Logo YouVersion
Ikona vyhledávání

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 7

7
የመ​ስ​ፍኑ ሎሌ እንደ ዳነ
1ለሕ​ዝ​ቡም ቃሉን ነግሮ ከፈ​ጸመ በኋላ ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆም ገባ። 2አንድ የመቶ አለ​ቃም ነበረ፤ አገ​ል​ጋ​ዩም ታሞ ሊሞት ቀርቦ ነበር፤ እር​ሱም በእ​ርሱ ዘንድ የተ​ወ​ደደ ነበር። 3የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስ​ንም ነገር በሰማ ጊዜ፥ መጥቶ አገ​ል​ጋ​ዩን እን​ዲ​ያ​ድ​ን​ለት ይማ​ል​ዱት ዘንድ የአ​ይ​ሁ​ድን ሽማ​ግ​ሎች ወደ እርሱ ላከ። 4ወደ ጌታ​ችን ወደ ኢየ​ሱ​ስም መጥ​ተው ማለ​ዱት፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “ፈጥ​ነህ ውረድ፤#“ፈጥ​ነህ ውረድ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ይህን ልታ​ደ​ር​ግ​ለት ይገ​ባ​ዋ​ልና። 5እርሱ ወገ​ና​ች​ንን ይወ​ዳ​ልና፤ ምኵ​ራ​ባ​ች​ን​ንም ሠር​ቶ​ል​ና​ልና።” 6ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሄደ፤ ወደ ቤቱም በቀ​ረበ ጊዜ፥ የመቶ አለ​ቃዉ ወዳ​ጆ​ቹን እን​ዲህ ብሎ ላከ፥ “አቤቱ፥ አት​ድ​ከም፤ ከቤቴ ጣራ በታች ልት​ገባ አይ​ገ​ባ​ኝ​ምና። 7እኔም ወደ አንተ ልመጣ አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ነገር ግን በቃ​ልህ እዘዝ፤ ብላ​ቴ​ና​ዬም ይድ​ናል። 8እኔም እኮ ገዢ ሰው ነኝ፤ ወታ​ደ​ሮ​ችም አሉኝ፤ አን​ዱን ሂድ ብለው ይሄ​ዳል፤ ሌላ​ው​ንም ና ብለው ይመ​ጣል፤ አገ​ል​ጋ​ዬ​ንም እን​ዲህ አድ​ርግ ብለው ያደ​ር​ጋል።” 9ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ከእ​ርሱ በሰማ ጊዜ አደ​ነ​ቀው፤ ዘወር ብሎም ይከ​ተ​ሉት ለነ​በ​ሩት ሕዝብ፥ “እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልስ እንኳ እን​ዲህ ያለ እም​ነት ያለው ሰው አላ​ገ​ኘ​ሁም” አላ​ቸው። 10የተ​ላ​ኩ​ትም በተ​መ​ለሱ ጊዜ ብላ​ቴ​ና​ውን ድኖ አገ​ኙት።
ስለ መበ​ለ​ቲቱ ልጅ መዳን
11በማ​ግ​ሥ​ቱም ናይን ወደ​ም​ት​ባል ወደ አን​ዲት ከተማ ሄደ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ብዙ ሕዝ​ብም አብ​ረ​ውት ሄዱ። 12ወደ ከተ​ማው በር በደ​ረሰ ጊዜም እነሆ፥ ያን​ዲት መበ​ለት ሴት ልጅ ሙቶ ሬሳ​ውን ተሸ​ክ​መው ሲሄዱ አገኘ፤ ይኸ​ውም ለእ​ናቱ አንድ ነበረ፤ ብዙ​ዎ​ችም የከ​ተማ ሰዎች አብ​ረ​ዋት ነበሩ። 13ጌታ​ች​ንም በአ​ያት ጊዜ አዘ​ነ​ላ​ትና፥ “አታ​ል​ቅሺ” አላት። 14ቀር​ቦም ቃሬ​ዛ​ውን ያዘ፤ የተ​ሸ​ከ​ሙ​ትም ቆሙ፤ እር​ሱም፥ “አንተ ጐበዝ ተነሥ እል​ሃ​ለሁ” አለው። 