Logo YouVersion
Ikona vyhledávání

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 3

3
ስለ መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ ስብ​ከት
1ጢባ​ር​ዮስ ቄሣር በነ​ገሠ በዐ​ሥራ አም​ስት ዓመት ጴን​ጤ​ና​ዊው ጲላ​ጦስ የይ​ሁዳ ገዢ ሆኖ ሳለ፥ ሄሮ​ድ​ስም በገ​ሊላ የአ​ራ​ተ​ኛው ክፍል ገዢ ሳለ፥ ወን​ድሙ ፊል​ጶ​ስም የኢ​ጡ​ር​ያ​ስና የጥ​ራ​ኮ​ኒ​ዶስ አራ​ተኛ ክፍል ገዢ፥ ሊሳ​ን​ዮ​ስም የሳ​ብ​ላ​ኒስ አራ​ተኛ ክፍል ገዢ ሆነው ሳሉ፥ 2ሐናና ቀያ​ፋም ሊቃነ ካህ​ናት በነ​በ​ሩ​በት ወራት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በም​ድረ በዳ ወደ ዘካ​ር​ያስ ልጅ ወደ ዮሐ​ንስ መጣ። 3ስለ ኀጢ​አት ስር​የት ለን​ስሓ የሚ​ያ​በቃ ጥም​ቀ​ትን እየ​ሰ​በከ በዮ​ር​ዳ​ኖስ አው​ራጃ ዞረ። 4በም​ድረ በዳ የሚ​ጮኽ የአ​ዋጅ ነጋሪ ድምፅ በነ​ቢዩ በኢ​ሳ​ይ​ያስ መጽ​ሐፍ ቃል እንደ ተጻፈ፥ እን​ዲህ ሲል፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ጥረጉ፤ ጥር​ጊ​ያ​ው​ንም አስ​ተ​ካ​ክሉ። 5ጐድ​ጓ​ዳው ሁሉ ይምላ፤ ተራ​ራ​ውም፥ ኮረ​ብ​ታ​ውም ሁሉ ዝቅ ይበል፤ ሰን​ከ​ል​ካ​ላ​ውም የቀና ጥር​ጊያ ይሁን፤ ወጣ ገባው መን​ገ​ድም ይስ​ተ​ካ​ከል። 6#ኢሳ. 40፥3-5። ሰውም ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትድ​ግና ይይ።”
7 # ማቴ. 12፥34፤ 23፥33። ዮሐ​ን​ስም ሊያ​ጠ​ም​ቃ​ቸው የመ​ጡ​ትን ሰዎች እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንት የእ​ፉ​ኝት ልጆች፥ ከሚ​መ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ታመ​ልጡ ዘንድ ማን ነገ​ራ​ችሁ? 8#ዮሐ. 8፥33። እን​ግ​ዲህ ለን​ስሓ የሚ​ያ​በ​ቃ​ች​ሁን ሥራ ሥሩ፤ አብ​ር​ሃም አባ​ታ​ችን አለን በማ​ለት የም​ታ​መ​ልጡ አይ​ም​ሰ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮች ለአ​ብ​ር​ሃም ልጆ​ችን ማስ​ነ​ሣት እን​ደ​ሚ​ችል እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ። 9#ማቴ. 7፥19። እነሆ፥ ምሳር በዛ​ፎች ላይ ተቃ​ጥ​ቶ​አል፤ መል​ካም ፍሬ የማ​ያ​ፈ​ራ​ው​ንም ዛፍ ሁሉ ይቈ​ር​ጡ​ታል፤ ወደ እሳ​ትም ይጥ​ሉ​ታል።”
