Logo YouVersion
Ikona vyhledávání

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 6

6
ስለ ሰን​በት
1 # ዘዳ. 23፥25። ከዚ​ህም በኋላ ደግሞ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በሰ​ን​በት ቀን በእ​ርሻ መካ​ከል ሄደ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እሸት ቈር​ጠው በእ​ጃ​ቸው እያሹ በሉ። 2ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “በሰ​ን​በት ሊደ​ረግ የማ​ይ​ገ​ባ​ውን ለምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?” አሉ​አ​ቸው። 3#1ሳሙ. 21፥1-6። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እር​ሱና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትም በተ​ራቡ ጊዜ ዳዊት ያደ​ረ​ገ​ውን አላ​ነ​በ​ባ​ች​ሁ​ምን? 4#ዘሌ. 24፥9። ወደ ቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገባ፥ ከካ​ህ​ና​ቱም ብቻ በቀር ሊበ​ሉት የማ​ይ​ገ​ባ​ውን የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን ኅብ​ስት ወስዶ እንደ በላ፥ አብ​ረ​ውት ለነ​በ​ሩ​ትም እንደ ሰጣ​ቸው አላ​ነ​በ​ባ​ች​ሁ​ምን? 5የሰው ልጅ ለሰ​ን​በት ጌታዋ ነው” አላ​ቸው።
እጁ ስለ ደረ​ቀ​ችው ሰው
6ከዚ​ህም በኋላ በሌ​ላ​ይቱ ሰን​በት ወደ ምኵ​ራቡ ገባና አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ በዚ​ያም ቀኝ እጁ የሰ​ለ​ለች ሰው ነበረ። 7ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም የሚ​ከ​ሱ​በት ምክ​ን​ያት ያገኙ ዘንድ፥ በሰ​ን​በት ይፈ​ው​ሰው እንደ ሆነ ብለው ይጠ​ባ​በ​ቁት ነበር። 8እርሱ ግን ዐሳ​ባ​ቸ​ውን ያው​ቅ​ባ​ቸው ነበ​ርና እጁ የሰ​ለ​ለ​ች​ውን ሰው፥ “ተነ​ሥ​ተህ በመ​ካ​ከል ቁም” አለው፤ ተነ​ሥ​ቶም ቆመ። 9ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እጠ​ይ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ በሰ​ን​በት ሊደ​ረግ የሚ​ገ​ባው ምን​ድ​ነው? መል​ካም መሥ​ራት ነውን? ወይስ ክፉ መሥ​ራት? ነፍ​ስን ማዳን ነውን? ወይስ መግ​ደል?” 10እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ ወደ እነ​ር​ሱም ዙሮ ከተ​መ​ለ​ከተ በኋላ፦ ያን ሰው፥ “እጅ​ህን ዘርጋ” አለው፤ ሰው​ዬ​ውም ዘረ​ጋት፤ እጁም ዳነ​ችና እንደ ሁለ​ተ​ኛ​ይቱ ሆነች። 11እነ​ርሱ ግን፥ እጅግ ተቈጡ፤ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱ​ስም ምን እን​ድ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​በት እርስ በር​ሳ​ቸው ተማ​ከሩ።
