ዘፍጥረት 6

6
የጥፋት ውሃ
1ሰዎች በምድር ላይ እየበዙ ሲሄዱ ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው። 2የእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ወንዶች ልጆች የሰዎችን ሴቶች ልጆች ውብ ሆነው አዩአቸው፤ ከመካከላቸውም የመረጧቸውን አገቡ። 3እግዚአብሔርም (ያህዌ)፣ “ሰው ሟች#6፥3 ወይም በስባሽ ስለሆነ መንፈሴ እያዘነ#6፥3 ወይም መንፈሴ አይኖርም ከእርሱ ጋር ለዘላለም አይኖርም፤ ዕድሜው 120 ዓመት ይሆናል” አለ።
4የእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ልጆች የሰዎችን ሴቶች ልጆች ተገናኝተው ልጆች በወለዱ ጊዜም ሆነ ከዚያም በኋላ ኔፊሊም የተባሉ ሰዎች በምድር ላይ ነበሩ። እነርሱም በጥንቱ ዘመን በጀግንነታቸው ከፍ ያለ ዝና ያተረፉ ናቸው።
5 እግዚአብሔር (ያህዌ) አምላክ የሰው ዐመፅ በምድር ላይ የበዛና የልቡም ሐሳብ ዘወትር ወደ ክፋት ብቻ ያዘነበለ መሆኑን ተመለከተ። 6እግዚአብሔር (ያህዌ) ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፤ ልቡም እጅግ ዐዘነ። 7ስለዚህም እግዚአብሔር (ያህዌ)፣ “የፈጠርሁትን የሰው ዘር ከምድረ ገጽ አጠፋለሁ፤ ከሰው እስከ እንስሳ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጡራን እስከ ሰማይ ወፎች አጠፋለሁ፤ ስለ ፈጠርኋቸው ተጸጽቻለሁና” አለ። 8ኖኅ ግን በእግዚአብሔር (ያህዌ) ዘንድ ሞገስን አገኘ።
9የኖኅ ታሪክ እንደሚከተለው ነው፤ ኖኅ በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ ይልቅ ጻድቅና ከበደል የራቀ ሰው ነበር፤ አካሄዱንም ከእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ጋር አደረገ።
10ኖኅም ሴም፣ ካምና ያፌት የሚባሉ ሦስት ወንዶች ልጆች ነበሩት።
11ምድር በእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ፊት በክፉ ሥራ ረከሰች፤ በዐመፅም ተሞላች። 12እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ምድር ምን ያህል በክፉ ሥራ እንደ ረከሰች አየ። እነሆ፤ ሰው ሁሉ አካሄዱን አበላሽቶ ነበርና 13ስለዚህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ኖኅን እንዲህ አለው፦ “ሰውን ሁሉ ላጠፋ ነው፤ ምድር በሰው ዐመፅ ስለ ተሞላች በርግጥ ሰውንም ምድርንም አጠፋለሁ። 14አንተ ግን በጎፈር#6፥14 በዕብራይስጥ የዚህ ቃል ትርጕም አይታወቅም። ዕንጨት መርከብ ሥራ፤ ለመርከቧም ክፍሎች አብጅላት፤ ውስጧንና ውጭዋን በቅጥራን ለብጠው። 15እንዲህ አድርገህ ሥራት፦ ርዝመቷ 140 ሜትር፣ ወርዷ 23 ሜትር፣ ከፍታዋ 13.5 ሜትር ይሁን። 16ለመርከቧ ጣራ አብጅላት፣ ጣራና ግድግዳው በሚጋጠምበት ቦታ ግማሽ ሜትር ክፍተት ተው፤#6፥16 ወይም ለብርሃን መግቢያ አድርገህ ሥራ ከጐኗ በር አውጣላት፤ ባለ ሦስት ፎቅ አድርገህ ሥራት። 17እኔም ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለባቸውን ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ለማጥፋት እነሆ፤ በምድር ላይ የጥፋት ውሃ አወርዳለሁ፤ በምድር ላይ ያለ ሁሉ ይጠፋል። 18ከአንተ ጋር ግን ቃል ኪዳን እመሠርታለሁ። አንተና ወንዶች ልጆችህ፣ ሚስትህና የልጆችህ ሚስቶች ከአንተ ጋር ወደ መርከቧ ትገባላችሁ። 19ከአንተ ጋር በሕይወት እንዲቈዩ ከሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ተባዕትና እንስት እያደረግህ ሁለት ሁለቱን ወደ መርከቧ ታስገባለህ። 20ከእያንዳንዱ የወፍ ወገን፣ ከእያንዳንዱ የእንስሳ ወገን፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረት ሁሉ በየወገናቸው በሕይወት ይቈዩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ አንተ ይመጣሉ። 21ለአንተና ለእነርሱ የሚያስፈልገውን ምግብ ሁሉ አከማች።”
22ኖኅም ሁሉን እግዚአብሔር (ኤሎሂም) እንዳዘዘው አደረገ።

Pilihan Saat Ini:

ዘፍጥረት 6: NASV

Sorotan

Berbagi

Salin

None

Ingin menyimpan sorotan di semua perangkat Anda? Daftar atau masuk