የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 9

9
ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ስለ ማዳኑ
1ከዚ​ያም ሲያ​ልፍ ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ሰው አየ። 2ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደው በማን ኀጢ​ኣት ነው? በራሱ ነውን? ወይስ በወ​ላ​ጆቹ?” ብለው ጠየ​ቁት። 3ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ሊገ​ለ​ጥ​በት ነው እንጂ እርሱ አል​በ​ደ​ለም፤ ወላ​ጆ​ቹም አል​በ​ደ​ሉም። 4ነገር ግን ቀን ሳለ የላ​ከ​ኝን ሥራ ልሠራ ይገ​ባ​ኛል፤ ማንም ሥራ ሊሠራ የማ​ይ​ች​ል​ባት ሌሊት ትመ​ጣ​ለ​ችና። 5#ማቴ. 5፥14፤ ዮሐ. 8፥12። በዓ​ለም ሳለሁ፤ የዓ​ለም ብር​ሃን እኔ ነኝ።” 6ይህ​ንም ብሎ በም​ድር ላይ ምራ​ቁን እን​ትፍ አለ፤ በም​ራ​ቁም ጭቃ አድ​ርጎ የዕ​ዉ​ሩን ዐይ​ኖች ቀባው። 7እን​ዲ​ህም አለው፥ “ሂድና በሰ​ሊ​ሆም መጠ​መ​ቂያ ታጠብ” ትር​ጓ​ሜ​ውም የተ​ላከ ማለት ነው፤ ሄዶም ታጠ​በና እያየ ተመ​ለሰ። 8ጎረ​ቤ​ቶ​ቹና ቀድሞ የሚ​ያ​ው​ቁት፥#“የሚ​ያ​ው​ቁት” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ሲለ​ም​ንም ያዩት የነ​በ​ሩት ግን፥ “ይህ በመ​ን​ገድ#“በመ​ን​ገድ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ የለም። ተቀ​ምጦ ይለ​ምን የነ​በ​ረው አይ​ደ​ለም?” አሉ። 9“ይህ እርሱ ነው” ያሉ አሉ፤ ሌሎ​ችም፥ “አይ​ደ​ለም፤ ይመ​ስ​ለ​ዋል እንጂ” አሉ፤ እርሱ ራሱ ግን፥ “እኔ ነኝ” አለ። 10እነ​ር​ሱም፥ “ዐይ​ኖ​ችህ እን​ዴት ተገ​ለጡ?” አሉት። 11እር​ሱም መልሶ፥ “ኢየ​ሱስ የሚ​ባ​ለው ሰው በም​ራቁ ጭቃ አድ​ርጎ ዐይ​ኖ​ችን ቀባ​ኝና ሂደህ በሰ​ሊ​ሆም ውኃ ታጠብ አለኝ፤ ሄጄም ታጠ​ብ​ሁና አየሁ” አላ​ቸው። 12አይ​ሁ​ድም፥ “ሰው​የው የት አለ?” አሉት፤ እር​ሱም፥ “አላ​ው​ቅም” አላ​ቸው።
13ያን ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደ​ው​ንም ሰው ወደ ፈሪ​ሳ​ው​ያን ወሰ​ዱት። 14ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በም​ራቁ ጭቃ አድ​ርጎ ዐይ​ኖ​ቹን ያበ​ራ​በት ቀኑ ሰን​በት ነበ​ርና። 15ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም እን​ዴት እን​ዳየ ዳግ​መኛ ጠየ​ቁት፤ እር​ሱም፥ “በም​ራቁ ጭቃ አድ​ርጎ በዐ​ይ​ኖች አኖ​ረው፥ ታጥ​ቤም አየሁ” አላ​ቸው። 16ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም አን​ዳ​ን​ዶች፥ “ይህ ሰው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለም፤ ሰን​በ​ትን አያ​ከ​ብ​ር​ምና” አሉ፤ ሌሎች ግን “ኀጢ​ኣ​ተኛ ሰው እን​ዲህ ያለ ተአ​ም​ራት ማድ​ረግ እን​ዴት ይች​ላል?” አሉ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተለ​ያዩ። 17ዳግ​መ​ኛም ዕዉ​ሩን፥ “አንተ ስለ እርሱ ምን ትላ​ለህ? ዐይ​ኖ​ች​ህን ከፍ​ቶ​ል​ሃ​ልና” አሉት፤ እር​ሱም፥ “ነቢይ ነው” አላ​ቸው።
18አይ​ሁ​ድም የዚ​ያን ያየ​ውን ሰው ወላ​ጆች እስ​ኪ​ጠሩ ድረስ ዕዉር ሆኖ እንደ ተወ​ለደ፥#ግሪኩ “ዕዉር እንደ ነበረ” ይላል። እን​ዳ​የም አላ​መ​ኑም። 19“ዕዉር ሆኖ ተወ​ለደ የም​ት​ሉት ልጃ​ችሁ ይህ ነውን? እን​ግ​ዲያ አሁን እን​ዴት ያያል?” ብለው ጠየ​ቁ​አ​ቸው። 20ወላ​ጆ​ቹም መል​ሰው እን​ዲህ አሉ፥ “ይህ ልጃ​ችን እንደ ሆነ፥ ዕዉር ሆኖም እንደ ተወ​ለደ እና​ው​ቃ​ለን። 21አሁን ግን እን​ዴት እን​ደ​ሚ​ያይ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ማን እንደ አበ​ራ​ለት አና​ው​ቅም፤ እር​ሱን ጠይ​ቁት፤ ዐዋቂ ነውና፤ ስለ ራሱም መና​ገር ይች​ላ​ልና።” 22ወላ​ጆቹ አይ​ሁ​ድን ስለ ፈሩ ይህን አሉ፥ “እርሱ ክር​ስ​ቶስ ነው ብሎ በእ​ርሱ የሚ​ያ​ምን ቢኖር ከም​ኵ​ራብ ይውጣ” ብለው አይ​ሁድ ተስ​ማ​ም​ተው ነበ​ርና። 