ሐዋ​ር​ያ​ትን ስለ መም​ረጡ
12በዚ​ያም ወራት ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ሊጸ​ልይ ወደ ተራራ ወጣ፤ ሌሊ​ቱን ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ልይ ነበር፤ 13ሲነ​ጋም ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን ወደ እርሱ ጠራ​ቸው፤ ከው​ስ​ጣ​ቸ​ውም ዐሥራ ሁለ​ቱን መረጠ፤ ሐዋ​ር​ያት ብሎም ሰየ​ማ​ቸው። 14እነ​ር​ሱም እነ​ዚህ ናቸው፦ ጴጥ​ሮስ የተ​ባ​ለው ስም​ዖን፥ ወን​ድ​ሙም እን​ድ​ር​ያስ፥ ያዕ​ቆ​ብና ዮሐ​ንስ፥ ፊል​ጶ​ስና በር​ተ​ሎ​ሜ​ዎስ። 15ማቴ​ዎ​ስና ቶማስ፥ የእ​ል​ፍ​ዮስ ልጅ ያዕ​ቆ​ብና ቀናዒ የሚ​ባ​ለው ስም​ዖን። 16የያ​ዕ​ቆብ ወን​ድም ይሁዳ፥ የከ​ዳ​ውና#“የከ​ዳ​ውና” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። አሳ​ልፎ የሰ​ጠው ያስ​ቆ​ሮቱ ሰው ይሁ​ዳም ናቸው። 17ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ወርዶ በሰፊ ቦታ ቆመ፤ ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ወገን ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከመ​ላው ይሁ​ዳና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ከጢ​ሮ​ስና ከሲ​ዶና ባሕር ዳርቻ ትም​ህ​ር​ቱን ሊሰሙ፥ ከደ​ዌ​አ​ቸ​ውም ሊፈ​ወሱ የመ​ጡት ከሕ​ዝቡ ወገን እጅግ ብዙ​ዎች ነበሩ። 18ክፉ​ዎች አጋ​ን​ንት ያደ​ሩ​ባ​ቸ​ውም ይፈ​ወሱ ነበር። 19ሕዝቡ ሁሉ ሊዳ​ስ​ሱት ይሹ ነበር፤ ኀይል ከእ​ርሱ ይወጣ ነበ​ርና፥ ሁሉ​ንም ይፈ​ው​ሳ​ቸው ነበር።
በተ​ራራ ላይ ስለ አስ​ተ​ማ​ረው ትም​ህ​ርት
20እር​ሱም ወደ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ዐይ​ኖ​ቹን አን​ሥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ድሆች፥ ብፁ​ዓን ናችሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት የእ​ና​ንተ ናትና። 21ዛሬ የም​ት​ራቡ፥ ብፁ​ዓን ናችሁ፤ ትጠ​ግ​ባ​ላ​ች​ሁና፤ ዛሬ የም​ታ​ለ​ቅሱ፥ ብፁ​ዓን ናችሁ፤ ትስ​ቃ​ላ​ች​ሁና። 22#1ጴ​ጥ. 4፥14። ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ቢጠ​ሉ​አ​ችሁ፥ ከሰው ለይ​ተው ቢአ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ችሁ፥ ቢሰ​ድ​ቡ​አ​ችሁ፥ ክፉ ስምም ቢአ​ወ​ጡ​ላ​ችሁ ብፁ​ዓን ናችሁ። 23#2ዜ.