15የሞ​ተ​ውም ተነ​ሥቶ ተቀ​መጠ፤ መና​ገ​ርም ጀመረ፤ ለእ​ና​ቱም ሰጣት። 16ሁሉም ፈሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገኑ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ታላቅ ነቢይ ተነ​ሣ​ልን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ጐብ​ኝ​ቶ​አ​ልና።” 17ይህም የእ​ርሱ ዜና በይ​ሁዳ ሀገ​ሮች ሁሉና በአ​ው​ራ​ጃዋ ሁሉ ተሰማ።
ከዮ​ሐ​ንስ ስለ ተላ​ኩት መል​እ​ክ​ተ​ኞች
18ይህ​ንም ሁሉ ደቀ መዝ​ሙ​ርቱ ለዮ​ሐ​ንስ ነገ​ሩት። 19ዮሐ​ን​ስም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሁለ​ቱን ጠርቶ፥ “የሚ​መ​ጣው አንተ ነህን? ወይስ ተስፋ የም​ና​ደ​ር​ገው ሌላ አለ?” ብሎ ወደ ጌታ​ችን ወደ ኢየ​ሱስ ላካ​ቸው። 20መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ወደ እርሱ ደር​ሰው፥ “የሚ​መ​ጣው አንተ ነህን? ወይስ ተስፋ የም​ና​ደ​ር​ገው ሌላ አለ? ብሎ መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ ወደ አንተ ልኮ​ናል” አሉት። 21ያን​ጊ​ዜም ብዙ​ዎ​ችን ከደ​ዌ​አ​ቸ​ውና ከሕ​መ​ማ​ቸው ከክ​ፉ​ዎች አጋ​ን​ን​ትም ፈወ​ሳ​ቸው፤ ለብ​ዙ​ዎች ዕው​ራ​ንም እን​ዲ​ያዩ ብር​ሃ​ንን ሰጣ​ቸው። 22#ኢሳ. 35፥5-6፤ 61፥1። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሄዳ​ችሁ ያያ​ች​ሁ​ት​ንና የሰ​ማ​ች​ሁ​ትን ለዮ​ሐ​ንስ ንገ​ሩት፤ ዕው​ሮች ያያሉ፤ አን​ካ​ሶ​ችም ይሄ​ዳሉ፤ ለም​ጻ​ሞ​ችም ይነ​ጻሉ፤ ደን​ቆ​ሮ​ችም ይሰ​ማሉ፤ ሙታ​ንም ይነ​ሣሉ፤ ለድ​ሆ​ችም ወን​ጌል ይሰ​በ​ካል። 23በእ​ኔም የማ​ይ​ሰ​ና​ከል ብፁዕ ነው።”
ጌታ መጥ​ምቁ ዮሐ​ን​ስን ስለ ማመ​ስ​ገኑ
24የዮ​ሐ​ንስ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም ከሄዱ በኋላ ለሕ​ዝቡ ስለ መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ እን​ዲህ ይላ​ቸው ጀመር፥ “ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣ​ችሁ? ከነ​ፋስ የተ​ነሣ የሚ​ወ​ዛ​ወዝ ሸን​በ​ቆን ነውን? 25ወይስ ምን ልታዩ ወጥ​ታ​ች​ኋል? ቀጭን ልብስ የለ​በ​ሰ​ውን ሰው ነውን? እነሆ፥ በክ​ብር ልብስ ያጌ​ጡስ በነ​ገ​ሥ​ታት ቤት አሉ። 26ወይስ ምን ልታዩ ወጥ​ታ​ች​ኋል? ነቢ​ይን ነውን? አዎን፥ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከነ​ቢ​ይም ይበ​ል​ጣል። 