YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 62

62
በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድረ በዳ በነ​በረ ጊዜ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አም​ላኬ፥ አም​ላኬ፥ ወደ አንተ እገ​ሠ​ግ​ሣ​ለሁ፤
ነፍሴ አን​ተን ተጠ​ማች፥
እን​ጨ​ትና ውኃ በሌ​ለ​በት ምድረ በዳ
ሥጋ​ዬን ለአ​ንተ እን​ዴት ልዘ​ር​ጋ​ልህ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሥጋዬ አን​ተን እን​ዴት ናፈ​ቀች” ይላል።
2ኀይ​ል​ህ​ንና ክብ​ር​ህን ዐውቅ ዘንድ
እን​ዲሁ በመ​ቅ​ደስ ውስጥ ተመ​ለ​ከ​ት​ሁህ።
3ምሕ​ረ​ትህ ከሕ​ይ​ወት ይሻ​ላ​ልና፥
ከን​ፈ​ሮቼ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል።
4እን​ዲህ በሕ​ይ​ወቴ ዘመን አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥
በአ​ን​ተም ስም እጆ​ችን አነ​ሣ​ለሁ።
5ነፍሴ በቅ​ቤና በስብ እን​ደ​ሚ​ጠ​ግቡ ትጠ​ግ​ባ​ለች፥
ደስ​ተ​ኞች ከን​ፈ​ሮቼም ስም​ህን ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።
6በመ​ኝ​ታ​ዬም አስ​ብ​ሃ​ለሁ፥
በማ​ለ​ዳም እና​ገ​ር​ል​ሃ​ለሁ፤
7ረዳቴ ሆነ​ኽ​ል​ኛ​ልና፥
በክ​ን​ፎ​ች​ህም ጥላ እታ​መ​ና​ለሁ።
8ነፍሴ በኋ​ላህ ተከ​ታ​ተ​ለች፥
እኔ​ንም ቀኝህ ተቀ​በ​ለ​ችኝ።
9እነ​ርሱ ግን ነፍ​ሴን ለከ​ንቱ ፈለ​ጓት፤
ወደ ምድር ጥልቅ ይግቡ።
10በሰ​ይፍ እጅ አል​ፈው ይሰጡ፥
የቀ​በ​ሮ​ዎ​ችም ዕድል ፋንታ ይሁኑ።
11ንጉሥ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይለ​ዋል፤
በእ​ር​ሱም የሚ​ምል ሁሉ ይከ​ብ​ራል፥
ዐመ​ፅን የሚ​ና​ገር አፍ ይዘ​ጋ​ልና።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in