መዝሙረ ዳዊት 64
64
ለመዘምራን አለቃ የዳዊት የምስጋና መዝሙር።
1አቤቱ፥ በጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል፥
ለአንተም በኢየሩሳሌም ጸሎት ይቀርባል።
2ወደ አንተ የሚመጣ የሰውን ሁሉ ጸሎት ስማ
3የዐመፀኞች ነገር በረታብን፤
ኀጢአታችንንስ አንተ ይቅር ትላለህ።
4አንተ የመረጥኸው በአደባባዮችህም ለማሳደር የተቀበልኸው ብፁዕ ነው፤
አቤቱ፥ ከቤትህ በረከት ጠገብን።
5ቤተ መቅደስህ ቅዱስ ነው በጽድቅም ድንቅ ነው።
በምድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስፋቸው የሆንህ፥
አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ ስማን።
6በኀይልህ ተራሮችን አጸናሃቸው፥
እነርሱም በኀይል ታጥቀዋል።
7የባሕሩን ዓሣ አንበሪ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የባሕሩን ጥልቀት” ይላል። የሚያውከው እርሱ ነው
የሞገድዋንም ድምፅ የሚቃወመው ማን ነው?
8ከተአምራትህ የተነሣ አሕዛብ ይደንግጣሉ፥
በምድር ዳርቻም የሚኖሩ ይፈራሉ፤
በጥዋት ይወጣሉ፥ ማታም ይደሰታሉ።
9ምድርን ጐበኘሃት አረካሃትም፥
ብልጽግናዋንም እጅግ አበዛህ፤
የእግዚአብሔር ወንዝ ውኆችን የተመላ ነው፤
ምግባቸውን አዘጋጀህ፥ እንዲሁ ታሰናዳለህና።
10ትልምዋን አርካው፥
መከሯንም አብጀው፤
በነጠብጣብህም ደስ ብሏት ትበቅላለች
11የምሕረትህን ዓመት አክሊል ትባርካለህ#ዕብ. “ዓመቱን በቸርነትህ ታቀዳጃለህ” ይላል።
ምድረ በዳዎችም ጠልን ይጠግባሉ።
12የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ፥
ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ።
13የበጎች አውራዎችም#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “መሰማሪያዎች መንጎችን ለበሱ” ይላል። ስብን ይለብሳሉ፥
ሸለቆዎችም ስንዴን ይመላሉ፤
እየጮሁ ያመሰግናሉ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 64: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in