ኦሪት ዘፍጥረት 2
2
1ሰማይና ምድር ሠራዊታቸዉም ሁሉ ተፈጸመ። 2እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኚው ቀን ፈጸመ፤ በሰባተኚውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። ፈጸመ፤ በሰባተኚውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። 3እግዚአብሔርም ሰባተኚውን ቀን ባረከው ቀደሰውም፤ እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረዉ ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና። 4እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ አምላክ ሰማይንና ምድርን ቀን፤ በተፈጠሩ ጊዜ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው። 5የሜዳ ቁጥቋጦ ሁሉ በምድር ላይ ገና አልነበረም የሜዳውም ቡቃያ ሁሉ ገና አልነበረም ነበር፤ እግዚአብሔር አምላክ ምድር ላይ አላዘነበም ነበርና፤ ምድርም የሚሠራባት በምድር ላይ አላዘነበም ነበርና፤ 6ምድርንም የሚሠራባት ሰው አልነበረም፤ ነገር ግን ጉም ከምድር ትወጣ ነበር፤ የምድርንም ፊት ሁሉ ታጠጣ ነበር። 7እግዚአብሔር አምላክም ሰውንም ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ። 8እግዚአብሔር አምላክም በምሥራቅ በዔድን ገነትን ተከለ የፈጠረውንም ሰው ከዚያው አኖረው። 9እግዚአብሔር አምላክም ለማየት ደስ የሚያስኘውን፤ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፤ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፤ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ። 10ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከዔድን ይወጣ ነበር፤ ከዚያም ከአራት ክፍል ይከፈል ነበር። 11የአንደኚው ወንዝ ስም ፊሶን ነው፤ እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል፤ የዚያም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው። 12ከዚያም ሉልና የከበረ ድንጋይ ይገኚል። 13የሁለተኚውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል። 14የሦስተኚውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው፤ እርሱም በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነው። 15አራተኚውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው። እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔድን ገንት አኖረው። 16እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፤ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ 17ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና። 18እግዚእብሔር አምላክም አለ፤ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም የሚመቸውን ረት እንፍጠርለት። 19እግዚአብሔር አምላክም የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎእን ሁሉ ከመሬት አደረገ በምን ስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው፤ እዳምም ሕያው ነፍስ ልስለው ሁሉ በስሙ እንደ ጠርው ስሙ ያው ሆነ። 20አዳምም ለእንስሳት ሁሉ፤ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፤ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላአው፤ ነገር ግን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር። 21እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ከባድ እንቅልፍን ጣለበት፤ አንቀላዳም ከጎኑም አንዲት እጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው። 22እግዚእብሔር አምልስክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት ወደ አዳምም አመጣት። 23አዳምም አለ፤ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፤ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። 24ስለዚህ ሰዉ አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ በሚስቱም ይጣበቃ፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። 25አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፤ አይተፋፈሩም ነበር።
Actualmente seleccionado:
ኦሪት ዘፍጥረት 2: አማ54
Destacar
Compartir
Copiar
¿Quieres guardar tus resaltados en todos tus dispositivos? Regístrate o Inicia sesión