23ስለ​ዚ​ህም ወላ​ጆቹ፥ “ዐዋቂ ነውና እር​ሱን ጠይ​ቁት” አሉ። 24ዕውር የነ​በ​ረ​ው​ንም ሰው ዳግ​መኛ ጠር​ተው፥ “ሂድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና አቅ​ርብ፤ ይህ ሰው ኀጢ​ኣ​ተኛ እንደ ሆነ እኛ እና​ው​ቃ​ለን” አሉት። 25ያም ሰው መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እርሱ ኀጢ​ኣ​ተኛ እንደ ሆነ እኔ አላ​ው​ቅም፤ እኔ ዕዉር እንደ ነበ​ርሁ፤ አሁን ግን እን​ደ​ማይ ይህን አንድ ነገር ብቻ አው​ቃ​ለሁ።” 26ዳግ​መ​ኛም፥ “ምን አደ​ረ​ገ​ልህ? ዐይ​ኖ​ች​ህ​ንስ እን​ደ​ምን አበ​ራ​ልህ?” አሉት። 27እር​ሱም መልሶ፥ “አት​ሰ​ሙ​ኝም እንጂ ነገ​ር​ኋ​ችሁ፤ እን​ግ​ዲህ ደግሞ ምን ልት​ሰሙ ትሻ​ላ​ችሁ? እና​ን​ተም ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ልት​ሆኑ ትሻ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው። 28እነ​ር​ሱም ሰደ​ቡት፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “አንተ የእ​ርሱ ደቀ መዝ​ሙር ሁን፤ እኛስ የሙሴ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ነን። 29እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እንደ ተነ​ጋ​ገ​ረው እና​ው​ቃ​ለን፤ ይህን ግን ከወ​ዴት እንደ ሆነ አና​ው​ቅም።” 30ያም ሰው መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ከወ​ዴት እንደ ሆነ፥ አታ​ው​ቁ​ት​ምና ይህ እጅግ ድንቅ ነው፤ ነገር ግን ዐይ​ኖ​ችን አበ​ራ​ልኝ። 31እኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ራ​ው​ንና ፈቃ​ዱን የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን እር​ሱን ይሰ​ማ​ዋል እንጂ ኃጥ​ኣ​ንን እን​ደ​ማ​ይ​ሰ​ማ​ቸው እና​ው​ቃ​ለን። 32ዓለም ከተ​ፈ​ጠረ ጀምሮ ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ዐይ​ኖች ያበራ አል​ተ​ሰ​ማም። 33ይህ ሰው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባይ​ሆን ኖሮ ምንም ማድ​ረግ ባል​ቻ​ለም ነበር።” 34እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “ራስህ በኀ​ጢ​ኣት የተ​ወ​ለ​ድህ አንተ እኛን ታስ​ተ​ም​ረ​ና​ለ​ህን?” አሉት፤ ወደ ውጭም አወ​ጡት። 35ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ ውጭ እን​ዳ​ወ​ጡት ሰማ፤ አገ​ኘ​ው​ምና፥ “አንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ታም​ና​ለ​ህን?” አለው። 36ያ ሰውም፥ “አቤቱ፥ አም​ን​በት ዘንድ እርሱ ማነው?” ብሎ መለ​ሰ​ለት። 37ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የም​ታ​የው፥ ከአ​ንተ ጋርም የሚ​ነ​ጋ​ገ​ረው እርሱ ነው” አለው። 38እር​ሱም፥ “አቤቱ፥ አም​ና​ለሁ” ብሎ ሰገ​ደ​ለት። 39ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ የማ​ያ​ዩት እን​ዲ​ያዩ፥ የሚ​ያ​ዩ​ትም እን​ዲ​ታ​ወሩ ወደ​ዚህ ዓለም ለፍ​ርድ መጥ​ቻ​ለሁ” አለው። 40ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ይህን ሲና​ገር ሰም​ተው፥ “እኛ ደግሞ ዕዉ​ሮች ነን?” አሉት። 41ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ዕዉ​ሮ​ችስ ብት​ሆኑ ኀጢ​ኣት ባል​ሆ​ነ​ባ​ች​ሁም ነበር፤ አሁን ግን እና​ያ​ለን ትላ​ላ​ችሁ፤ አታ​ዩ​ምም፤ ስለ​ዚ​ህም ኀጢ​ኣ​ታ​ችሁ ጸንቶ ይኖ​ራል” አላ​ቸው።

Sorotan

Berbagi

Salin

None

Ingin menyimpan sorotan di semua perangkat Anda? Daftar atau masuk