ኦሪት ዘፍጥረት 6:1-4

ኦሪት ዘፍጥረት 6:1-4 አማ54

እንዲህም ሆነ ሰዎች በምድር ላይ መብዛት በጀመሩ ጊዜ ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደ ሆኑ አዩ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ። እግዚአብሔርም፤ መንፈሴ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም፤ እርሱ ሥጋ ነውና፤ ዘመኖቹም መቶ ሀያ ዓመት ይሆናሉ አለ። በእነዚያ ወራት ኔፊሊም በምድር ላይ ነበሩ ደግሞም ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች ባገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው እነርሱም በዱሮ ዘመን ስማቸው የታወቀ ኂያላን ሆኑ።