መዝሙረ ዳዊት 63
63
ለመዘምራን አለቃ የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ ወደ አንተ የለመንሁትን ጸሎቴን ስማኝ፥
ከጠላትም ጥርጥር#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ፍርሀት” ይላል። ነፍሴን አድናት።
2ከክፉዎች ሴራ
ከብዙዎች ዐመፅ አድራጊዎች ሰውረኝ።
3እንደ እባብ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሰይፍ” ይላል። ምላሳቸውን አሰሉ፤
መራራ ነገርን ለማድረግ፥
4ንጹሕንም በስውር ለመግደል ቀስትን ገተሩ፤
በድንገት ይነድፏቸዋል#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ይነድፏታል” ይላል። አይፈሩምም።
5ለእነርሱ ለራሳቸው ክፉ ነገርን አጸኑ፤
ወጥመድን ይሰውሩ ዘንድ ተማከሩ፤
የሚያምንም የለም ይላሉ።
6ዐመፃን ፈለጓት፥
ሲፈትኑም ሲጀምሩም አለቁ፤
ሰው በጥልቅ ልብ#ከዕብራይስጥ ይለያል። ውስጥ ይገባል፥
7እግዚአብሔርም ከፍ ከፍ ይላል።
መቅሠፍታቸው እንደ ልጆች ሕንፃ ሆነ፤#ዕብ. “የድንገት ፍላጻ ይነድፋቸዋል” ሲል ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቍስላቸው በልጆች ፍላጻ ሆነ” ይላል።
8አንደበታቸው በላያቸው ደከመ፥
የሚያዩአቸውም ሁሉ ደነገጡ።
9ሰው ሁሉ ፈራ፥
የእግዚአብሔርንም ሥራ ተናገሩ፥
ሥራውንም ዐወቁ።
10ጻድቅ በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል፥ በእርሱም ይታመናል፤
ልባቸውም የቀና ሁሉ ይከብራሉ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 63: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in