10ሕዝ​ቡም፥ “እን​ግ​ዲህ ምን እና​ድ​ርግ?” ብለው ጠየ​ቁት። 11እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሁለት ልብስ ያለው አን​ዱን ለሌ​ለው ይስጥ፤ ምግብ ያለ​ውም እን​ዲሁ ያድ​ርግ።” 12#ሉቃ. 7፥29። ቀራ​ጮ​ችም ሊያ​ጠ​ም​ቃ​ቸው መጡና፥ “መም​ህር፥ ምን እና​ድ​ርግ?” ብለው ጠየ​ቁት። 13እር​ሱም፥ “ከታ​ዘ​ዛ​ች​ሁት አት​ር​ፋ​ችሁ አት​ው​ሰዱ” አላ​ቸው። 14ጭፍ​ሮ​ችም መጥ​ተው፥ “እኛሳ ምን እና​ድ​ርግ?” አሉት፤ “በደ​መ​ወ​ዛ​ችሁ ኑሩ እንጂ በማ​ንም ግፍ አት​ሥሩ፤ ማን​ንም አት​ቀሙ፤ አት​በ​ድ​ሉም” አላ​ቸው።
15ሕዝ​ቡም ሁሉ በል​ባ​ቸው ዐሰቡ፤ ዮሐ​ን​ስም ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ መሰ​ላ​ቸው። 16ዮሐ​ን​ስም መልሶ ሁሉ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ በውኃ አጠ​ም​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ግን የሚ​በ​ል​ጠኝ የጫ​ማ​ውን ማሰ​ሪያ እንኳ ልፈ​ታ​ለት የማ​ይ​ገ​ባኝ ይመ​ጣል፤ እርሱ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ፥ በእ​ሳ​ትም ያጠ​ም​ቃ​ች​ኋል። 17መንሹ በእጁ ነው፤ የዐ​ው​ድ​ማ​ው​ንም እህል ያጠ​ራል፤ ስን​ዴ​ው​ንም በጎ​ተ​ራው ይሰ​በ​ስ​ባል፤ ገለ​ባ​ውን ግን በማ​ይ​ጠፋ እሳት ያቃ​ጥ​ላል።”
18ሕዝ​ቡ​ንም ይገ​ስ​ጻ​ቸ​ውና በሌ​ላም በብዙ ነገር የም​ሥ​ራች ይነ​ግ​ራ​ቸው ነበር።
ስለ ዮሐ​ንስ መጥ​ምቅ መታ​ሰር
19ዮሐ​ን​ስም የአ​ራ​ተ​ኛው ክፍል ገዢ ሄሮ​ድ​ስን የወ​ን​ድ​ሙን የፊ​ል​ጶ​ስን ሚስት ሄሮ​ድ​ያ​ዳን ስለ​ማ​ግ​ባ​ቱና ሄሮ​ድስ ያደ​ር​ገው ስለ​ነ​በ​ረው ክፉ ነገር ሁሉ ይገ​ሥ​ጸው ነበር። 20#ማቴ. 6፥17-18። ደግ​ሞም ከዚህ ሁሉ በላይ ጨምሮ ዮሐ​ን​ስን ተቀ​የ​መ​ውና በግ​ዞት ቤት አስ​ገ​ባው።
ጌታ​ችን ስለ መጠ​መቁ
21ሕዝ​ቡም ሁሉ ከተ​ጠ​መቁ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ተጠ​መቀ፤ ሲጸ​ል​ይም ሰማይ ተከ​ፈተ። 22#ዘፍ. 22፥2፤ መዝ. 2፥7፤ ኢሳ. 42፥1፤ ማቴ. 3፥17፤ ማር. 1፥11። መን​ፈስ ቅዱ​ስም የር​ግብ መልክ ባለው አካል አም​ሳል በእ​ርሱ ላይ ወረደ፤ ከሰ​ማ​ይም፥ “የም​ወ​ድህ፥ በአ​ን​ተም ደስ የሚ​ለኝ ልጄ አንተ ነህ” የሚል ቃል መጣ። ሉቃ. 9፥35።
