1
የሉቃስ ወንጌል 14:26
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
“ወደ እኔ የሚመጣ፥ ሊከተለኝም የሚወድ አባቱንና እናቱን፥ ሚስቱንና ልጆቹን፥ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፥ የራሱንም ሰውነት እንኳ ቢሆን የማይጠላ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
Compare
የሉቃስ ወንጌል 14:26ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
2
የሉቃስ ወንጌል 14:27
መስቀሉን ተሸክሞ ሊከተለኝ የማይመጣ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።”
የሉቃስ ወንጌል 14:27ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
3
የሉቃስ ወንጌል 14:11
ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፤ ራሱንም ያሚያዋርድ ከፍ ይላልና።”
የሉቃስ ወንጌል 14:11ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
4
የሉቃስ ወንጌል 14:33
እንግዲህ እንደዚሁ ከእናንተ ወገን ከሁሉ ያልወጣ፥ የእርሱ ገንዘብ ከሆነውም ሁሉ ያልተለየ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
የሉቃስ ወንጌል 14:33ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
5
የሉቃስ ወንጌል 14:28-30
“ከእናንተም ወገን የግንብ ቤት መሥራት የሚወድ ቢኖር ይጨርሰው ዘንድ የሚችል እንደ ሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ የሚፈጅበትን የማያስብ ማን ነው? መሠረቱን ጥሎ መጨረስ ያቃተውም እንደ ሆነ ያዩት ሁሉ፥ ‘ይህ ሰው ሊሠራ ጀመረ፤ ግን መጨረስ ተሳነው’ እያሉ ሊዘብቱበት ይጀምራሉ።
የሉቃስ ወንጌል 14:28-30ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
6
የሉቃስ ወንጌል 14:13-14
ነገር ግን በበዓል ምሳ በምታደርግበት ጊዜ ድሆችንና ጦም አዳሪዎችን፥ ዕውሮችን፥ እጅና እግርም የሌላቸውን ጥራ። አንተም ብፁዕ ትሆናለህ፤ የሚከፍሉህ የላቸውምና፤ ነገር ግን ጻድቃን በሚነሡበት ጊዜ ዋጋህን ታገኛለህ።”
የሉቃስ ወንጌል 14:13-14ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
7
የሉቃስ ወንጌል 14:34-35
“ጨው መልካም ነው፤ ጨው አልጫ ከሆነ እንግዲህ በምን ያጣፍጡታል? ለምድርም ቢሆን፥ ለፍግ መቆለያም ቢሆን አይረባም፤ ነገር ግን ወደ ውጭ ይጥሉታል፤ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”
የሉቃስ ወንጌል 14:34-35ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
Home
ਬਾਈਬਲ
Plans
ਵੀਡੀਓ