈ፤ በምድር ላይም እጅግ በዛ፤ መርከቢቱም በውኃ ላይ ተንሳፈፈች። 19ውኃውም በምድር ላይ እጅግ በጣም አሸነፈ፤ ከሰማይ በታች ያሉ ረዣዥም ተራሮችን ሁሉ ሸፈነ። 20ውኃው ወደ ላይ ዐሥራ አምስት ክንድ ከፍ ከፍ አለ፤ ረዣዥም ተራሮችንም ሸፈነ። 21በምድር ላይ ሥጋ ያለው የሚንቀሳቀሰው ሁሉ ወፉም፥ እንስሳውም፥ አራዊቱም፥ በምድር ላይ የሚርመሰመሰው ተንቀሳቃሹምሁሉ፥ ሰውም ሁሉ ጠፋ። 22የሕይወት እስትንፋስ ያለው ሁሉ፥ በየብስም ያለው ሁሉ ሞተ። 23በምድር ላይ የነበረውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ፥ እስከሚርመሰመሰውም ሁሉ ድረስ፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ ተደመሰሰ፤ ከምድርም ተደመሰሱ። ኖኅም አብረውት በመርከብ ከነበሩት ጋር ብቻውን ቀረ። 24ውኃውም መቶ አምሳ ቀን በምድር ላይ ሞላ።
Atualmente Selecionado:
ኦሪት ዘፍጥረት 7: አማ2000
Destaque
Compartilhar
Copiar
Quer salvar seus destaques em todos os seus dispositivos? Cadastre-se ou faça o login