1
ዘፍጥረት 17:1
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
አብራም ዕድሜው 99 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤ ነቀፋም አይኑርብህ፤
비교
ዘፍጥረት 17:1 살펴보기
2
ዘፍጥረት 17:5
ከእንግዲህ ወዲያ ስምህ አብራም መባሉ ቀርቶ አብርሃም ይሆናል፤ የብዙ ሕዝቦች አባት አድርጌሃለሁና።
ዘፍጥረት 17:5 살펴보기
3
ዘፍጥረት 17:7
በእኔና በአንተ፣ ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋራ ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ በዚህም የአንተና ከአንተም በኋላ የዘርህ አምላክ እሆናለሁ።
ዘፍጥረት 17:7 살펴보기
4
ዘፍጥረት 17:4
“እነሆ፤ የምገባልህ ኪዳን ይህ ነው፤ የብዙ ሕዝቦች አባት ትሆናለህ።
ዘፍጥረት 17:4 살펴보기
5
ዘፍጥረት 17:19
እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ይሁን ዕሺ፤ ነገር ግን ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይሥሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፤ እኔም ከርሱ በኋላ ለዘሩ ሁሉ የሚሆን የዘላለም ኪዳን ከርሱ ጋራ እገባለሁ።
ዘፍጥረት 17:19 살펴보기
6
ዘፍጥረት 17:8
ይህችን አሁን በእንግድነት የምትኖርባትን የከነዓንን ምድር በሙሉ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ ለዘላለም ርስት አድርጌ እሰጣቸዋለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ።”
ዘፍጥረት 17:8 살펴보기
7
ዘፍጥረት 17:17
አብርሃምም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ ሣቀና በልቡ፣ “እንዲያው ምንስ ቢሆን የመቶ ዓመት ሽማግሌ የልጅ አባት መሆን ይችላልን? ሣራስ በዘጠና ዓመቷ ልጅ መውለድ ትችላለችን?” አለ።
ዘፍጥረት 17:17 살펴보기
8
ዘፍጥረት 17:15
እግዚአብሔር አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “ሦራን ከእንግዲህ ሦራ ብለህ አትጠራትም፤ ስሟ ከዛሬ ጀምሮ ሣራ ይሁን።
ዘፍጥረት 17:15 살펴보기
9
ዘፍጥረት 17:11
ስለዚህ ሁላችሁም ሸለፈታችሁን ትገረዛላችሁ፤ ይህም በእኔና በእናንተ መካከል ላለው ኪዳን ምልክት ይሆናል።
ዘፍጥረት 17:11 살펴보기
10
ዘፍጥረት 17:21
ኪዳኔን ግን የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ልጅ፣ ከይሥሐቅ ጋራ አደርጋለሁ።”
ዘፍጥረት 17:21 살펴보기
11
ዘፍጥረት 17:12-13
የሚመጣውም ትውልድ ሁሉ፣ ማንኛውም ወንድ ልጅ፣ ስምንት ቀን ሲሞላው ይገረዝ፤ እንደዚሁም በቤትህ የተወለደውና ከውጭ በገንዘብ የተገዛ ባዕድ ሁሉ ይገረዝ። በቤትህ የተወለደም ሆነ በገንዘብህ የተገዛ ሁሉ መገረዝ አለበት፤ በሥጋችሁ የሚፈጸመው ይህ ኪዳኔ የዘላለም ኪዳን ይሆናል።
ዘፍጥረት 17:12-13 살펴보기
홈
성경
묵상
동영상