ስለ ጌታ​ችን ትው​ልድ መጽ​ሐፍ
23የጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም#ግሪኩ “ማስ​ተ​ማር ሲጀ​ምር” የሚል ይጨ​ም​ራል። ዕድ​ሜዉ ሠላሳ ዓመት ያህል ነበር፤ የዮ​ሴፍ ልጅም ይመ​ስ​ላ​ቸው ነበር። 24የኤሊ ልጅ፥ የማቲ ልጅ፥ የሌዊ ልጅ፥ የሜ​ልኪ ልጅ፥ የዮና ልጅ፥ የዮ​ሴፍ ልጅ፥ 25የማ​ታ​ትዩ ልጅ፥ የአ​ሞጽ ልጅ፥ የና​ሆም ልጅ፥ የኤ​ስ​ሎም ልጅ፥ የናጌ ልጅ፥ 26የማ​አት ልጅ፥ የማ​ታ​ትዩ ልጅ፥ የሴ​ሜይ ልጅ፥ የዮ​ሴፍ ልጅ፥ የዮዳ ልጅ፥ 27የዮ​ናን ልጅ፥ የሬስ ልጅ፥ የዘ​ሩ​ባ​ቤል ልጅ፥ የሰ​ላ​ት​ያል ልጅ፥ የኔሪ ልጅ፥ 28የሜ​ልኪ ልጅ፥ የሐዲ ልጅ፥ የዮሳ ልጅ፥ የቆ​ሳም ልጅ፥ የኤ​ል​ሞ​ዳም ልጅ፥ የኤር ልጅ፥ 29የዮ​ሴዕ ልጅ፥ የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ፥ የዮ​ራም ልጅ፥ የማ​ጣት ልጅ፥ የሌዊ ልጅ፥ 30የስ​ም​ዖን ልጅ፥ የይ​ሁዳ ልጅ፥ የዮ​ሴፍ ልጅ፥ የዮ​ናን ልጅ፥ የኤ​ል​ያ​ቄም ልጅ፥ 31የሜ​ልያ ልጅ፥ የማ​ይ​ናን ልጅ፥ የማ​ጣት ልጅ፥ የና​ታን ልጅ፥ የዳ​ዊት ልጅ፥ 32የዕ​ሤይ ልጅ፥ የኢ​ዮ​ቤድ ልጅ፥ የቦ​ዔዝ ልጅ፥ የሰ​ል​ሞን ልጅ፥ የነ​ዓ​ሶን ልጅ፥ 33የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ፥ የአ​ራም ልጅ፥ የኦ​ርኒ ልጅ፥ የኤ​ስ​ሮም ልጅ፥ የፋ​ሬስ ልጅ፤ የይ​ሁዳ ልጅ፥ 34የያ​ዕ​ቆብ ልጅ፥ የይ​ስ​ሐቅ ልጅ፥ የአ​ብ​ር​ሃም ልጅ፥ የታራ ልጅ፥ የና​ኮር ልጅ፥ 35የሴ​ሩኅ ልጅ፥ የራ​ግው ልጅ፥ የፋ​ሌቅ ልጅ፥ የኤ​ቦር ልጅ፥ የሳላ ልጅ፥ 36የቃ​ይ​ናን ልጅ፥ የአ​ር​ፋ​ክ​ስድ ልጅ፥ የሴም ልጅ፥ የኖኅ ልጅ፥ የላ​ሜሕ ልጅ፥ 37የማ​ቱ​ሳላ ልጅ፥ የሄ​ኖክ ልጅ፥ የያ​ሬድ ልጅ፥ የመ​ላ​ል​ኤል ልጅ፥ የቃ​ይ​ናን ልጅ፥ 38የሄ​ኖስ ልጅ፥ የሴት ልጅ፥ የአ​ዳም ልጅ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ።

Zvýraznění

Sdílet

Kopírovat

None

Chceš mít své zvýrazněné verše uložené na všech zařízeních? Zaregistruj se nebo se přihlas

Video k የሉ​ቃስ ወን​ጌል 3