27#ሚል. 3፥1። እነሆ፥ መን​ገ​ድ​ህን በፊ​ትህ የሚ​ጠ​ርግ መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ዬን በፊ​ትህ እል​ካ​ለሁ፥ ተብሎ ስለ እርሱ የተ​ጻ​ፈ​ለት ይህ ነው። 28እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሴቶች ከወ​ለ​ዱ​አ​ቸው መካ​ከል ከመ​ጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ የሚ​በ​ልጥ ማንም አል​ተ​ነ​ሣም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ግን የሚ​ያ​ን​ሰው ይበ​ል​ጠ​ዋል።” 29#ማቴ. 21፥32፤ ሉቃ. 3፥12። ሕዝ​ቡም ሁሉ ቀራ​ጮ​ችም በሰሙ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጻድቅ ነው አሉት፤ የዮ​ሐ​ን​ስን ጥም​ቀት ተጠ​ም​ቀው ነበ​ርና። 30ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንና የሕግ ጻፎች ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ#በግ​ሪኩ “ምክር” ይላል። ተቃ​ወሙ፤ በእ​ርሱ አል​ተ​ጠ​መ​ቁ​ምና።
31“እን​ግ​ዲህ የዚ​ችን ትው​ልድ ሰዎች በምን እመ​ስ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ? ማን​ንስ ይመ​ስ​ላሉ? 32በገ​በያ ተቀ​ም​ጠው ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ጠር​ተው፥ “አቀ​ነ​ቀ​ን​ላ​ችሁ፥#በግ​ሪኩ “እም​ቢ​ልታ ነፋ​ን​ላ​ችሁ” ይላል። አል​ዘ​ፈ​ና​ች​ሁ​ምም፤ ሙሾም አወ​ጣ​ን​ላ​ችሁ፥ አላ​ለ​ቀ​ሳ​ች​ሁ​ምም የሚ​ሉ​አ​ቸው ልጆ​ችን ይመ​ስ​ላሉ። 33መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ እህል ሳይ​በላ ወይ​ንም ሳይ​ጠጣ መጥቶ ነበ​ርና ጋኔን አለ​በት አላ​ች​ሁት። 34የሰው ልጅም እየ​በ​ላና እየ​ጠጣ መጣ፤ እና​ንተ ግን እነሆ፥ በላ​ተ​ኛና ወይን ጠጪ ሰው፥ የኃ​ጥ​ኣ​ንና የቀ​ራ​ጮች ወዳጅ አላ​ች​ሁት። 35ጥበ​ብም ከል​ጆ​ችዋ ሁሉ ጸደ​ቀች።”
ስለ ፈሪ​ሳ​ዊ​ውና ስለ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ዪቱ ሴት
36ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም አንዱ በእ​ርሱ ዘንድ ምሳ እን​ዲ​በላ ለመ​ነው፤ ወደ ፈሪ​ሳ​ዊ​ውም ቤት ገብቶ በማ​ዕድ ተቀ​መጠ። 37እነሆ፥ ከዚ​ያች ከተማ ሰዎ​ችም አን​ዲት ኀጢ​አ​ተኛ ሴት በፈ​ሪ​ሳ​ዊው ቤት በማ​ዕድ እን​ደ​ተ​ቀ​መጠ ዐውቃ ሽቱ የሞ​ላ​በት የአ​ል​ባ​ስ​ጥ​ሮስ ቢል​ቃጥ ገዝታ መጣች። 38#ማቴ. 26፥7፤ ማር. 14፥3፤ ዮሐ. 12፥3። በስ​ተ​ኋ​ላ​ውም በእ​ግ​ሮቹ አጠ​ገብ ቆማ አለ​ቀ​ሰች፤ እግ​ሮ​ቹ​ንም በእ​ን​ባዋ ታርስ ነበር፥ በራስ ጠጕ​ር​ዋም እግ​ሮ​ቹን ታብ​ሰ​ውና ትስ​መው፥ ሽቱም ትቀ​ባው ነበር። 