1
የሉቃስ ወንጌል 14:26
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
“ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ አባቱንና እናቱን፥ ሚስቱንና ልጆቹን፥ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፥ የራሱንም ሕይወት እንኳ ከእኔ አብልጦ የሚወድ ከሆነ የእኔ ደቀ መዝሙር ሊሆን አይችልም።
နှိုင်းယှဉ်
የሉቃስ ወንጌል 14:26ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
2
የሉቃስ ወንጌል 14:27
የራሱን መስቀል ተሸክሞ የማይከተለኝ፥ የእኔ ደቀ መዝሙር ሊሆን አይችልም።
የሉቃስ ወንጌል 14:27ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
3
የሉቃስ ወንጌል 14:11
ራሱን ከፍ የሚያደርግ ይዋረዳል፤ ራሱን የሚያዋርድ ግን ከፍ ይላል።”
የሉቃስ ወንጌል 14:11ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
4
የሉቃስ ወንጌል 14:33
እንዲሁም ከእናንተ መካከል ያለውን ሁሉ ለእኔ ሲል ያልተወ ማንም ሰው የእኔ ደቀ መዝሙር መሆን አይችልም።”
የሉቃስ ወንጌል 14:33ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
5
የሉቃስ ወንጌል 14:28-30
“ከእናንተ መካከል አንዱ ሕንጻ መሥራት ቢፈልግ ለሥራው ማስፈጸሚያ ምን ያኽል ገንዘብ እንደሚያስፈልገው አስቀድሞ የማያስብ ማነው? መሠረቱን ጥሎ የሕንጻውን ሥራ መፈጸም ያልቻለ እንደ ሆነ ግን በጅምር የቀረውን ቤት የሚያዩት ሁሉ ይዘባበቱበታል፤ ‘እነሆ፥ ይህ ሰው ቤት መሥራት ጀምሮ መጨረስ አልቻለም’ እያሉ ያፌዙበታል።
የሉቃስ ወንጌል 14:28-30ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
6
የሉቃስ ወንጌል 14:13-14
ነገር ግን ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ድኾችን፥ አካለ ስንኩሎችን፥ ሽባዎችን፥ ዕውሮችንም ሰዎች ጥራ። ይህን ብታደርግ እነርሱ ውለታ ለመክፈል ስለማይችሉ የተባረክህ ትሆናለህ። በጻድቃን ትንሣኤ ጊዜም እግዚአብሔር ይከፍልሃል።”
የሉቃስ ወንጌል 14:13-14ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
7
የሉቃስ ወንጌል 14:34-35
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ጨው መልካም ነው፤ ጨው የጨውነቱን ጣዕም ካጣ ግን በምን ሊጣፍጥ ይችላል? እንዲህ ዐይነቱ ጨው ለእርሻ መሬትም ሆነ ለማዳበሪያ የማይጠቅም ስለ ሆነ ወዲያ አውጥተው ይጥሉታል፤ ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ!”
የሉቃስ ወንጌል 14:34-35ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
ပင်မစာမျက်နှာ
ကျမ်းစာ
အစီအစဉ်
ဗီဒီယို