YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 68

68
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ በመ​ለ​ከ​ቶች የዳ​ዊት መዝ​ሙር
1አቤቱ፥ ውኃ እስከ ነፍሴ ደር​ሶ​ብ​ኛ​ልና አድ​ነኝ።
2በጥ​ልቅ ረግ​ረግ ጠለ​ቅሁ ኀይ​ልም የለ​ኝም፤
ወደ ጥልቁ ባሕ​ርም ደረ​ስሁ ማዕ​በ​ሉም አሰ​ጠ​መኝ።
3በጩ​ኸት ደከ​ምሁ፥ ጉሮ​ሮ​ዬም ሻከረ፤#ዕብ. “ሰለለ” ይላል።
አም​ላ​ኬን ተስፋ ሳደ​ርግ ዐይ​ኖቼ ፈዘዙ።
4በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ሉኝ ከራሴ ጠጉር በዙ፤
በዐ​መፅ የሚ​ከ​ብ​ቡኝ#ዕብ. “የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱኝ” ይላል። ጠላ​ቶቼ በረቱ፤
ያል​ወ​ሰ​ድ​ሁ​ትን ይከ​ፈ​ሉ​ኛል።
5አቤቱ፥ አንተ ስን​ፍ​ና​ዬን ታው​ቃ​ለህ፥
ኃጢ​አ​ቴም ከአ​ንተ አል​ተ​ሰ​ወ​ረም።
6አቤቱ፥ የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ፥ የሚ​ሹህ በእኔ አይ​ፈሩ፤
የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉህ በእኔ አይ​ነ​ወሩ።
7ስለ አንተ ስድ​ብን ታግ​ሻ​ለ​ሁና፥
እፍ​ረ​ትም ፊቴን ሸፍ​ኖ​ኛ​ልና።
8ለወ​ን​ድ​ሞቼ እንደ ባዕድ፥
ለአ​ባ​ቴና#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እናቴ ብቻ” ይላል። ለእ​ና​ቴም ልጆች እንደ እን​ግዳ ሆን​ሁ​ባ​ቸው።
9የቤ​ትህ ቅን​ዓት በል​ቶ​ኛ​ልና፥
የሚ​ሰ​ድ​ቡ​ህም ስድብ በላዬ ወድ​ቆ​አ​ልና።
10ሰው​ነ​ቴን በጾም አደ​ከ​ም​ኋት፥
ስድ​ብ​ንም ሆነ​ብኝ።
11ማቅ ለበ​ስሁ መተ​ረ​ቻም ሆን​ሁ​ላ​ቸው።
12በደጅ የሚ​ቀ​መጡ በእኔ ይጫ​ወ​ታሉ፤
ወይን የሚ​ጠ​ጡም በእኔ ይዘ​ፍ​ናሉ።
13እኔስ በጸ​ሎቴ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ#ዕብ​ራ​ይ​ስጥ ከግ​እ​ዙና ከግ​ሪኩ የአ​ነ​ጋ​ገር ልዩ​ነት አለው።
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታው በጊ​ዜው ነው፤
ይቅ​ር​ታህ ብዙ ሲሆን መድ​ኃ​ኒቴ ሆይ፥ በእ​ው​ነት አድ​ነኝ።
14እን​ዳ​ይ​ው​ጠኝ ከረ​ግ​ረግ አው​ጣኝ፤
ከጠ​ላ​ቶ​ችና ከጥ​ልቅ ውኃ አስ​ጥ​ለኝ።
15የውኃ ማዕ​በል አያ​ስ​ጥ​መኝ፥ ጥል​ቁም አይ​ዋ​ጠኝ፥
ጕድ​ጓ​ዶ​ችም አፋ​ቸ​ውን በኔ ላይ አይ​ክ​ፈቱ፤
16አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ትህ መል​ካም ናትና ስማኝ፤
እንደ ይቅ​ር​ታ​ህም ብዛት ወደ እኔ ተመ​ል​ከት፤
17ከባ​ሪ​ያ​ህም ፊት​ህን አት​መ​ልስ፤
ተጨ​ን​ቄ​አ​ለ​ሁና ፈጥ​ነህ ስማኝ።
18ነፍ​ሴን ተመ​ል​ክ​ተህ ተቤ​ዣት፤
ስለ ጠላ​ቶ​ችም አድ​ነኝ።
19አንተ ስድ​ቤን፥ እፍ​ረ​ቴ​ንም፥
ነው​ሬ​ንም ታው​ቃ​ለህ፤
በሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ሁሉ ፊት።#ዕብ. “የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ሁሉ በፊ​ትህ ናቸው” ይላል።