39የጠ​ራው ፈሪ​ሳ​ዊም ባየ ጊዜ በልቡ ዐሰበ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህስ ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህቺ የም​ት​ዳ​ስ​ሰው ሴት ማን እንደ ሆነች፥ እን​ዴ​ትስ እንደ ነበ​ረች ባላ​ወ​ቀም ነበ​ርን? ኀጢ​አ​ተኛ ናትና።” 40ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ስም​ዖን ሆይ፥ የም​ነ​ግ​ርህ ነገር አለኝ” አለው፤ እር​ሱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ተና​ገር” አለው። 41እር​ሱም እን​ዲህ አለው፥ “ለአ​ንድ አበ​ዳሪ ሁለት ባለ ዕዳ​ዎች ነበ​ሩት፤ በአ​ንዱ አም​ስት መቶ ዲናር ነበ​ረ​በት፤ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም አምሳ። 42የሚ​ከ​ፍ​ሉ​ትም ባጡ ጊዜ ለሁ​ለ​ቱም ተወ​ላ​ቸው፤ እን​ግ​ዲህ ከሁ​ለቱ አብ​ልጦ ሊወ​ደው የሚ​ገ​ባው ማን​ኛው ነው?” 43ስም​ዖ​ንም መልሶ፥ “ብዙ​ውን የተ​ወ​ለት ነው እላ​ለሁ” አለው፤ እር​ሱም፥ “መል​ካም ፈረ​ድህ” አለው። 44ወደ ሴቲ​ቱም ዘወር ብሎ ስም​ዖ​ንን እን​ዲህ አለው፥ “ይህ​ቺን ሴት ታያ​ታ​ለ​ህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ለእ​ግ​ሮች ውኃ ስንኳ አል​ሰ​ጠ​ኸ​ኝም፤ እር​ስዋ ግን አል​ቅሳ በእ​ን​ባዋ እግ​ሬን አራ​ሰች፤ በጠ​ጕ​ር​ዋም አበ​ሰች። 45አን​ተስ ሰላ​ምታ አል​ሰ​ጠ​ኸ​ኝም፤ እር​ስዋ ግን ከገ​ባሁ ጀምሮ እግ​ሬን ከመ​ሳም አላ​ቋ​ረ​ጠ​ችም። 46አንተ ራሴን እንኳ ዘይት አል​ቀ​ባ​ኸ​ኝም፤ እር​ስዋ ግን እግ​ሬን ሽቱ ቀባ​ችኝ። 47ስለ​ዚ​ህም እል​ሃ​ለሁ፤ ብዙ ኀጢ​ኣቷ ተሰ​ር​ዮ​ላ​ታል፤ በብዙ ወድ​ዳ​ለ​ችና፤ ጥቂት የሚ​ወ​ድድ ጥቂት ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል፤ ብዙ የሚ​ወ​ድ​ድም ብዙ ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።”#“ብዙ የሚ​ወ​ድድ ብዙ ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። 48ሴቲ​ቱ​ንም፥ “ኀጢ​ኣ​ትሽ ተሰ​ረ​የ​ልሽ” አላት። 49በማ​ዕዱ የተ​ቀ​መ​ጡ​ትም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ኀጢ​አ​ትን የሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ርይ ይህ ማነው?” ይሉ ጀመር። 50ሴቲ​ቱ​ንም አላት፥ “እም​ነ​ትሽ አድ​ኖ​ሻል፤ በሰ​ላም ሂጂ።”

Zvýraznění

Sdílet

Kopírovat

None

Chceš mít své zvýrazněné verše uložené na všech zařízeních? Zaregistruj se nebo se přihlas

Video k የሉ​ቃስ ወን​ጌል 7