መ. 36፥16፤ የሐዋ. 7፥52። ያን​ጊዜ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ በደ​ስ​ታም ዝለሉ፤ ዋጋ​ችሁ በሰ​ማይ ብዙ ነውና፤ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ነቢ​ያ​ትን እን​ዲሁ አድ​ር​ገ​ዋ​ቸው ነበ​ርና። 24ነገር ግን እና​ንተ ባለ​ጠ​ጎች፥ ወዮ​ላ​ችሁ፥ ደስ​ታ​ች​ሁን ጨር​ሳ​ች​ኋ​ልና። 25ዛሬ ለም​ት​ጠ​ግቡ፥ ወዮ​ላ​ችሁ፥ ትራ​ባ​ላ​ች​ሁና፤ ዛሬ ለም​ት​ስ​ቁም ወዮ​ላ​ችሁ፥ ታዝ​ና​ላ​ች​ሁና፤ ታለ​ቅ​ሳ​ላ​ች​ሁ​ምና። 26ሰዎች ሁሉ ስለ እና​ንተ መል​ካ​ሙን ነገር ቢና​ገ​ሩ​ላ​ችሁ ወዮ​ላ​ችሁ፥ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ለሐ​ሰ​ተ​ኞች ነቢ​ያት እን​ዲህ ያደ​ርጉ ነበ​ርና።
27“ለም​ት​ሰ​ሙኝ ለእ​ና​ንተ ግን እን​ዲህ እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ውደዱ፤ ለሚ​ጠ​ሉ​አ​ች​ሁም መል​ካም አድ​ርጉ። 28የሚ​ረ​ግ​ሙ​አ​ች​ሁን መር​ቁ​አ​ቸው፤ ለሚ​በ​ድ​ሉ​አ​ች​ሁም ጸል​ዩ​ላ​ቸው። 29ጕን​ጭ​ህን ለሚ​መ​ታ​ህም ሁለ​ተ​ኛ​ይ​ቱን ስጠው፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ህን ለሚ​ወ​ስ​ድም ቀሚ​ስ​ህን ደግሞ አት​ከ​ል​ክ​ለው። 30ለሚ​ለ​ም​ን​ህም ሁሉ ስጥ፤ ገን​ዘ​ብ​ህን የሚ​ወ​ስ​ደ​ው​ንም እን​ዲ​መ​ልስ አት​ጠ​ይ​ቀው። 31#ማቴ. 7፥12። ሰዎች ሊያ​ደ​ር​ጉ​ላ​ችሁ እን​ደ​ም​ት​ወ​ዱ​ትም እን​ዲሁ እና​ንተ አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው። 32የሚ​ወ​ድ​ዱ​አ​ች​ሁን ብቻ ብት​ወ​ዱማ እን​ግ​ዲህ ዋጋ​ችሁ ምን​ድን ነው? ይህ​ንስ ኃጥ​ኣ​ንም ያደ​ር​ጋሉ፤ የሚ​ወ​ድ​ዳ​ቸ​ው​ንም ይወ​ድ​ዳሉ። 33በጎ ለሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ላ​ችሁ በጎ ብታ​ደ​ርጉ እን​ግ​ዲህ ዋጋ​ችሁ ምን​ድን ነው? እን​ዲ​ህስ ኃጥ​ኣ​ንም ያደ​ር​ጋሉ። 34እን​ዲ​ከ​ፍ​ላ​ችሁ ተስፋ ለም​ታ​ደ​ር​ጉት ብታ​በ​ድሩ እን​ግ​ዲህ ዋጋ​ችሁ ምን​ድን ነው? ኃጥ​ኣ​ንም በአ​በ​ደ​ሩት ልክ ይከ​ፍ​ሉ​አ​ቸው ዘንድ ለኃ​ጥ​ኣን ያበ​ድ​ራ​ሉና። 35አሁ​ንም ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ውደዱ፤ መል​ካ​ምም አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ እን​ዲ​መ​ል​ሱ​ላ​ችሁ ተስፋ ሳታ​ደ​ርጉ አበ​ድሩ፤ ዋጋ​ች​ሁም ብዙ ይሆ​ናል፤ የል​ዑ​ልም ልጆች ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እርሱ ለበ​ጎ​ዎ​ችና#በግ​ሪኩ “ለማ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑና” ይላል። ለክ​ፉ​ዎች ቸር ነውና። 36ሰማ​ያዊ#በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “ሰማ​ያዊ” የሚ​ለው አይ​ገ​ኝም። አባ​ታ​ችሁ የሚ​ራራ እንደ ሆነ እና​ን​ተም የም​ት​ራሩ ሁኑ። 37አት​ፍ​ረዱ፥ አይ​ፈ​ረ​ድ​ባ​ች​ሁ​ምም፤ አት​በ​ድሉ፥ አይ​በ​ድ​ሉ​አ​ች​ሁ​ምም፤ ይቅር በሉ፥ ይቅ​ርም ይሉ​አ​ች​ኋል። 38ስጡ፥ ይሰ​ጣ​ች​ኋ​ልም፤ የሞ​ላና የበዛ፥ የተ​ት​ረ​ፈ​ረ​ፈም መል​ካም መስ​ፈ​ሪያ በዕ​ቅ​ፋ​ችሁ ይሰ​ጡ​አ​ች​ኋል፤ በሰ​ፈ​ራ​ች​ሁ​በ​ትም መስ​ፈ​ሪያ ይሰ​ፍ​ሩ​ላ​ች​ኋል።”