20ሰው​ነቴ ስድ​ብ​ንና ውር​ደ​ትን ታገ​ሠች፤
አዝኜ ተቀ​መ​ጥሁ፥ የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ኝ​ም አጣሁ።
21በመ​ብሌ ውስጥ ሐሞ​ትን ጨመሩ፥
ለጥ​ማ​ቴም ሆም​ጣ​ጤን አጠ​ጡኝ።
22ማዕ​ዳ​ቸው በፊ​ታ​ቸው
ለወ​ጥ​መድ፥ ለፍ​ዳና ለዕ​ን​ቅ​ፋት ትሁ​ን​ባ​ቸው፤
23ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ያዩ ይጨ​ልሙ፥
ጀር​ባ​ቸ​ውም ዘወ​ትር ይጉ​በጥ።
24መዓ​ት​ህን በላ​ያ​ቸው አፍ​ስስ፥
የቍ​ጣህ መቅ​ሠ​ፍ​ትም ያግ​ኛ​ቸው።
25ከተ​ማ​ቸው በረሃ ትሁን፥
በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም የሚ​ቀ​መጥ አይ​ገኝ፤
26አንተ የቀ​ሠ​ፍ​ኸ​ውን እነ​ርሱ ተከ​ት​ለ​ዋ​ልና፥
በቍ​ስ​ሌም ላይ ቍስ​ልን ጨመ​ሩ​ብኝ።
27በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ላይ ኃጢ​አ​ትን ጨም​ር​ባ​ቸው፥
በጽ​ድ​ቅ​ህም አይ​ግቡ።
28ከሕ​ያ​ዋን መጽ​ሐፍ ይደ​ም​ሰሱ፥
ከጻ​ድ​ቃ​ንም ጋር አይ​ጻፉ።
29እኔ ድሃና ቍስ​ለኛ ነኝ፤
የፊቴ፥ መድ​ኀ​ኒት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቀ​በ​ለኝ።#ዕብ. “የፊ​ትህ መድ​ኀ​ኒት ይቀ​በ​ለኝ” ይላል።
30የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም በዝ​ማሬ አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥
በም​ስ​ጋ​ናም ከፍ ከፍ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።
31ቀን​ድና ጥፍር ካላ​በ​ቀለ ከእ​ም​ቦሳ ይልቅ
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘ​ዋ​ለሁ።
32ድሆች ይዩ ደስም ይበ​ላ​ቸው፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈል​ጉት፥ ነፍ​ሳ​ች​ሁም ትድ​ና​ለች።
33እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድሆ​ችን ሰም​ቶ​እ​ቸ​ዋ​ልና፥
እስ​ረ​ኞ​ች​ንም አል​ና​ቃ​ቸ​ው​ምና።
34ሰማ​ይና ምድር፥ ባሕ​ርም፥
በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀሱ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።
35እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዮ​ንን አድ​ኗ​ታ​ልና፥#ዕብ. “ያድ​ና​ታ​ልና” ይላል።
የይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ይሠ​ራ​ሉና፤
በዚ​ያም ይቀ​መ​ጣሉ ይወ​ር​ሷ​ታ​ልም።
36የባ​ሪ​ያ​ዎ​ችህ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የባ​ሪ​ያ​ዎቹ” ይላል። ዘሮች ይኖ​ሩ​ባ​ታል፥
ስም​ህን#ስሙን። የሚ​ወ​ድዱ በው​ስጧ ይቀ​መ​ጣሉ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መዝ​ሙረ ዳዊት 68