39 # ማቴ. 15፥14። ምሳ​ሌም መሰ​ለ​ላ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ዕውር ዕው​ርን ሊመራ ይች​ላ​ልን? ሁለ​ቱስ በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ ይወ​ድቁ የለ​ምን? 40#ማቴ. 10፥24-25፤ ዮሐ. 13፥16፤ 15፥20። ከመ​ም​ህሩ የሚ​በ​ልጥ ደቀ መዝ​ሙር የለም፤ ለሁ​ሉም መጠኑ እንደ መም​ህሩ ይሆ​ናል። 41በወ​ን​ድ​ምህ ዐይን ውስጥ ያለ​ውን ጕድፍ ለምን ታያ​ለህ? በዐ​ይ​ንህ ውስጥ ያለ​ውን ምሰሶ አታ​ይ​ምን? 42ወን​ድ​ም​ህ​ንም፦ ወን​ድሜ ሆይ፥ ታገሥ፤ በዐ​ይ​ንህ ያለ​ውን ጕድፍ ላው​ጣ​ልህ ልት​ለው እን​ደ​ምን ትች​ላ​ለህ? አንተ ግን በዐ​ይ​ንህ ውስጥ ያለ​ውን ምሰሶ አታ​ይም፤ አንተ ግብዝ፥ አስ​ቀ​ድሞ ከዐ​ይ​ንህ ምሰ​ሶ​ውን አውጣ፤ ከዚህ በኋላ በባ​ል​ን​ጀ​ራህ ዐይን ውስጥ ያለ​ውን ጕድፍ ታወጣ ዘንድ አጥ​ር​ተህ ታያ​ለህ። 43ክፉ ፍሬን የሚ​ያ​ፈራ መል​ካም ዛፍ የለም፤ መል​ካም ፍሬ የሚ​ያ​ፈራ ክፉ ዛፍም የለም። 44#ማቴ. 12፥33። ዛፍ ሁሉ ከፍ​ሬው ይታ​ወ​ቃል፤ ከእ​ሾህ በለ​ስን አይ​ለ​ቅ​ሙም፤ ከደ​ን​ደ​ርም ወይ​ንን አይ​ለ​ቅ​ሙም። 45#ማቴ. 12፥34። መል​ካም ሰው ከልቡ መል​ካም መዝ​ገብ መል​ካ​ምን ያወ​ጣል፤ ክፉ ሰውም ከልቡ ክፉ መዝ​ገብ ክፉ ነገ​ርን ያወ​ጣል፤ ከልብ የተ​ረ​ፈ​ውን አፍ ይና​ገ​ራ​ልና።
46“ለምን አቤቱ፥ አቤቱ፥ ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ? የም​ላ​ች​ሁ​ንም አታ​ደ​ር​ጉም። 47ወደ እኔ የሚ​መ​ጣና ቃሌን ሰምቶ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውም ሁሉ የሚ​መ​ስ​ለ​ውን አሳ​ያ​ች​ኋ​ለሁ። 48መሠ​ረ​ቱን አጥ​ልቆ ቈፍሮ የመ​ሠ​ረ​ተና ቤቱን በዐ​ለት ላይ የሠራ ሰውን ይመ​ስ​ላል፤ ብዙ ፈሳ​ሾች በመጡ ጊዜ ጎር​ፎች ያን ቤት ገፉት፤ ሊያ​ነ​ዋ​ው​ጡ​ትም አል​ቻ​ሉም፤ በዐ​ለት ተሠ​ር​ቶ​አ​ልና። 49ቃሌን ሰምቶ የማ​ያ​ደ​ር​ገው ሰው ግን ቤቱን ያለ መሠ​ረት በአ​ፈር ላይ የሠራ ሰውን ይመ​ስ​ላል፤ ጎር​ፎች ገፉት፤ ወዲ​ያ​ው​ኑም ወደቀ፤ የዚ​ያም ቤት አወ​ዳ​ደቁ ታላቅ ሆነ።”

Zvýraznění

Sdílet

Kopírovat

None

Chceš mít své zvýrazněné verše uložené na všech zařízeních? Zaregistruj se nebo se přihlas

Video k የሉ​ቃስ ወን​ጌል 6